UMMA TOKEN INVESTOR

About me

I'm Engineer

Translation is not possible.

እነሱ ይጠራሉ ይገዳደፋሉ‼ ሙስሊም ሀገራት ግን ንፁሀን ህፃናትና ሴት በግፍ እያለቁ ዝምታን መርጠዋል። ጭራሽ ሀማስን ለማውገዝ ይገዳደራሉ እስኪ ዛሬ የወጣውን ዘገባ አንብቡልኝማ።👇

"አሜሪካ በርካታ ዓይነት  ያለው የጦር መሳሪያና ጥይት ለእስራኤል መላኳ ተሰምቷል‼️

የእስራኤል የመከላከያ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ መንግስት በአርባ አምስት የእቃ መጫኛ አውሮፕላኖች የጫናቸውን የጦር መሳሪያና ጥይት መቀበሉን አስታውቋል፡፡

የጦር መሳሪያና ጥይት የጫነውን አርባ አምስተኛ ግዙፍ አውሮፕላን በሀገሪቱ ምድር መድረሱ የተነገረ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ ለእስራኤል የህክምና ቁሳቁስና አምቡላንሶችን የጫኑ ግዙፍ አውሮፕላኗን መላኳን እስራኤል አስታውቃለች፡፡

የተላኩት የጦር ቁሳቁሶች የእስራኤልን የጦር ሀይል በከፍተኛ ደረጃ የሚገነቡ መሆናቸውን ዲፌንስ ፖስት ዘገባ ያስረዳል ሲል አሐዱ ራድዮ ነው ያስነበበው።"

https://t.me/SuZi_Tube

Telegram: Contact @SuZi_Tube

Telegram: Contact @SuZi_Tube

You can view and join @SuZi_Tube right away.
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የጡፋን አል አቅሳ አብዮት ጠንሳሽ የቀሳም ሙ*ጃ*ሂ*ድ ትንታግ፣ ከሞሳድ የተሸሸገ፣ ማንነቱ ከሁሉም የተደበቀ፣ የወራሪዋ ቁጥር አንድ ጠላት ገደልነው ሲሉ ብቅ አጠፋነው ሲሉ የሚከሰት ባለጥላው የጦር መሪ "የማይሞተው ሰይጣን" ብለው ስለሰየሙት ሙሐመድ ደይፍ የፍ#ልስ#ጤሙ ትንታግ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

𝓐𝓫𝓭𝓮𝓵𝓪𝔃𝓲𝔃 𝓑𝓲𝓷𝓜𝓾𝓱𝓪𝓶𝓶𝓮𝓭:

*የፍልስጤም እና እስራኤል ግጭት መቸ እና እንዴትጀመረ???***

ታሪካዊ ዳራ--------ክፍል①

____

✍ጥንቅር:©ዐብደልዐዚዝ ቢን ሙሐመድ

ግንቦት13/2013

©©©©©©©©©©©©

ፍልስጤም በመካከለኛው ምስራቅ ጥንታዊ እና ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ የጎላ ሚና የተጫወተች የምድር ክልል ናት ፡፡  የፍልስጤም ምድር ለበርካታ ዋና ዋና የዓለም ሃይማኖቶች መነሻ ነው።

ፍልስጤም የሚለው ቃል የተወሰደው"philistia" ከሚለው የግሪክ ቃል መሆኑን በ12ኛው መቶ ክፍለዘመን(B.C) የነበሩ የጥንታዊ የግሪክ ጸሐፊዎች በመፅሀፍቶቻቸው አስፍረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፍልስጤም በአፍሪካ እና በእስያ መካከል ጠቃሚ በሆነ የጂኦግራፊያዊ መስቀለኛ መንገድ ላይ በመቀመጡ በተደጋጋሚ የፖለቲካ ግጭቶች እና የኃይል ሚዛን መለዋወጥ የታየበት ነው ፡፡

በዚህ የግዛት ክልል የሚገኙ የአረብ ሰዎች "ፍልስጤማውያን" በመባል የሚታወቁ ሲሆን የፍልስጤም ህዝብ በዚህ በጅኦግራፊያዊ አቀማመጡ እና በታሪካዊነቱ ፉክክር የበዛበት የአለም ክልል ውስጥ ነፃ እና ገለልተኛ መንግስት ለመፍጠር ከፍተኛ የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

በአንደኛው የዓለም ጦርነት የኦቶማን መንግሥት ከወደቀበት ጊዜ አንስቶ እስከ 1948 ድረስ ፍልስጤም በተለምዶ በሜዲትራንያን ባሕር እና በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል የሚገኘውን  ጂኦግራፊያዊ ክልል በመወከል ትጠቀሳለች፡፡

በዚህም መሰረት ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ በዚህ ጅኦግራፊያዊ ክልል የሚኖሩ ሰዎች ፍልስጤማውያን መሆናቸውን አብዛኛው የዓለም ህዝብ  ይቀበላል፣ያምናልም ፡፡  አብዛኛው የዚህች ምድር በአሁኑ ጊዜ በእስራኤል ቁጥጥር ስር ሁኗል፡፡

