UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
1
Наган дахаан йохтахам.

"በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለች እያንዳንዷ አይሁዳዊት እንስት ቢያንስ አራት ጤናማ ህፃናትን የማትወልድ ከሆነ ፣ የውትድርና አገልግሎትን እንደሸሸ ሰውና ብሔራዊ ክህደትን እንደፈፀመች ይቆጠራል!"

ይህንን ከላይ ያለውን አዋጅ ያወጁት ፡ በአንድ ወቅት የእስራኤል መሪ የነበሩት "ዴቪድ ቤንጎሪዮን ናቸው" ይላል በአሜሪካውያኑ ጋዜጠኞች የተፃፈው "The Israel Lobby" የተሰኘው መፅሐፍ። ይህን አዋጅን እንዲያውጁም ያስገደዳቸው ፡ የፍልስጤማውያን እናቶች ወላዶች ከመሆናቸው የተነሳ የፍልስጤማውያን የህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመምጣቱ ጉዳይ እጅጉን አሳስቧቸው ነው።

አምላክየው ፡ የፍልስጤምን ህዝብ ከምድረ ገፅ ሳይጠፋ እስከዛሬም ድረስ እንዲቆይ ካደረገበት ጥበቡ ውስጥ አንዱ፦ የፍልስጤም እናቶችን ወላዶች በማድረግ ነው። የታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ሞህሰን ፡ "History of Palestine" በተሰኘው መፅሐፋቸው ውስጥ ፡ በ2002 ላይ የነበረውን የፍልስጤማውያንን የወሊድ መጠን ሲገልፁ "አንዲት የጋዛ ፍልስጤማዊት እናት በአማካይ ከ6 ልጆች በላይ ትወልዳለች" ይላሉ። "ይህም ደግሞ በአለም ላይ ትልቁ የወሊድ መጠን ነው" በማለትም ያክላሉ።

የፍልስጤማውያን እናቶች የወሊድ መጠን በዚህ መልኩ ከፍተኛ ባይሆን ኖሮ ፣ በእስራኤል መንግስት ከሚደርስባቸው ጭፍጨፋ አንፃር እስከዛሬ ድረስ ከምድረ ገፅ በጠፉ ነበር። ነገር ግን አምላክየው በመከራ ውስጥ እንዲያልፉ በማድረግ ቢፈትናቸውም ፣ ፈተናቸው በዝቶ ከምደረ ገፅ እስኪያጠፋቸው ድረስ ግን አልተዋቸውም። የፍልስጤማውያን እናቶችን ማህፀን ለምለም በማድረግ ፡ ከሚጨፈጨፉት በላይ የሚወለዱት እንዲበዙ አደረገ።

ለብዙ አስርት አመታቶች ያህል በእስራኤል መንግስት ሲጨፈጨፉ ነበር። ዛሬም እየተጨፈጨፉ ነው። ነገር ግን ዛሬም አሉ ፣ አልጠፉም። በቁጥርም እየበዙ ሄዱ እንጂ አላነሱም!🙏

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

እናት❤..... እናትነት❤.... የእናትነት ስሜት!❤

ሴትን ልጅ ግን ፡ የራሷን ችግር ተቋቁማና ደብቃ ፡ ልጆቿን ለማስደሰት እንድትጥር የሚያደርጋት "የእናትነት ስሜት" ፡ እንዴት ያለ ስሜት ይሆን?!🤔..... ይህንን ሴትነት ውስጥ ያለውን የእናትነት ስሜትን በማስተዋል ይሆን ፡ ጋሽ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር በአንድ ወቅት ላይ "ድጋሚ የመፈጠር እድልን ባገኝ ኖሮ ሴት ሆኜ መፈጠርን እመርጥ ነበር!" በማለት የተናገረው?!🤔.... ጋሼ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር ለእናትና ለእናትነት ያለው ስሜት ይለያል። እናት የልጇን ችግርና ስሜትን ምን ያህል እንደምታውቅና እንደምትረዳ ስለሚያውቅም ይሆናል በአንድ ወቅት ላይ "ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ወንድ ልጅን አሳምራ የምታውቀው እናቱ ናት!" በማለት የተናገረው።

