zeyada awel Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

zeyada awel shared a
Qumuqta qilghuchi yo'q.

መነበብ ያለበት በጣም ወሳኝ ርዕስ ለአላህ ብለው በትኩረት ያምብቡት።

        #ዓይን_ቡዳ በማለት የምንጠራው

               (Evil Eye)

               بــســم الــلــه الــرحــمــن الــرحــيمــ

                         الحمد الله رب العالمين

ዓይን የአረብኛ ቃሉ ሲሆን ፤ ትርጉሙ በእይታ (አይንን በመጠቀም) ሰውን መጉዳት ማለት ነው፡፡ በአማርኛ ቡዳ ብለው ይጠሩታል ነገር ግን ዓይን ቡዳ ከሚለው የሰፋ ትርጉም አለው፡፡ ብዙ ግዜ በቅናት ይፈጠራል

በተጨማሪም በአንድ ነገር በጣም በመደነቅ የዓይን በሽታ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ዓይን ከዓይን ከሚያደርገው ሰው ወደ ዓይን ሚደረግበት ሰው ልክ እንደሚተኮስ ቀስት ነው፡፡ቀስት ኢላማ እንደሚመታው እና እንደሚስተው

ሁሉ ዓይንም ሰውየውን ሊያጠቃው ወይም ሊስተው ይችላል፡፡ ዓይን ሚደረግበት ሰው ራሱን በዚክር፣በዱዓ እና በሌሎች ዒባዳ የጠበቀ ከሆነ ዓይን አይጎዳዉም እንደዉም ወደ ዓይን የሚያደርገው ሊመለስ ይችላል፡፡

ራሱን ያልጠበቀ ከሆነ ግን ሊያጠቃው ይችላል፡፡ሙስሊሞች ራሳቸን ዚክር፣ዱዓ እና ሌሎች ዒባዳዎችን በአግባቡ በማከናወን መጠበቅ ይኖርብናል፡ ፡አንድ ሰው ራሱን በዓይን ሊያሳምም ይችላል በራሱ በጣም የሚደንቅ እና የሚገረም ከሆነ ራሱን ሊጎዳ ይችላል፡፡ ይህን ለመከላከል መልካም ነገር ባየን ግዜ" ባረከላህ ፊክ ለወንድ” ፤ “ባረከላህ ፊኪ” ለሴት ወይም “አላሁማ ባሪክ ፊህ” ለወንድ “አላሁማ ባሪክ ፊሀ ለሴት። ለራሱ አንዳች ነገር ከፈራ "ማሻ አላህ ላቁወተ ኢላ ቢላህ" ወይም ባረከላህ ፊየ ሀዛ ይበል፡፡ ይችላል፡፡ ሙሸሪኮች ነብዩን(ﷺ)አላህ በቁርአን ገልፆልናል፡፡ በዓይን ለማጥፋት ሲጥሩ እንደነበር

<< እነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ)ይቀርባሉ፡፡›› አል-ቀለም 51

ነብዩ(ﷺ)ኢብን አባስ ባስተላለፉት እና ሙስሊም፣ አህመድ እና ቲርሚዚይ በዘገቡት ሀዲስ፡-

  ዓይን እውነት ነው፤ ቀደርን የሚቀድመው ነገር ቢኖር ኖሮ ዓይን ይሆን ነበር፡፡ ለዓይን(በአይን ለጎዳችሁት ሰው )እንድትታጠቡ ስትጠየቁ፤ መታጠብ ይኖርባቹሃል፡፡(ሙስሊም)

ከሀዲሱ የምንማረው ዓይን እውነት እንደሆነ እና ዓይን ያደረገው(ጎጂው)መታጠብ ግዴታው መሆኑን እና የታመመው ስው ደግሞ ዓይን ያደረገው ሰው በታጠበበት ሲታጠብ እንደሚፈወስ ከሀዲሱ እንገነዘባለን፡፡ ዓይን ያደረገው የሚታወቅ ከሆነ ፊቱን፣ እጁን፣ ክንዱን፣ ጉልበቱን፣ እግሩን እና ሽርጡንም(ትንሽ የጨርቁን ክፍል)በእቃ ላይ እንዲታጠብ በመጠየቅ ከታመመው ሰው ላይ በማፍሰስ መፈወስ ይቻላል፡፡ ዓይን ያደረገው ሰው መታጠብ ግዴታው ነው፤ በተጠየቀ ግዜ መታጠብ ይኖርበታል፡፡

