🏝 አስደናቂው የሰልማን አልፋሪሲ 🏝
የህይወት ታሪክ ክፍል~ሁለት
~~~~~~~~~
📚 በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ
📚 አብደሏህ ኢብኑ አባስ ሰልማን አልፋሪሲ ታሪኩን እንዲህ ሲል ነገረኝ ብሎ ይጀምራል።
💫 እኔ ፋርሳዊ ነኝ አስበሐን ከምትባል የኢራን ከተማ (ጀይ) ተብላ ከምትጠራ መንደር ነዋሪዎች ነበርኩኝ።
👉አባቴም የመንደሯ ትልቅ ሰው ነበር እኔም አባቴ ዘንድ ከሰዎች ሁሉ የተወደድኩኝ ነበርኩኝ።
◉አባቴ እኔን በጣም ከመውደዱ የተነሳ አንድ ነገር እንዳልሆንበት ስለሚፈራ ልክ ልጃ ገረድ የሆኑ ሴቶች ከቤት እንደማይወጡት ሁሉ እኔንም ከቤት እንዳልወጣ አሰረኝ ።
እርሱ እሳትን ያመልክ ስለ ነበር እኔም የአባቴን እምነት በመከተል ያንን እሳት ኣመልክ ነበር።
◉እሳትን በማምለክም በጣም ብዙ ጊዜ ቆይቻለሁ።
◉ያንን የምናመልከውን እሳት እንዳይጠፋ እቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ እጠብቃለሁ። ለአባቴም የእርሻ ስራ የሚያሰራበት ትልቅ የሆነ የእርሻ ስራ ቦታ ነበረው።
◉ሁሌም እየሄደ እርሻውን ይከታተላል።
◉ከእለታት አንድ ቀን ግን አባቴ የሆነ ግንባታን በማስገንባት ወደ እርሻው ቦታ መሄድ ሳይችል በመቅረቱ :-
👉<< ልጄ ሆይ ዛሬ ወደ እርሻው ቦታ እኔ መሄድ ሰላልቻልኩኝ አንተ ሂድና ተመልከት >> አለኝ።
ከሄድኩም በኋላ ምን መስራት እንዳለብኝ ነግሮኝ ወደ እርሻችን ቦታ መሄድ ጀመርኩኝ።
◉በመንገድ ላይ እየሄድኩኝ ሳለሁ የቤተክርስቲያን ድምፅ ሰማሁኝ በሰማሁት ድምፅ በጣም ስለተማረኩኝ ወደ ስፍራው ተጠጋሁ ቦታው ላይ ስደርስ ሰዎች ስግደትን እያከናወኑ ነበር።ነገር ግን እኔ ከቤት ወጥቼ ስለ ማላውቅ ስለ ሰዎች እምነት አላውቅም ነበርና
ወደ ቤተክርስቲያኑም በር ላይ ደርሼ ወደ ውስጥ ገባሁኝ ። ከገባሁ በኋላ በተመለከትኩት ነገር በጣም አድናቆቴ ጨመረ።
◉ስግደታቸውም በጣም አስደሰተኝ ልቤም ወደዚህ እምነት አዘነበለ ወደድኩትም ለራሴም ይህ ሐይማኖት እኔና ቤተሰቦቼ ከምንከተለው ሐይማኖት የተሻለ ነው አልኩኝ
◉ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስም እዚያው ቤተክርስቲያን ውስጥ በመቆየቴ ወደ አባቴ እርሻ ሳልሄድ ቀረው ።
ሰዎቹንም የዚህ ሐይማኖታቹ መነሻው ከየት ነው ብዬ ጠየኳቸው ? እነሱም(ሶሪያ) እንደሆነ ነግረውኝ ወደ አባቴ ቤት ተመለስኩኝ አባቴ ግን ከእርሻው ቦታ ቶሎ ስላልተመለስኩኝ እኔን እያፈላለገኝ ነበርና እቤት ስደርስ ልጄ ምን ሆነህ ነው? አደራ ብዬህ ሳለ ለምንድነው ወደ እርሻው ቦታ ያልሄድከው አለኝ? አባቴ እኔ ወደ እርሻችን ቦታ እየሄድኩኝ ሳለሁ መንገድ ላይ በጣም የሚማርክ ድምፅ ሰማሁኝ በሰማሁት ድምፅ በጣም ተማርኬ ወደ እርሻችን ቦታ ሳልሄድ እስከ አሁን ቆየሁኝ አልኩት ።
👉አባቴም ልጄ ሆይ አሁን አንተ የተመለከትከው ሐይማኖት ላይ ምንም መልካም ነገር የለውም አለኝ።( አባቴ ለሚያመልከው እምነት ወገንተኝነት ይዞት ነበርና )
◉ልጄ አንተ ያለህበት አያት ቅድመ አያቶችህ የነበሩበት እምነት አሁን እዚያ ከተመለከትከው እምነት የተሻለ ነው አለኝ።
👉እኔም <<አባቴ በፍፁም አይሻልም የእነርሱ እምነት ከእኛ እምነት የተሻለ ነው>> ስለው ያን ጊዜ አባቴ ፈራኝና ሁለት እግሮቼን በሰንሰለት አስሮ ከቤት እንዳልወጣ አደረገኝ ።
👉እኔም ወደ ክርስቲያኖች ዘንድ መልዕክተኛን በመላክ << የሶሪያ ነጋዴዎች እናንተ ዘንድ ከመጡ አሳውቁኝ >> አልኳቸው።
◉ከጊዜያት በኋላ የሶሪያ ነጋዴዎች እንደመጡ መልዕክተኛ ልከው ሲነግሩኝ
ነጋዴዎቹ የሚሸጡትን ሸጠው የሚገዙትን ገዝተው ጨርሰው ወደ ሀገራቸው መመለስን ሲፈልጉ አሳውቁኝ አልኳቸው።
◉ነጋዴዎቹም ጨርሰው ሊመለሱ እንደሆነ ባሳወቁኝ ጊዜ እግሮቼ ላይ የታሰረውን የብረት ሰንሰለት አውልቄ በመጣል ከነዚያ ነጋዴዎች ጋር ተገናኝቼ ወደ ሶሪያ ጉዞ ጀመርን።
◉ልክ ሶሪያ እንደደረስን ለነጋዴዎቹ እዚህ ሀገር ላይ በዚህ ሐይማኖት ላይ በላጩ ማነው ብዬ ጠየኳቸው ?
👉እነሱም እዚህ የእምነት ቤት ውሰጥ ያሉት አባት ናቸው አሉኝ።
◉ወደ ተባለውም ሰው በመሄድ አባቴ ሆይ እኔ ይህንን እምነት ወድጄዋለሁ እኔ ከእርሶ ጋር መሆንን እፈልጋለሁ እኔ እዚሁ የእምነት ቤት እርሶንም እያገለገልኩኝ ከእርሶም ሐይማኖቱን ልማር ከእርሶም ጋር ልፀልይ ብዬ ጠየኳቸው? እሳቸውም ፍቃደኝነታቸውን ገልፀውልኝ ገባሁኝ የተወሰኑ ጊዜያቶችንም አብረን ቆየን።
◉ነገር ግን........
በአላህ ፍቃድ ክፍል ሶስት ይቀጥላል።
✏️አቡ ሙጃሂድ አብዱረህማን