Translation is not possible.

አንድ ቀን ይነጋል። እንደመሸ የሚቀር ለሊት የለም። እንደጠለቀች የምትቀር ፀሐይም የለችም። ለሊቱ ይረዝም እንደሆነ እንጂ መንጋቱ አይቀርም። በጨለማ የተጋረደችው ፀሐይ ፡ ጨለማውን ገፍፋ ብቅ ትላለች። ጨልሞባቸው በተስፋ ማጣት ውስጥ ላደሩት ፍጡራን የተስፋ ብርሃንን ትፈነጥቃለች። በለሊቱ የጨለማ ብርድ ሲሰቃዩ ያነጉትን ፍጡራን በህይወት ሰጪው ሙቀቷ ታነቃለች። ጨለማው እስኪገፈፍ ፣ ብርሃንም እስኪፈነጥቅ ድረስ መሸበርና መንገላታት ይኖሩ ይሆናል። ይህ ግን ለትንሽ ጊዜ ነው። ምክንያቱም ህይወት ጨልማ አትቀርም ፣ ትነጋለች። ፀሐይም ጠልቃ አትቀርም ፣ ትወጣለች!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group