UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

💪💪💪 እንዲህ ነው አላህ ቁዋው ይጨምርላችሁ

7 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ዓጃኢብ የሆነ ታሪክ

November 26, 2022

አጃዒብ የሆነ ታሪክ ላካፍላችሁ‼

ዲኔ ላይ ደህና ነኝ፡፡ መልክ አለኝ ባይባልም አልከፋም፡፡ በባህሪዬ ጥሩ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡፡ ከቤተሰብ ሳልርቅ ነው ያደግኩት፡፡ የልጅነት ጊዜዬ አልፎ ወጣትነት መጣ፡፡ እንደማንኛዋም ሴት ትዳር አሰብኩ፡፡ ግና በማላውቀው ምክንያት ድርሻዬ ዘገየብኝ፡፡ ለጋብቻ የሚጠይቀኝ ጠፋ፡፡ ከኔ በኋላ የተወለዱ የቤተሰብም፣ የዘመድም፣ የሰፈርም ልጆች አንድ በአንድ አገቡ፡፡ ወለዱ፡፡ ልጆቻቸውም አደጉ፡፡ ሳላስበው 34 ዓመት ሆነኝ፡፡ እድሜዬን ሳስታውሰው ደነገጥኩ፡፡ ብቻዬን ቆሜ የቀረሁ እስኪመስለኝ ድረስ ተሰማኝ፡፡

⊙ የሆነ ጊዜ ከቅርብ ዘመድ የሆነ አንድ ወጣት ለጋብቻ ጠየቀኝ፡፡ ፈቃደኝነቴን ገለፅኩ፡፡ ሁለት ዓመት ይበልጠኛል፡፡ ዲኑም ፀባዩም ቆንጆ ነው፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ከሀሳቤ የተገላገልኩ መሰለኝ፡፡ ቤተሰብም ደስ አለው፡፡

≅ ኒካሕ ለማሰር ተዘጋጀን፡፡ አንዳንድ ጉዳዮችን ለመጨረስ ብሎ መታወቂያዬን ይዞ ሄደ፡፡ 

.

ከሁለት ቀን በኋላ ስልክ ተደወለልኝ፡፡ እናቱ ነበረች፡፡ እንደምትፈልገኝ ነገረችኝ፡፡ ምን ይሆን ብዬ እየበረርኩ ሄደኩኝ፡፡ ቤታቸው ገባሁ፡፡ ጥቂት ካወራን በኋላ መታወቂያዬን እያሳየችኝ እዚህ ላይ የተጠቀሰው የትውልድ ቀኔ ትክክል ስለመሆኑ ጠየቀችኝ፡፡ “አዎን! ትክክል ነው” አልኳት፡፡ 

“እንግዲያውስ አንች አርባ ተጠግተሻል መውለድ አትችይም” አለችኝ፡፡ “34 ዓመቴኮ ነው እንዴት አልችልም” አልኳት፡፡ 

“አይ … አንች ሰላሳ አልፎሻል እኔ ደግሞ ልጅ አይደለም ገና የልጅ ልጅ ማየት እፈልጋለሁ” አለች፡፡ ጋብቻው እንዲሰረዝ ሞገተች፡፡ ልጇንም አሳመነች። ለቤተሰቤ ምን እንደምላቸው እያሰላሰልኩ ተስፋ ቆርጬ ወደቤቴ ተመለስኩ፡፡

≅ ቀናት አለፉ፡፡ ድፍን ስድስት ወራትን በሐዘን አሳለፍኩ፡፡ ረጃጅም ቀንና ሌሊቶችን ስብሰለሰል ከረምኩ፡፡ በር በሩን ባይ እኔን ብሎ የሚመጣ ለኔ የተፃፈ ባል ጠፋ፡፡ ብቸኝነት፣ ባይተዋርነት፣ አጥንት ድረስ ዘልቆ ተሰማኝ፡፡ 

