አባ ቅጣው ኻሊድ!
~
በፋርስ ኤምፓየር እና በሮማ ኤምፓየር መካከል የተካሄደው ጦርነት 700 ዓመታት ዘልቋል። በዚህ ረጅም ዘመን ውስጥ ከ1000 በላይ ጦርነቶችን አካሂደዋል።
ኻሊድ ብኑል ወሊድ ግን ሁለቱንም ኤምፓየሮች በ4 ዓመታት ብቻ ነበር ያንኮታኮታቸው። ፋርሶችን በ15 ጦርነት ድል አድርጎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኃያልና ገናና ሆኖ ለረጅም ዘመናት የዘለቀውን መንግስታቸውን ሙሉ በሙሉ ከምድረ ገፅ አጠፋው። ለአንድ ሺህ አመታት ምስራቅ ላይ የነገሰውን የሮማ ቁጥጥር በዘጠኝ ጦርነቶች ቋጨው። በተናጠል ቢያቅታቸው ጊዜ የዘመናት ባላንጣዎቹ ፋርስና ሮማ ኻሊድ ብኑል ወሊድን ለመውጋት ህብረት ፈጥረው የፊራድ ጦርነት ላይ ገጥመው ነበር። ያም ሆኖ የዘመኑ ኃያላን ህብረት የኻሊድን ጦር መቋቋም አልቻለም። ይልቁንም ፍፁም በሆነ የበላይነት መራር የሆነ የሽንፈት ጽዋን ነበር ያቀመሳቸው።
እኚህ ናቸው አባቶቼ - አምሳያ ካለህ ዝከር
በሰው ልጅ ረጅም ታሪክ - የማይገኝላቸው ወደር
የፍትህ የጀግንነት - ጫፍ የተቆናጠጡ
ለጨካኞች ተንበርክከው - ፍፁም እጅ የማይሰጡ።
Ibnu Munewor
=