በነገራችን ላይ ፡ ሴትን ልጅ እንዳከብር የሚያደርገኝ ትልቁ ምክንያቴ ፡ ሴትነት ውስጥ እናትነት በመኖሩ ነው። የእናትነት ስሜትን አይደለም እኛ ወንዶቹ ቀርቶ ፡ ሴቶቹ እራሱ እናት ሆነው እስካላዩት ድረስ የሚረዱት አይመስለኝም። የእናትነት ስሜቱን ባልረዳውም ታላቅነቱን ግን እረዳለሁኝ። ብዙ መስዋዕትነትን የሚጠይቅ የተከበረ ማንነት መሆኑንም ጠንቅቄ አውቃለሁኝ።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በአንድ ወቅት ላይ ስለ እናት ክብር ሲናገሩ ፡ "ገነት በእናት እግር ስር ናት" በማለት ዘመን የማይሽረውን ታላቅ ምስክርነትን ሰጥተዋል። በአንድ ወቅትም አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ዘንድ መጥቶ ፡ "ከሰዎች ሁሉ አብልጬ ልቀርበው የሚገባኝ ሰው ማነው?" ብሎ ጠየቃቸው። ነብዩም "እናትህን ነው" በማለት መለሱለት። ሰውየውም "ቀጥሎስ?" አላቸው። አሁንም "እናትህን" አሉት። ሰውየው አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ "ቀጥሎስ?" አላቸው። ነብዩም በድጋሚ "እናትህን" አሉት። ከዚያም በአራተኛው ደረጃ ላይ "አባትህን" በማለት መለሱለት። ሠለላሁ ዓለይሂ ወሰለም። እናትነት በታላቁ ነብይ ዘንድ ፡ ወርቁንም ፣ ብሩንም ሆነ ነሐሱን የሚያሰጥ ታላቅ ማንነት መሆኑ ተመስክሮለታል!❤

#እናትነት

#የተከበረ_ማንነት

#ክብር_ለእናቶች!🙏

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

በየገበያው ቦታ ፡ ሽንኩርት ተራ ፣ በርበሬ ተራ... ወዘተ. እንዳለ ሁሉ ፡ በሁሉም ገበያ ቦታዎች ላይም "መፅሐፍ ተራ" ተብሎ ሰዎች መፅሐፍን እንደ አስቤዛ የሚሸምቱበት ጊዜ ይናፍቀኛል!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

አንድ ቀን ይነጋል። እንደመሸ የሚቀር ለሊት የለም። እንደጠለቀች የምትቀር ፀሐይም የለችም። ለሊቱ ይረዝም እንደሆነ እንጂ መንጋቱ አይቀርም። በጨለማ የተጋረደችው ፀሐይ ፡ ጨለማውን ገፍፋ ብቅ ትላለች። ጨልሞባቸው በተስፋ ማጣት ውስጥ ላደሩት ፍጡራን የተስፋ ብርሃንን ትፈነጥቃለች። በለሊቱ የጨለማ ብርድ ሲሰቃዩ ያነጉትን ፍጡራን በህይወት ሰጪው ሙቀቷ ታነቃለች። ጨለማው እስኪገፈፍ ፣ ብርሃንም እስኪፈነጥቅ ድረስ መሸበርና መንገላታት ይኖሩ ይሆናል። ይህ ግን ለትንሽ ጊዜ ነው። ምክንያቱም ህይወት ጨልማ አትቀርም ፣ ትነጋለች። ፀሐይም ጠልቃ አትቀርም ፣ ትወጣለች!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
መፅሐፈ ያሬድዋን Сhanged his profile picture
7 month
Наган дахаан йохтахам.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group