UMMA TOKEN INVESTOR

A jelil umer shared a
Translation is not possible.

የዓለም ህዝብ ግን አይገርምም⁉️

=======================

(ዓለም በዚህ ዘመን አይታው የማታውቀው የጦር ወንጀልና የዘር ጭፍጨፋ በጘዝ'ዛ)

||

✍ 365 km² ስፋት ባላት አነስተኛ ከተማ ውስጥ 2.3+ ሚሊዮን ዜጎች ተጠጋግተው ይኖሩባታል። በዚህች densely populated በሆነች ከተማ ላይ ለተከታታይ 3 ሳምንታት ያላባራ ከ12 ሺህ ቶን በላይ ቦምብ ሲዘንብ፤ በዚህም ሳቢያ፦

1) በትንሹ 7,028 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙስሊሞች ሲገደሉ፣

2) ከ70% በላይ የሚሆኑት ህፃናትና ሴቶች ሲሆኑ (2,913 ህፃናትና 1,709 ሴቶች)፣

3) 18,482 የሚሆኑት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ሲዳረጉ፣

4) ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 481 የሚሆኑት ሲገደሉ (ከመካከላቸው 209 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው።)፣

5) ከ1,650 በላይ የሚሆኑት ጀናዛቸው እንኳ ሳይገኝ እስካሁን ድረስ በቦምብ በፈራረሱት ህንፃዎች ስር ሲሆኑ (ከመካከላቸው 940 ህፃናት አሉበት።)፣

6) 731 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙሉ ቤተሰቦች ሲገደሉ፣

⑦) 101 የጤና ባለሙያዎች ሲገደሉና 100 የሚሆኑት ሲቆስሉ፣

⑧) 12 ሆስፒታሎችና 32 የጤና ማዕከላት በነዳጅ እጥረትና በቦምብ ጥቃት ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ፣

9) በኢንኩቤተር ውስጥ የሚገኙ ከ130 በላይ የሚሆኑ ህፃናት ያሉበት ሆስፒታል ባጋጠመው በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ነፍሳቸው በእንጥልጥል ላይ ሲገኝ፣

⑩) ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ንጹሐን ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች፣ በት/ቤቶች፣ በሆስፒታል ግቢዎች፣ በመስጂዶችና ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ሳለ በዛው ባሉበት ጥቃቱ ሲያገኛቸው…

(ከሰው ነፍስ አይበልጥምና ወደ አመድነት ስለተቀየሩት ውብ ህንፃዎችና መሠረተ ልማቶችማ አውርተን አንዘልቀውም።)

የሰለጠነ ተብዬው ዓለም አሁንም «ጦርነቱ ይቁም!» ከማለት ይልቅ «እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት፣ ሐማስ መጥፋቱን ማረጋገጥ አለባት፣ ከጎንሽ ነን፣ ሐማስ ሽብርተኛ ነው፣ በሐማስ ጥቃት ለሞቱተረ እስራኤላዊያን አዝነናል!…» እያሉ ነው።

ትንሽ አሻሻልን የሚሉት ደግሞ ጦርነቱ መቆም የለበትም፤ ግን የተወሰነች እርዳታ ይግባላቸው ይላሉ።

እስካሁን በጋዛ መብራት የለ፣ ውሃ የለ፣ ምግብ የለ፣ ነዳጅ የለ…። በዚህ የተነሳ የቆሰሉትና መደበኛ ህመም የሚታመሙትም መታከም አልቻሉም።

ዙሪያውን በከበባ ስለሆነ ለጠናበት ታማሚ የውጭ ሕክምና እንዲያገኝ ማድረግ አልተቻለም።

እስራኤል ከላይ በአየር ከምታዘንበው የቦምብ ዝናብ ባሻገር ከምግብና ውሃ እንዲሁም ከሕክምና ከልክላ በጅምላ ጭፍጨፋ የጦር ወንጀልና የዘር ማፅዳት ወንጀል በመፈጸም ላይ ትገኛለች። ይህ ሁሉ የሚሆነው ዓለም እያዬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ተመድ ተብዬውም ሆነ የትኛውም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚል ተቋም ሁሉ የውሃ ሽታ ሆኗል። የነርሱ ህግ እነርሱን ለማዳን እንጂ ለሌላው አይሠራም። እነርሱ ዘንድ የሙስሊም፣ የዓረብና የአፍሪካዊ ሞት ከውሻቸው ሞት በታች ነው።