አይሻ(ረድየላሁ አንሃ)፡-“ዓይን ያደረገው ሰው እንዲታጠብ ይታዘዛል፤ አይን የተደረገበት ሰው ዓይን ያደረገው በታጠበበት ዉሀ ይታጠባል፡፡" አቡ

ዳዉድ ዘግበዉታል

በነብዩ ዘመን የተከሰተውን እንመልከት አቢ ኡማመታ ኢብን ሰህል ኢብን ሀኒፍ እንዲህ ብለዋል፡- ሰህል ኢብን

ሀኒፋ ሲታጠብ አምር ኢብን ራቢእ ተመለከተው እና “ በአላህ ይሁንብኝ እንዲህ የሚያምር ቆዳ አይቼ አላውቅም በልጃ ገረድ ቢሆን እንኳ" አለ ሳህል ኢብን ሀኒፋም ወደቀ፡፡ ወደ ነብዩ ወሰዱት እና “ አንቱ የአላህ

መልእክተኛ ሆይ ለሰህል ኢብን ሀኒፍ አንዳች የሚያደርጉለት ነገር አለን በአላህ ይሁንብን ራሱን እንኳ አያነሳም አሉ” ነብዩም “የምትጠረጥሩት

ሰው አለ እንዴ?" በማለት ጠየቁ እነሱም “አምር ኢብን ራቢእን ነው የምንጠረጥረው በማለት መለሱ ነብዩም(ﷺ)አምር ኢብን ራቢእን ጠሩት እና አከበዱበት " አንዳችሁ ለምን ወንድሙን ይገድላልን? (ጥሩ ነገር በተመለከታችሁ ግዜ አላህ)ኢንዲባርክለት ዱዓ አታደርግለትምን አሉ በመቀጠልም አምር ኢብን ራቢእ እንዲታጠብ አዘዙት እሱም ፊቱን፣ እጁን፣ ክንዱን፣ ጉልበቱን፣እግሩን እና ሽርጡንም(ትንሽ የጨርቁን ክፍል) በዉሀ መያዣ እቃ ላይ ታጠበ፡፡የታጠበበት ዉሃ በሳህል ኢብን ሀኒፋ ላይ አፈሰሱት ሳህል ኢብን ሀኒፋም ምንም እንዳልሆነ ሰው ተነስቶ፤ ከሰዎች ጋርም ተቀላቀለ፡፡ “ኢማሙ ማሊክ ዘግበዉታል በሌላ ዘገባ ደግሞ ነብዩ(ﷺ)አምር ኢብን ረቢዕን ዉዱእ እንድያደርግ አዘዙት የሚል አለ አሁንም በሌላ ዘገባ በሳህል ኢብን ሀኒፍ በራሱ እና በጀርባው ላይም አፈሰሱበት የሚል አለ፡፡ ሩቅያ እና መታጠብ ለዓይን ፈውስ ናቸው፡፡ ከተቻለ ዓይን አድራጊው በእቃ ላይ ፊቱን እንዲታጠብ ፣ እንዲጉመጠመጥ በተጨማሪም እጁን ፣እግሮቹን እና ጉልበቱን እንዲታጠብ፤ ሽርጡንም(ትንሽ የጨርቁን ክፍል)እንዲያጥብ ይደረጋል ከዚያም ዉሀው በታማሚው ላይ ያፈሰሳል፡፡ ዓይን ያደረገበት ሰው ካልታወቀ ታማሚዉ በሩቅያ ይታከማል፡፡

    

https://ummalife.com/Meryemhassen

Meryem hassen Hadra | UmmaLife

Meryem hassen Hadra | UmmaLife

Send as a message
Share on my page
Share in the group
zeyada awel shared a
Qumuqta qilghuchi yo'q.

ሙዓዊያ እና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁማ በተጋጩ ግዜ ሁለት

ኢስላማዊ ስረወ መንግስት ተመሰረተ የሮሙ ንጉስ ይህን ሰምቶ

እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈ።

<<ከሮም ንጉሰ ነገስት ለ ሙስሊሞች መሪ ሙዐዊያ አቡ ሱፍያን!!

