mohammed seid Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

mohammed seid shared a
Translation is not possible.

#ቀብር_ስጋን_እና_ስብን_ይበላል ኢማንን ግን አይበላል

Burial eats meat and fat but does not eat Iman

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
mohammed seid shared a
Translation is not possible.

የፍልስጤም ታሪክ

ምዕራፍ -1

የኦቶማን ኢምፓየር ጣዕረ-ሞት

ክፍል-5

[ተፃፈ-በአብዱልከሪም ሙሐመድ @kerimmmo ]

የፅዮናዊያንን ሀገር የመመስረት ሀሳብ የተቃወሙ ብዙ አይሁዳዊያን ነበሩ (ም/ም በእምነታቸው መሰረት ‘መሲሑ’ መጥቶ ነውና ወደ ሀገራቸው የሚመልሳቸው)፡፡ አቅመ ቢሷም ፍትሃዊ አለም ተቃውሞን አሰምታለች፡፡

የሰው መሬት ቀምቶ ሃገር ለመመስረት መጣር መቼም ቢሆን ጤነኛ ሰው ሊቀበለው አይችልምና፡፡

ዞሮ ዞሮ የመጀመሪያው ፍልሰት በመባል የሚታወቀው በ54 አመት ውስጥ (1850-1903) ወደ 50 ሺ የሚሆን ህዝብ ሰፍሯል(በአመት ከ926 ሰው በታች)፡፡ ከ ፅዮናውያን ንቅናቄ ከተጠናከረ በኋላ ማለትም 1904-1910 (በ 7 አመት) ብቻ 20ሺ (2857 ሰው በላይ በአመት) ከዛም በአንደኛው አለም ጦርነት መባቻ ባሉት 4 አመታት ደግሞ 14 ሺ (3500 ሰው በአመት) የሚሆን ህዝብ ተሟል፡፡

ወደ አንደኛው አለም ጦርነት መጀመርያ አካባቢ ኦቶማንን ለመጣል የሚተጋው ሁሉ አቅሙን አጠናክሯል፡፡ ከውስጥ በኩል አረባውያን ደስተኛ አይደሉም ፣ ከባዕዷ እንግሊዝ ጋር ማሴር ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡ ዋና መናገሻው ቱርክ ውስጥ እንኳን ብዙ ፓርቲዎች ተፈጥረው ጥል ውስጥ ሰጥመዋል፡፡

አውሮፓ የተማሩ ወጣቶች ሃገራቸውን እነሱ በተቃኙበት ዜማ (በተለይ ሮል ሞዴላቸው ጀርመን) ለመቀለፅ የጀመሩት የያንግ ተርክስ (ወጣት ቱርካውያን) ንቅናቄ ተፅዕኖ ከማድረግ አልፎ የኢምፓየሩን ቁልፍ ወንበሮች መቆጣጠር ችለዋል (የመከላከያ፣ የውስጥ ጉዳይ እና የባህር ኃይል ሚኒስቴሮች ይገኙበታል)፡፡

በዚህ ላይ ሊያስቆመው ማይችል የአይሁዳዊያን ፍሰት ፍልስጤምን ሊጠራርጋት ይመስላል፡፡ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የረጅም ግዜ ወዳጁ (በሆዷ ነገር ብትበላም) እንግሊዝ መፍረሻ ቀኑን ስታልም ነበርና በግልፅ ጠላትነቷን አወጀች፡፡

ከውድቀቱ በኋላ ግዛቱን እንዴት እንደሚቀራመቱ በዲፕሎማቶቻቸው ካርታ ላይ ካሰመሩ በኋላ የብዙ ግዜ ጠላቶች (ለምሳሌ የናፖሊዮን ዘመቻ ኤከር ላይ) ፈረንሳይም የ አላይድ (የእንግሊዝን) ጎራ ያዘች፡፡

የያንግ ተርክ አባላት በሆኑት ባለስልጣናት በፀደቀ ወዳጅነት ኦቶማን ከ(አክሲስ ጎራ) ጀርመን ጎን መሰለፉ ዘግይቶም ቢሆን መርዶ ተነገረው፡፡