ግን ነፍስ ሁሉ እኩል ናትና የእጃቸውን አንድ ቀን ማግኘት አይችሉም። ነገ ላይ በሌላ የነርሱ አካል ላይ ጥቃት ሲፈጸም በሚዲያቸውም ሆነ ባልተጻፈው ህጋቸው ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ሲለፍፉ እናገኛቸዋለን።

አላህ ውርደታቸውን ያቅርበው፤ ለተበዳዮች ነስሩን ያፍጥነው።

አላህ የአሸናፊዎች ሁሉ አሸናፊ የሆነ ጥበበኛና ታጋሽ ጌታ ነው። አንድ ቀን አይርላቸውም።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
A jelil umer shared a
Translation is not possible.

ፎቶ ①: ወራሪዋ እስራኤል በጋዛ ከተማ ንጹሐን ነዋሪዎች ላይ ህፃናት፣ ሴቶችና አረጋውያን፣ ት/ቤትና ሆስፒታል፣ መጠለያ ካምፕና የእምነት ተቋም ሳትለይ እየፈጸመችው ያለ ያላባራ የቦምብ ማዕበል

ፎቶ ②: ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ወራሪዋ የምድር ጦር ጋዛ ላይ ስለጀመረች የተገደሉባት 11 ወታደሮች

√ አሸባሪዋ አሜሪካ በምትሰጣት ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በአየር ቦምብ በማዝነብ እንጂ እንደ ጀግና ፊት ለፊት ገጥሞ በማሸነፍ'ማ የለችበትም። ልብ ከየት ተገኝቶ!

ጦርነቱ ከተጀመረ 26ኛውን ቀን ይዟል። ወራሪዋ በተለመደው የአሜሪካና አጋሮቿ እገዛ በ1967 በ6 ቀን አሸንፊያለሁ ብላ ስትጎረር ነበር። ግን የአንድት መንደር ታጣቂ ሐማስ የተባለ ቡድን ብቻውን ይሄው አንድ ወር ገደማ ቀጥ አድርጎ ይዟታል። ያውም እርሱ ከአላህ ውጭ ማንም ደጋፊ የለውም። እርሷ ግን የዓለማችን ቁጥር አንድ ጦረኛ በሆነችው አሜሪካና ኃያላን በሚባሉት የአውሮፓ ሃገራት ያላሰለሰ ድጋፍ እየተደረገላት ነው። ጉራ ብቻ መሆኗን ዓለም ታዝቧል። እነዚህ አጋሮቿ ባይኖሩ ኖሮ ደግሞ በ26 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ሐማስ እስራኤልን ተቆጣጥሮ ሊያስገብራት ይችላል።

ከዚህ በተጨማሪ ከዐረብ ሃገራት በባሰ መልኩ ሌሎች ሰብዓዊነት ከተሰማቸው ሃገራት ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ክስረት አጋጥሟታል። እንደ ኮሎምቢያ፣ ቺሊና ቦይሊቪያ ያሉ ሃገራት አምባሳደሯን ከማባረር ጀምሮ ከርሷ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እስከማቋረጥ ደርሰዋል። ከባለፈው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጀምሮ በርካታ የአውሮፓ ሃገራትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከዷት መሆኑን የሚያሳይ አቋም አንጸባርቀዋል። ኢንሻ አላህ ቀስ በቀስ ከዓለም የተነጠለች ብቸኛ ተገፊ መሆኗ አይቀርም።

ጋዛዊያን ግን እንኳን የጦር መሳሪያ ምግብና ውሃ እንኳ እንዳያገኙ ተደርገው ይሄው በፅናት እያሳለፉ ነው።

አላህ ነስሩን ያቅርብላቸውና!

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
A jelil umer shared a
Translation is not possible.