አባቴ ሁኔታዬን ይከታተላል፡፡ ስለኔ አብዝቶ ተጨነቀ፡፡ በመጨረሻም ከወንድሜ ጋር ለዑምራ እንድሄድ መከረኝ፡፡ “ሂጂና በተከበረው የአላህ ቤት አጠገብ ብሶትሽን ተናገሪ፤ የውስጥሽን የውስጥ አዋቂ ለሆነ ጌታ ተንፍሺ” አለኝ፡፡ 

ዑምራ ሄድኩኝ፡፡ የአላህ ቤት ከዕባ ፊት ቁጭ ብዬ ረጅም ዱዓ አደረግኩ፡፡ ለርሱ የውስጥ ስሜቴን ሁሉ አንሾካሸኩ፡፡ አለቀስኩ፤ ፈረጄን ያቀርብልኝ ዘንድ ተማፀንኩት፡፡

≅ የሆነ ቀን ሱንና ከሰገድኩ በኋላ ጥቂት ቁጭ አልኩ፡፡ ከኋላዬ አንዲት ሴት ባማረ ድምጽ ቁርኣንን ታነባለች። “የአላህ ችሮታ ብዙ ነው።” የሚል ትርጉም ያለውን የቁርኣን አንቀጽ ስታነብ ቀልቤ በተለየ መልኩ ወደዚያ ተሳበ፡፡ በቁርኣን ውስጥ የዚህ ዓይነት አንቀፅ ስለመኖሩ ገረመኝ፡፡ አላህ በችሮታው ያስበኝ ዘንድ ተማፀንኩት፡፡ 

ሴትዮዋ አየችኝ፡፡ ምን እንደሆንኩ ጠየቀችኝ፡፡ ሁኔታዬን ነገርኳት፡፡ “አብሽሪ” አለችኝ “አብሽሪ አላህም ያሰብሽውን ይሰጥሻል፤ ኢን ሻኣላህ ደስም ይልሻል” አለችኝ፡፡

≅ ዑምራውን አጠናቅቄ ተመለስኩ፡፡ ድንገት የረጅም ጊዜ ጓደኛዬንና ባሏን በአይሮፕላን ማረፊያው አገኘኋቸው፡፡ የባሏን ጓደኛ ለመቀበል እየጠበቁ ነበር፡፡ ሰላምታ አቅርቤላቸው ትንሽ እንዳወጋን ጓደኛቸው ደረሰና ተሰነባበትን፡፡ ወዲያው አባቴ ደርሶ ተቀበለኝ፡፡

ጥቂት ቀናት አለፉ፡፡ አሁን ከበፊቱ በተሻለ ልቤ በመጠኑ ሰክኗል፡፡ ዱዓዬን አላቋረጥኩም፡፡

የሆነ ቀን ያች ጓደኛዬ ደወለችልኝ ያን ቀን ያየኝ የባሏ ጓደኛ ለትዳር እንዳሰበኝ ነገረችኝ፡፡ በአንድ ቀን እይታ እንዴት ሊሆን ይችላል ብዬ ተገረምኩ፡፡ ግና ለአላህ ምን ይሳነዋል!!፡፡ 

በእውነቱ የማይታሰብ ነገር ሆነብኝ፤ ማመን አቃተኝ፡፡ እሱ ግን የምሩን ነበር፡፡ ስለኔ ሁሉን ነገር ከጓደኛዬ ከሰማ በኋላ አላንገራገረም፡፡ ወደ ቤተሰቦቼ ሽማግሌ ላከ፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ተስፋዬ ለመለመ፡፡ ወዜ ተመለሰ፡፡ ስሜቴ ታደሰ፡፡

በመጨረሻም አገባሁ። ጥሩ አፍቃሪ፣ መልካምና ደጋፊ፣ አዛኝና አሳቢ ባል … አላህ ሰጠኝ። ለኔም ለወላጆቹም ጥሩ ሰው ነበር፡፡

ካገባሁ ቀናት ሄዱ፣ ሁለትና ሶስት ወራት ተተኩ፡፡ ሌላ ሀሳብ አስጨነቀኝ፡፡ የእርግዝና ምልክት ናፈቀኝ፡፡ ግና እስካሁን ምንም አላስተዋልኩም፡፡ ሲበዛ አሳሰበኝ፡፡ እንቅልፍ አጣሁ፡፡

