እናት❤..... እናትነት❤.... የእናትነት ስሜት!❤
ሴትን ልጅ ግን ፡ የራሷን ችግር ተቋቁማና ደብቃ ፡ ልጆቿን ለማስደሰት እንድትጥር የሚያደርጋት "የእናትነት ስሜት" ፡ እንዴት ያለ ስሜት ይሆን?!🤔..... ይህንን ሴትነት ውስጥ ያለውን የእናትነት ስሜትን በማስተዋል ይሆን ፡ ጋሽ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር በአንድ ወቅት ላይ "ድጋሚ የመፈጠር እድልን ባገኝ ኖሮ ሴት ሆኜ መፈጠርን እመርጥ ነበር!" በማለት የተናገረው?!🤔.... ጋሼ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር ለእናትና ለእናትነት ያለው ስሜት ይለያል። እናት የልጇን ችግርና ስሜትን ምን ያህል እንደምታውቅና እንደምትረዳ ስለሚያውቅም ይሆናል በአንድ ወቅት ላይ "ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ወንድ ልጅን አሳምራ የምታውቀው እናቱ ናት!" በማለት የተናገረው።
በነገራችን ላይ ፡ ሴትን ልጅ እንዳከብር የሚያደርገኝ ትልቁ ምክንያቴ ፡ ሴትነት ውስጥ እናትነት በመኖሩ ነው። የእናትነት ስሜትን አይደለም እኛ ወንዶቹ ቀርቶ ፡ ሴቶቹ እራሱ እናት ሆነው እስካላዩት ድረስ የሚረዱት አይመስለኝም። የእናትነት ስሜቱን ባልረዳውም ታላቅነቱን ግን እረዳለሁኝ። ብዙ መስዋዕትነትን የሚጠይቅ የተከበረ ማንነት መሆኑንም ጠንቅቄ አውቃለሁኝ።
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በአንድ ወቅት ላይ ስለ እናት ክብር ሲናገሩ ፡ "ገነት በእናት እግር ስር ናት" በማለት ዘመን የማይሽረውን ታላቅ ምስክርነትን ሰጥተዋል። በአንድ ወቅትም አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ዘንድ መጥቶ ፡ "ከሰዎች ሁሉ አብልጬ ልቀርበው የሚገባኝ ሰው ማነው?" ብሎ ጠየቃቸው። ነብዩም "እናትህን ነው" በማለት መለሱለት። ሰውየውም "ቀጥሎስ?" አላቸው። አሁንም "እናትህን" አሉት። ሰውየው አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ "ቀጥሎስ?" አላቸው። ነብዩም በድጋሚ "እናትህን" አሉት። ከዚያም በአራተኛው ደረጃ ላይ "አባትህን" በማለት መለሱለት። ሠለላሁ ዓለይሂ ወሰለም። እናትነት በታላቁ ነብይ ዘንድ ፡ ወርቁንም ፣ ብሩንም ሆነ ነሐሱን የሚያሰጥ ታላቅ ማንነት መሆኑ ተመስክሮለታል!❤
#እናትነት
#የተከበረ_ማንነት
#ክብር_ለእናቶች!🙏