በዩ ቲዩብ ገንዘብ መቀበል እንደት ይታያል⁉️

============================

✍ ሌላኛው ባለፈ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ መልስ ከሰጠባቸው ጥያቄዎች አንዱ የሰማሁት በዩ ቲዩብ ቻነል በኩል ዩ ቲዩብ የሚከፍለውን ገንዘብ በተመለከተ ብይኑ ምንድን ነው የሚለው ነው።

ይህ ብዙዎቻችሁን ስለሚመለከት ቃል በቃል ባይሆን የመልሱን ይዘት ላጋራችሁ።

እኔ እስከማውቀው ድረስ ዩ ቲዩብ ገንዘብ የሚከፍለው ማስታወቂያ እንዲሠራላቸው የሚፈልጉ አካላት ገንዘብ ይከፍሉትና ዩ ቲዩብ ደግሞ ያንን እንዲሰራጭ የሚፈልጉትን ማስታወቂያቸውን በተለያዩ ቻነሎች ላይ የሚለቀቁ ቪድዮዎች ሲታዩ ማስታወቂያው ጣልቃ እንዲገባ በማድረግ ነው። እነዚህ የማስታወቂያ ጣልቃ የሚገባባቸው ቻነሎች ከዩ ቲዩብ ጋር መስፈርቱን አሟልተው ተነጋግረው ይህ ማስታወቂያ በሚሰሯቸው ቪድዮዎች ጣልቃ እንዲገባና ቪድዮዋቸውን የሚያይ እንዲያየው መፍቀዳቸው ነው። (በጎግል AdSense በኩል የሚፈጸመው የዩቲዩብ monetization ማለት ነው በአጭሩ!)

ነገሩ እንደዛ ከሆነ እነዚያ በማስታወቂያነት ጣልቃ የሚገቡት ነገሮች በይዘት ደረጃም ሆነ ማስታወቂያው በሚቀርብበት መንገድ ሐላልነታቸው ሊረጋገጥ ይገባል። ማለትም እነዚህ ማስታወቂያዎች ይዘታቸው በሸሪዓው የተከለከለ ሐራም ነገር መሆን የለበትም። በመሠረታቸው ሐላል ቢሆኑ እንኳ ማስታወቂያ የቀረበበት መንገድ ሐራም መሆን የለበትም። (ለምሳሌ፦ አንድ አዲስ ሐላል ለስላሳ መጠጥ ቢመረትና ያመረተው አካል ማስታወቂያውን ያሠራው በተገላለጠች ሴት ሊሆን ይችላል።)

ስለዚህ እነዚህ በየ ቪድዮው ጣልቃ የሚገቡ ማስታወቂያዎች (Ads) በይዘትም ሆነ በአቀራረብ ሐራም ከሆኑ በነርሱ ሰበብ የተገኘውም ገንዘብ ሐራም ይሆናል። ምክንያቱም አላህን በማመፅና በወንጀል መተባበር ስለሌለብን።

ምናልባት ግን ዩ ቲዩበሩ ከዩ ቲዩብ ጋር ስምምነቱን ሲፈጽም፤ በቪድዮው ላይ ጣልቃ እንዲገቡ የሚፈቅድላቸውን ኮንተንቶች ሐላል ሐላሎቹን ብቻ መርጦ ስምምነት መፈጸም የሚችልበት ነገር ካለ ችግር የለውም። ይሄን ደግሞ እርግጠኛ መሆን አለበት።

እንደ ጥቅል ደግሞ ዲናዊ በሆኑ ቪድዮዎች ገንዘብ ባይቀበልና ለአላህ ብሎ ቢሠራ የተሻለ ነው። ከዚያ ውጭ እንደ አካዳሚክና መሰል ሐላል ኮንተንቶች ላይ ይሻላል። ይሄውም ሐራም ማስታወቂያን መከላከል ከተቻለ ነው።

አላሁ አዕለም! በሉ! በዚህ ዘርፍ ላይ የተሰማራችሁና ለመሠማራት ያቀዳችሁ ካላችሁ ማስታወቂያውን ተውት፤ ወይም ለገንዘብ ከሆነ ደግሞ ሌላ ሐላል ከስብ ፈልጉ። በዚህ ሰበብ ነፍስያችሁን ካላሸነፋችሁ ሌላውንም ሐላል ገንዘባችሁን እንዳይበክልባችሁ።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
A jelil umer shared a
Translation is not possible.