ባንተ እና በዐሊይ መካከል የተከሰተውን ግጭት

ሰምተናል።ስለዚህም ለሙስሊሞች መሪ አንተ መሆን

እንዳለብህም ስለምናምን አንተ ፍቃድህ ከሆነ የዐሊይን ጭንቅላት

ቀንጥሶ የሚያመጣልህን ወታደር ልላክልህ>>

ይህ ደብዳቤ ሙዐዊያ ጋር እንደደረሰም ሙዓዊያም

<<ከሙዓዊያ ለሮም መሪ!!! ሁለት ወንድማማቾች ስለተጣሉ

አንተ ምን አገባህ? አፍህን የማትዘጋ ከሆነ ጅማሬው እኔ ጋ የሆነ

እና ፍፃሜው አንተ ጋ የሆነ ሰራዊት ልኬ አንገትህን በማስቀንጠስ

ለዐሊይ በስጦታ መልኩ አበረክትለታለሁ>>

#ይህ_ትክክለኛ_ሙስሊሞች_ሳለን_ነው

_____

___

ካሊድ ኢብን ወሊድ ለፐርሺያው ንጉሰ ነገስት እንዲህ ሲል

ደብዳቤ ፃፈለት

<<ስለም ትድናለህ። እንቢ ያልክ እንደሆን ግን፤ እናንተ ህይወትን

የምትወዱትን ያህል ሞትን የሚወዱ ሰራዊቶችን ይዤልህ

እመጣለሁ።>>

ንጉሱ ይህን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የቻይናውን ንጉስ የጦር እርዳታ

ሊለምነው ደብዳቤ ፃፈለት።

የቻይናውም ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ መልሶ ላከለት።

<<ንጉስ ሆይ! ተራራን እንኳን ለመናድ ካሰቡ ምንም

ከማያግዳቸው ወታደሮች ጋር ለመጋፈጥ አቅሙ ስለሌለኝ

ጥያቄህን መፈፀም አልችልም።>>

# ምን_ያህል_ሀያላን_እንደነበርን_ተመልከቱ

_____

____

በደውለቱል ዑስማኒያ የአገዛዝ ዘመን የሙስሊም ወታደሮች የጦር

መርከቦቻቸውን ይዘው በአውሮፓ ደሴቶች ሲያልፉ በአከባቢው ያሉ

አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ሙስሊሞች መጥተው ፈትህ

እንዳያደርጉ በመፍራት ከበሮ ከመምታት እና ምንም አይነት ድምፅ

ከማሰማት ይቆጠቡ ነበር።

#ያኔ_ጀግና_ሳለን

_____

____

በደውለቱል ኡስማኒያ የአገዛዝ ዘመን በያንዳንዴ ቤት ደጅ ላይ

ሁለት የበር ማንኳኩያዎች ይኖራሉ። አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ትንሽ

ነው። በትልቀኛው ከተንኳኳ አንኳኪው ወንድ ነው'ና በሩን ሊከፍት

ሚመጣው ወንድ ይሆናል። ነገር ግን በትንሸኛዋ ከተንኳኳ

አንኳኪዋ ሴት መሆኗ ስለሚታወቅ ሴት ትከፍትላታለች።

በዚያ ምርጥ ዘመን አንድ ቤት ውስጥ ሰው ከታመመ ደጅ ላይ

ቀይ አበባ ይንጠለጠል ነበር። ያን አበባ የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ

እዝያ ቤት በሽተኛ መኖሩን ስለሚያውቁ በበሩ ሲያልፉ ድምፃቸውን

ዝቅ ያደርጉ ነበር።

#ሹፍ_ምን_እንመስል_እንደነበር !!!

_____

_

ግዜው ሰላሁዱን አል አዩቢ በይተል መቅዲስን ባስመለሰበት ግዜ

ነበር። እና ጦርነቱ ነገውን ሊጀመር ማታ ላይ የጦር መሪው

ሰላሁዲን የወታደሮቹን ድንኳን እየዞረ ሲያዳምጥ፤ ግማሹ ለይል

ይሰግዳል፣ ሌላው ቁርአን ይቀራል፣ የተቀሩት ደግሞ ይዘክራሉ።

ግን ድንገት በሆነ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ በድንኳኑ ውስጥ ያሉት

ሁሉም ተኝተው ነበር። ይህን ግዜ፦"በዚህች ድንኳን አዳሪዎች

ምክንያት ልንሸነፍ እንችላለን" ብሎ አለፈ።

#ማንተኛበት_ዘመን

_____

___

ቀደምት ዑለማኦች በሶስት ነገራት አደራ ይባባሉ ነበር።

1፦ሰውዬው በሱ እና በአላህ መካከል ያለውን ግንኙነት ካሳመረ፤

በሱ እና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ያምርለታል።

2፦ሰውዬው ሚስጥራዊ ተግባሩን ካሳመረ አላህ ይፋዊ ተግባሩን

ያሳምርለታል።

3፦ሰውዬው የአኪራው ጉዳይ ካስጨነቀው አላህ የዱንያውንም

የአኪራውንም ጉዳይ ያግራራለታል።

_____

_

#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው

ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ

ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።

በእለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ ቁርአንን መቅራት ካልተካተተ ትልቅ

ኪሳራ ነው።

ይህን ፅሁፍ በማሰራጨት ጓደኛህን እንድታነቃው ይከጀላል!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Qumuqta qilghuchi yo'q.

image
1 view
Send as a message
Share on my page
Share in the group
zeyada awel shared a
Qumuqta qilghuchi yo'q.

