UMMA TOKEN INVESTOR

1 year Translate
Translation is not possible.

✅ በቲንሹ የሴት ልጅ ተወዳጅ ባህሪዎች ....

       ~   ~     ~     ~       ~      ~

~ሁሌም ምትፈልግ የጌታዋን ውዴታ፣

~ለባልዋ ምታስብ እዲኖር በደስታ፣

~አምስት ወቅት ሰላቷን ሳታዛንፍ ሰጋጅ፣

~ያለትልቅ ጉዳይ የማትወጣ ከደጅ፣

~ ቅርፃ ማይታወቅ ሂጃባን ምጠብቅ፣

~ ድምፃ ከፍ ማይል የማታስረቀርቅ፣

~ከጎኖ ሲለያት ለባሎ ምትጨነቅ፣

~ ከወጣ እስኪመለስ እሱን ምትናፍቅ፣

~ጉዳትም ሲደርስበት ከልባ ምትራራ

~ሚስጥሩን ጠባቂ ለሁሉ ማዘራ!!

~ ለትዳሯ ታማኝ ቤተሰብ አክባሪ!!

~ ልጅ ተከባካቢ ተውሂድ አስተማሪ!!

~ሱናን የጨበተች ጌታዋን አወዳሽ!!

~ ጎሮቤት አክባሪ በመከራ ታጋሽ!!

~ እውነት ተናጋሪ ብትሆንም ተወቃሽ !!

t.me/https_Asselfya

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አዎ በአላህ ፍቃድ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

•አንዳንድ ወዳጆች አሉ… አንተን እንደራሱ የሚወድ፤ ምናልባት ከራሱም የሚያስበልጥህ፡፡ በሁሉ ነገር የቅርብህ ነው፣ ብታጠፋ ዝም አይልህም፣ ብትሳሳትም አይስቅብህም፣ ጥሩ ባትሆን እንኳ ያስተካክልሃል እንጂ በሌላ አይቀይርህም፡፡

• አንዳንድ ወዳጆች አሉ…ስሜትህን የሚረዳልህ፣ ብሶትህን የሚያዳምጥልህ፣ እንባህን የሚጠርግልህ፣ እጅህን ይዞ የሚያነሳ ወዳጅ…

• አንዳንድ ወዳጆች አሉ… ቅድሚያ ላንተ ይሰጣል፣ ጉዳዬ አንተ ነህ ይላል፣ አንዳንዴ ከነፍስህ ጭምር ቀድሞ ይደርስልሃል፣ ነፍስህ በመጥፎ ስታዝህ እሱ በመልካም ነገር ያዝሃል።

• አንዳንድ ወዳጆች አሉ… በቃል ሳይሆን በተግባር ስላንተ ብዙ ይሆናል፣ ከዕረፍቱ በፊት ላንተ ማረፍ ይጨነቃል፤ ባንተ መደሰት ይደሠታል፣ ባንተ መብላት መጠጣት ይረካል፣ ስላንተ እያሰበ ያለ እንቅልፍ ያድራል ፡፡

⇛ትንሽ ያጋነንኩ ይመስላል አይደል!? አይ! አላጋነንኩም። የዚህ ዓይነት ወዳጆችም አሉን ―አልሐምዱ ሊላህ― ለሰው ብቻ የሚኖሩ፣ ስለሰው የሚጨነቁ። አላህ ይጠብቅልን!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

"በቃ ማለት በቃ ነው" ሀሚድ አልታኒ

የኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ በዛሬው እለት በጋዛ ላይ የእስራኤል ጦርነት እንዲያቆም ጥሪ አቅርበዋል "በቂ ነው" ብለዋል።

ሼክ ታሚም የሀገሪቱ የሹራ ምክር ቤት 52ኛ አመታዊ ጉባኤ መክፈቻ ላይ “በቃ እያልን ነው” ሲሉ እስራኤል ውሃ፣ መድሃኒት እና ምግብን እንደ መሳሪያ እንድትጠቀም መፍቀድ የለበትም ሲሉ ተናግረዋል።

“ይህ ከሁሉም ወሰን ያለፈ ጦርነት እና ደም መፋሰስ እንዲቆም እንጠይቃለን። ሰላማዊ ዜጎችን ወታደራዊ ግጭት ከሚያስከትላቸው መዘዞች ይታደጉ፣ ግጭቱም ወደ መባባስ እንዳይሄድ ይከላከሉ” ሲሉ ሼክ ታሚም ተናግረዋል።

#qatarforpalestine

#gaza

{Anadolu Agency}

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ትንቢቱ እየተፈጸመ ነው!

ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 69

አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለው፥ ገዳይም ለምን እንደሚገድል የማያውቅበት፤ ተገዳይም ለምን እንደሚገደል የማያውቅበት ጊዜ በሰዎች ላይ ይመጣል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ لَيَأْتِيَنَّ عَلَى النَّاسِ زَمَانٌ لاَ يَدْرِي الْقَاتِلُ فِي أَىِّ شَىْءٍ قَتَلَ وَلاَ يَدْرِي الْمَقْتُولُ عَلَى أَىِّ شَىْءٍ قُتِلَ ‏"‏

✍ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://t.me/Wahidcom

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group