መመርመር እንደምፈልግ ለባሌ ነገርኩት፡፡ ወደ ሀኪም ቤት ሄድን፡፡ ጥቂት ቆይተን ለውጤቱ ተጠራን፡፡ ልቤ መምታቱን ጨመረ፡፡ ገና እንደገባሁ “መዳም መብሩክ!” አለችኝ ሀኪሟ፡፡

አርግዤ ነበር፡፡ ሱብሐነላህ! ለዚህ ብስራት ነበር እንዴ አላህ እዚህ ድረስ ያመጣኝ አልኩ፡፡

የእርግዝና ጊዜዬ ሰላማዊ ነበር፡፡ ግና የእድሜዬ መግፋት መጠነኛ ተጽእኖ ነበረው፡፡ ሆዴ እያደገ ሲመጣ ሰውነቴ ከበደኝ፡፡ እንደምንም የድካሙ ወራት አለፈ፡፡ የምጡ ቀን ደረሰ፡፡ በቀዶ ጥገና ነበር የወለድኩት፡፡ ከተሰጠኝ ሰመመን ስነቃ ቤተሰቦቼና ባለቤቴ ዙርያዬ ተሰብስበዋል፡፡ ይስቃሉ፣ ይጫወታሉ፡፡

“ምን ወለድኩ?” አልኳቸው ያለሁበትን ሁኔታ እያስታወስኩ፡፡

የተመካከሩ ነበር የሚመስለው፡፡ አንድ ላይ ሆነው ነበር ሰርፕራይዝ ያደረጉኝ “ወንድ እና ሴት!” አሉኝ፡፡ መንታ!!፡፡ የኔን መንቃት ሲጠብቅ የነበረው ባሌ በደስታ ተፍነከነከ፡፡ እኔንም ሀሴት የምሆነውን አሳጣኝ፡፡ ብችል ተነስቼ በዘለልኩ፡፡ ቁስሌ ገና እርጥብ ነው፡፡ ሱጁድም ራቀኝ፡፡ በተኛሁበት እንባዬ በሁለቱም ጉንጮቼ በኩል ዝም ብሎ ሲፈስ ይታወቀኛል፡፡ በትኩስ እንባ ፊቴ ታጠበ፡፡ ምስጋናዬን ያወጣሁበት ቃል እሱ ነበር፡፡ 

  የሚለውን የቁርኣን አንቀጽ አስታወስኩ፡፡ ስለ አላህ አሰብኩና በሀሳብ ርቄ ሄድኩ፡፡ የሱ ሥራ አብዝቶ ገረመኝ፡፡ እኛ ተስፋ እንቆርጣለን እንጂ እሱ ያዘጋጀልን ነገር አለ፡፡ እኛው ሁለት ልብ ሆነን ተቸገርን እንጂ በርግጠኝነት በአንድ ሆነን ልብ ይሰጠናል ብለን ብንለምነው ይሰጠናል፡፡ 

እኛው እንቸኩላለን እንጂ እሱ ለሁሉም ነገር መላና መፍትሄ አለው፤ ለሁሉም ነገር ምክንያትና ጊዜ አለው፡፡ ለአላህ ውሳኔ መታገስና ፈረጃውን መጠበቅ ትልቅ ዒባዳ ነው፡፡ 

እንኳን እኛ ነቢዩ ዘከርያም በልጅ እጦት ተፈትነዋል፡፡ “ጌታዬ ሆይ ብቻዬን አትተወኝ!!” ሲሉ ነበር ዱዓ ያደረጉት፡፡ 

ኢን ሻኣላህ ፈጣሪሽ ያሰብሽውን ይሰጥሻል፤ አንቺም አንድ ቀን ደስ ይልሻል፡፡

📚 “ቂሶሱን ሚነል ዋቂዕ” ከተሰኘ መጽሐፍ የተወሰደ፡፡ 

☑️ ተስፋ የቆረጡ ተስፋቸው ይለመልም ዘንድ እባክዎ ሼር ያድርጉ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

2 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

2 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group