✏️የነቢያችን_ሰለሏሁ_ዐለይሂ_ወሰለም_የአመጋገብ_ሱና

✏️➊➭ ነቢያችን ከምግብ በፊት ይታጠቡ ነበር። የሚበሉትም ከፊታቸው ነበር

✏️➋➭ ነቢያችን ተደግፈው በልተው አያውቁም። ለምግብ ሲቀመጡ ወይ ተሸሁድ ላይ አይነት፣ ወይም እንዲሁ ተቀምጠው አንድ እግራቸውን ጉልበት ደረታቸው ላይ በማቀፍ ወይ ደግሞ ቁጢጥ በማለት ነበር።

✏️➌➭ ነቢዩ ምግብ ሲጀምሩ ቢስሚላህ በማለት ነው።

✏️➍ ➭ነቢያችን ምግቡን ካልወደዱት ስለምግቡ ምንም ሳይናገሩ መመገብ ይተው ነበር።

✏️➭ የማያውቁት ምግብ ከገጠማቸው አስቀድመው ስለምግቡ ይጠይቁ ነበር።

✏️➏ ➭ነቢያችን ምግባቸውን አሽትተው አያውቁም። ጥሩ ያለሆነ ልምድ እንደሆነም ይቆጥሩታል።

✏️➐ ➭በጣም የሞቀ ምግብ አይመገቡም ያቀዘቅዙት ነበር። «አላሁ ተዐላ እሳት አይመግበንም» ይሉ ነበር። በጣም የሞቀ ምግብ ውስጥ በረካ የለውም ብለዋል።

✏️➑➭ ነበዩ ምግብም ሆነ መጠጥ ላይ ተንፍሰው አያውቁም። መጠጥን በትንፋሽ ማቀዝቀዝ አይወዱም ነበር።

✏️➒ ➭ነቢዩ ሀብታሞች ቤት እንደሚሆነው በብዙ ሳህን የሚቀርብ ምግብ አይወዱም ነበር።

✏️➓ ➭በአብዛኛው ነቢዩ ሲመገቡ በሶስት ጣታቸው (አውራ፣ ጠቋሚና መሐል ጣታቸውን) በመጠቀም ሲሆን ምግቡ ቀጠን ያለ ከሆነ ቀለበት ጣታቸውን ይጨምሩ ነበር።

✏️➊➊➭ አንድ አይነት ምግብ ከቀረበላቸው ከፊታቸው ይመገባሉ የተለያየ አይነት ከሆነ ግን ከሌላ ቦታ ከመመገብ አይቆጠቡም ነበር።

✏️➊➋ ➭ነቢዩ ከሰው ጋር እየበሉ ከሆነ የሚነሱት በመጨረሻ ነበር። ቀስ ብለው የሚመገቡ ሰዎችን ላለማሳፈር።

✏️➊➌➭ ሲጨርሱ ጣታጫውን በአፋቸው ያፀዱ ነበር።

✏️➊➍➭ ነቢዩ ተመግበው ሲጨርሱ እንዲህ ይሉ ነበር «የምንበላውና የምንጠጣውን የሰጠኸን፣ ሙስሊምም ያደረግኸን አምላክ ምስጋና ይገባህ!» ይሉ ነበር።

✏️➊➎➭ ነቢዩ ምግብ ለተሰባሰቡ ሰዎች የሚያከፋፍሉ ከሆነ በቀኝ ይጀምሩ ነበር። በግራ መጀመር ከፈለጉ በቀኝ ያለውን ያስፈቅዱ ነበር።

✏️➊➏ ➭ነቢያችን ስጋ ወደ ቤት ሲያመጡ ለጎረቤት እንዲበቃ ተደርጎ እንዲሰራ ያደርጉ ነበር።

✏️➊➐➭ ነቢዩ ሀለዋ፣ ማር፣ ኮምጣቴ፣ ተምር፣ ሀብሀብ፣ ኪያር እና ዝኩኒ ይወዱ ነበር።

Send as a message
Share on my page
Share in the group