የባልካን ሃገራት ለዘመናት በእጁ ስር ቆይተው የነበሩ ቢሆንም በራሺያው ዛር ስርወ-መንግስት እርዳታ ራሳቸውን ችለው ትናንሽ ሃገራት ሆኑ፡፡ በዚህ እና ራሺያ ራሷን የምስራቁ ኦርቶዶክስ እንባ ጠባቂ ነኝ ብላ ማሰቧ የረጅም ግዜ ጠላት እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

የ ድሮው ቂም ማለትም የኦቶማን ባዛንታይንን ወደ መቃብር መላክ ፣ ዋና ከተማዋን (ኮንስታንቲኖፕልን) ወደ ኢስታንቡል መቀየር ፣ ታላቅ የነበረውን ሀጌ ሶፍያ ቤተ-ክርስቲያን ወደ መስጂድነት በሙሐመድ አልፋቲህ ሁለተኛ ቀጥታ መቀየሩ ሁሉ ለእንባ ጠባቂዋ እያደር የሚመረቅዝ ቁስል ነበር፡፡ በዚህም አላይድ ጎራ ከተሰለፈች ቱርክን እንደምትጠቀልል ቃል ተገባላት፡፡

(በጣም ባጭሩ)

አንደኛው የአለም ጦርነት ተጀመረ ፤ ጀርመን ለአላይዶች የማትበገር ጠንካራ ተዋጊ ነበረች፡፡ ሆኖም እንግሊዝ በአንድም በሌላም መንገድ አሜሪካን ወደ ጎራዋ ስትቀላቅል ሰማዩ ምድር፣ምድሩ ሰማይ ሆነ፡፡ ኦስትሮ-ሃንጋሪም የሶስቱን የበረታ ክንድ መቋቋም አቅቷት በዝረራ ተረታች፡፡

ለቱርካዊያኑ ግን የራሳቸውን ወታደር እንኳን ማሰለፍ አልተጠበቀባቸውም፡፡ በጥቂት እንግሊዛውያን መሪነት አረቦች ራሳቸው እስከ ቱርክ መግቢያ በር ድረስ አባረሯቸው፡፡

ሁሉም የአረብ ሃገራት ከኢስላማዊው መንግስት እጅ ወጡ ፤ ሆኖም ባላሰቡት መንገድ የአውሮፓውያን ቀኝ ግዛት ሆነው አረፉት፡፡ ሙስሊም እና ሙስሊም ተዋግቶ ካፊር አሸነፈ ይልሀል ይህ ነው፡፡

ከዛ በኋላ ቱርኮች በቀኝ ገዢ ላለመያዝ ከ3 አመት በላይ ተዋግተው ቢያሸንፉም፣ የአስተሳሰብ ቀኝ ግዛት ውስጥ ቀድመው ገብተው ስለነበር (አውሮፓዊት ያልሆነች አውሮፓዊት) ዘመናዊዋን አምላክ የለሽ ቱርክ በኮማንደር ሙስጠፋ ከማል በ1923 እውን አደረጉ፡፡

የልብ ትርታችን ፍልስጤም ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች ውስጥ አንዷ ሆነች፡፡

ምዕራፍ ሁለትን ቀጣይ ይጠብቁን!!! ኢንሻአላህ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
mohammed seid shared a
Translation is not possible.

ሰው ከሆንክ ... እና ነፃ ከወጣህ ... እውነቱን ለአለም ከማሳየት ወደ ኋላ አትበል እና "በፍልስጤም ውስጥ ያለውን የእስራኤል ናዚዎችን" በማጋለጥ።

ግብዝ ከሆንክ በጋዛ ሰርጥ ህጻናትን፣ ሴቶችን እና ሲቪሎችን በመግደል ላይ ትሳተፋለህ።

“ድምጻችሁን ከፍ አድርጉ፣ እናም መከላከያ የሌለውን የፍልስጤም ህዝብ እና ህዝቦቿን ለመከላከል ከህዝቡ የወጣውን የፍልስጤም ተቃውሞ ይሟገቱ” ማለት ብቻ ነው።

አክለውም “እስራኤል የፍልስጤምን ምድቀር የሰረቀ አሸባሪ ድርጅት መሆኗን አለም ማወቅ አለበት። እነሱ ሌቦች እና ናዚዎች ናቸው, እና "እስራኤል" የሚባል ነገር የለም.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
mohammed seid shared a
Abdeselam seid Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group