ዲቪ መሙላት እንደት ይታያል⁉️

=====================

✍ ባለፈ እሁድ በኢማሙ አሕመድ መስጅድ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ በነበረው የፈታዋ ፕሮግራም ላይ መልስ ከሰጠባቸው ጥያቄዎች አንዱ ወደ ሃገረ አሜሪካ ለመሄድና ነዋሪ ለመሆን የሚሞላውን የዲቪ እጣ (DV Lottery) በተመለከተ ነበር።

ጉዳዩ የብዙዎቻችሁም ጥያቄ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ቃል በቃል ባይሆንም የመልሱን ጭብጥ ላጋራችሁ።

ሐቂቃ ወደ ኩፍ'ር ሃገር ሂዶ በነርሱ የፈሳድ ህግ ተገዢ ሆኖ ለመተዳደር መሄድ አይፈቀድም። ከዲን አንፃር እነርሱ ጋ ካለው ፈሳድ በአንፃሩ የኛ የተሻለ ነው። (ምንም እንኳ የኛም ሃገር በሸሪዓህ የሚተዳደር ባይሆንም!)

አንድ ሰው የቱንም ያክል በዲኑ ጠንካራ ቢሆንም እዛ ሲሄድ ያለው የፈሳድ ጫና ከመክበዱ የተነሳ ሳያስበው ቀስ በቀስ እየተሸረሸረ ይሄዳል። በተለይ ደግሞ የልጆች ጉዳይ አሳሳቢ ነው። አንድ ሰው ለራሱ እዚህ የሆነ የዲን ግንዛቤ ኖሮት በዛ ጥንካሬው እቋቋማለሁ ብሎ ቢያስብ እንኳ እዛ ሂዶ ልጅ ከወለደ በኋላ ግን፤ ያለው የሃገሪቱ ህግ ወላጅ በልጁ ላይ እንኳ መብት እንዳይኖረው ተደርጎ የተደነገገ ስለሆነ ልጆችን በመልካም ኢስላማዊ አስተዳደግ ለማኖር ይከብዳል።

ስለዚህ የምንሄደው መቼም ዱንያን ፍለጋ ስለሆነ ያ ዱንያ ዲንን የሚያሳጣ ከሆነ ከነ ድህነታችን ይሄው ሃገራችን ይሻለናል።

(በተለይም ይሄ ከቅርብ ጊዜ በኋላ የጀመሩት ወላጆች የልጆቻቸውን እንኳ ጾታ መምረጥ አይችሉም ተብሎ ህፃናቱ ራሳቸው ናቸው ሲያድጉ ጾታቸውን የሚመርጡት ተብሎ የተደነገገው ነገር፤ በተለያዩ የትምህርት አይነቶቻቸው ላይ የሰገሰጉት የፈሳድ ጉዳይ፣ ለምሳሌ፦ ግብረ ሶዶማዊነትን ከመብት መቁጠር፣ እምነት አልባነትን… ወዘተ የልጆችን ለጋ አስተሳሰብ ይቀይራል። ገና አስተሳሰባቸው ሳይጎለብት ይሄንና መሰል ፈሳዶችን እየተጋቱ ያደጉ ልጆች ወላጆች ላስተካክላቸው ቢሉ እንኳ አይችሉም።

ይሄንን ደግሞ በደንብ የሚያውቁት እዛው ውጭ ላይ ያሉ ልጅ ያላቸው ወላጆች ናቸው። ሌላው ቀርቶ ኢስላማዊ ት/ቤቶች ራሱ ይሄንና መሰል ነገሮች ከመተዳደሪያቸው ውስጥ አስገብተው እንዲተገብሩ በሃገሪቱ ህግ ጫና የሚደረግባቸው አሉ። አሜሪካ ብቻ ሳይሆን እንደ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ደንማርክና መሰል የአውሮፓ ሃገራት ላይም ይህ አይነት ፈሳድ በብዛት ስላለ በተለይም ለልጁና ለሚስቱ የወደፊት ህይዎት የሚቆረቆር ወላጅ ወደነዚህ የፈሳድ ሃገራት ለመኖር ባይመርጥ የተሻለ ነው።)

አላሁ አዕለም!

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
A jelil umer shared a
Translation is not possible.

ትዊተር ላይ ግቡና እነዚህን ሃሽታጎች ደጋግማችሁ ለጥፉ።

DO NOT STOP TALKING ABOUT PALESTINE

LET'S SPREAD THE WORDS‼️📢

IT'S A HUMANITARIAN DUTY!

No internet communication, no food, no safe place to live.

How many PALESTINIAN CHILDREN have to die before Israel stops their TERRORISM?

#stopgenocideingaza

#ceasefirenow

#nooilforisrael

https://x.com/MuradTadesse/sta....tus/1719053090739937

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group