Translation is not possible.

ሴት ልጅ በደደቦች ሸሪዓ እና

በነቢያቶች ሸሪዓ

⚡️በየ መድረኩ መዝፈንን ሀላል አደረጉላት፣

አላህ ግን አዛን፣ ኢቃማና አሚን በማለት ድምጿን ከፍ ከማድረግ ከልክሏታል።

⚡በሲኒማ ቤቶች እና በመድረክ ላይ እንድትሰራ ፈቀዱላት አላህም የጁምአ ሰላት እና የጀመዓ ሰላትን በሷ ላይ ግዴታ እንዳይሆን አድርጓል ።

🩸የኦሎምፒክ እና የማራቶን ሻምፒዮን አደረጓት አላህ ግን በሁለቱ ምልክቶች መካከል በሰፍዋና እና በመርዋ መካከል እንዳትሮጥ የከለከላት ጨዋነቷን እና ንፅህናዋን ለመጠበቅ ነው።

⚡በቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅቶች እና ሌሎችም ደንበኞችን ለመሳብ በድምፅዋ ጥሪን በመመለስ ላይ በኤሌክትሮኒክስ ማስታወቂያ ተጠቅመውባታል።

አላህ ግን በሶላት ላይ ኢማሙ ቢሳሳት እንኳ ከማጨብጨብ ውጪ ድምፃን ከፍ አድርጋ" ሱብሃነላህ" በማለት ድምፃን ከማሰማት ከልክሏታል።

🩸በመዝናኛ ጉዞ ላይ ያለ መህራም( ያለ ወንድ ቤተሰብ) እንድትጓዝ አደረጓት።

አላህ ከእርሷ ላይ አንድ መህረም ካላገኘች ከእስልምና ማእዘን ውስጥ የሆነውን ሀጅን እንኳን አውርዶላታል።

⚡️የስፖርት ቡድኖችን ለማበረታታት እና ለመደገፍ ወሰዷት፤ አላህም ለጂሃድ ሃይማኖትን ለመደገፍ እንዳትወጣ ከልክሏታል።

🩸ከቤቷ ሽቶ የተቀባች፣ የተዋበች ውበቷን ለአደባባይ የገለፅች ሆና እንድትወጣ አደረጓት ።

አላህ ግን በእግሮቿ ላይ ያደረገችውን ጌጥ ለሰዎች ይሰማ ዘንድ መሬትን በእግሮቿ እየደበደበች እንዳትሄድ ከልክሏታል።

✍ ከሸይኽ አብድገንይ ገፅ ተወስዶ የተተረጎመ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/AbuEkrima

Telegram: Contact @AbuEkrima

Telegram: Contact @AbuEkrima

ይህ ቻናል የተለያዩ አስተማሪና አነቃቂ የሆኑ ትምህሮችን፣ ሙሃደራዎችን፣ የቀደምት አኢማዎችን ንግግሮች እንዲሁም የተለያዩ በጊዜያችን ያሉትን የሱና ዑለማዎች ፈትዋና ንግግር የምናቀርብበት ቻናል ነው።
Send as a message
Share on my page
Share in the group