ዛሬ ፍልስጤም "በንድፈ ሀሳብ" የዌስት ባንክን (በዘመናዊቷ እስራኤል እና ዮርዳኖስ መካከል የተቀመጠች ክልል) እና የጋዛ ሰርጥ (የዛሬይቱን እስራኤል እና ግብፅን የሚያዋስን ክልል)ያካትታል።ሆኖም ፣ ይህንን ክልል መቆጣጠር ውስብስብ እና ተለዋዋጭ ሁኔታ ነው ፡፡  ድንበሮችን በተመለከተ ዓለም አቀፍ መግባባት የሌለ ሲሆን በፍልስጤማውያን ይገባኛል የሚሉ ብዙ አካባቢዎች በእስራኤላውያን ለዓመታት ተይዘዋል ፡፡

ከ135 በላይ የተባበሩት መንግስታት አባል አገራት ፍልስጤምን እንደ ገለልተኛ ሀገር እውቅና ይሰጣሉ።እስራኤል እና አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች አንዳንድ ሀገሮች ግን ይህንን ሃቅ መቀበል አይፈልጉም፡፡

የፍልስጤም ቀደምትአስተዳደር ምንይመስልነበር?

የጥንታዊ ግሪክ ፀሀፊዎችን ጨምሮ ሌሎችም የታሪክ ምሁራን “ፍልስጤም” የሚለው ስም በመጀመሪያ “philistia” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ነው ብለው የሚያምኑ መሆናቸውን አይተናል።ይህም በ12ኛው ክፍለ ዘመን(B.C)አካባቢ የክልሉን የተወሰነ ክፍል የያዙ ፍልስጤማውያንን የሚያመለክት ነው ፡፡

በተለያዩ የታሪክ ዘመናት ፍልስጤም በኢስያውያን፣በባቢሎናውያን ፣ በፐርሺያ፣በግሪክ ፣ በሮማውያን ፣ በአረቦች ፣ በፋጢሚዶች ፣ በሳልጁክ ቱርኮች ፣ በመስቀል ጦረኞች ፣ በግብፃውያን እና ማሙልኮችን ጨምሮ በበርካታ ቡድኖች ትተዳደር ነበር ፡፡

ከ1517 እስከ 1917 ገደማ ድረስ የኦቶማን ኢምፓየር አብዛኛውን የዚህ አካባቢው ይገዛ ነበር ፡፡

ከአንደኛው የዓለም ጦርነት(1914)በፊት መካከለኛው ምስራቅን ጨምሮ የሰሜን አፍሪካን፣የደቡብ ምስራቅ አውሮፓ ሃገሮችን እና የምእራብ ኤሲያ ሃገራትን ያስተዳድር የነበረው የኦቶማን ቱርክ መንግስት፣በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከጀርመን፣አውስትሪያ ሃንጋሪ እና ቡልጋሪያ ጋር በመሆን ማእከላዊ ሃይሎች(Central powers)የሚል የጦር ግንባር በመመስረት ከብርታንያ፣ፈረንሳይ፣ሩሲያ፣ኢጣሊያ እና U.S.A ሃይሎች(Allied powers)ጋር በሀምሌ18,1914 የለየለት የጦርነት ፍልሚያ ገቡ።

ከ4አመት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱበት እልህ አስጨራሽ አስከፊ የጦርነት ፍልሚያ በሗላ የሃይል ሚዛኑ ወደ Allied Powers ስላዘነበለ፣እነ ኦቶማን ቱርክ እና ጀርመን ያሉበት ማእከላዊ ሃይል የሽንፈት ካባውን ሲከናነብ፣የሽንፈቱ ገፈታ ቀማሽ የሆነው የኦቶማን ኢምፓየርም ፍልስጤምን ጨምሮ በርካታ ግዛቶቹን በእነ እንግሊዝ በሃይል ተነጠቀ።

ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ፍፃሜ( November 11, 1918) በሗላ January10,1920 የተቋቋመው የመንግስታቱ ማህበር(League of Nations)ብሪታንያ ፍልስጤም በምትገኝበት የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ላይ አስተዳደራዊ ስልጣን እንዲሰጣት የሚያደርግ ሰነድ ያፀደቀ ሲሆን፣ይህም ሰነድ ፍልስጤም ውስጥ የአይሁድ መንግስት(አስተዳደር)ለማቋቋም የሚያስችሏቸውን ድንጋጌዎች ያካተተ ነበር።

በመሆኑም ይህ የብርታንያ በፍልስጤም

ላይ በሞግዚት አስተዳደርነት መሾም፣እነዚያን በተለያዩ የአውሮፓ ሃገሮች ተበታትነው ይኖሩ የነበሩ እርኩስ አይሁዶች ወደ ፍልስጤም ምድር አምጥቶ የተከላቸው አጋጣሚ መሆኑን ስለመካከለኛው ምስራቅ ታሪክ የሚያጠኑ ምሁራን በሙሉ ድምፅ ይስማማሉ።

(ክፍል②ይቀጥላል………

*የፍልስጤም እና ኢስራኤል ግጭት መቸ እና እንደት ጀመረ?

ታሪካዊ ዳራ____ክፍል②

*አይሁዶች በፍልስጤም ምድር መንግስት ለመመስረት ያደረጓቸው እንቅስቃሴዎች እና በሂደቱ የተከሰቱ አበይት ክስተቶች!!*

__

ዘመናዊው የእስራኤል መንግስት እ.ኤ.አ. ግንቦት 1948 ከናዚ ጀርመን የአይሁዶች ጭፍጨፋ እና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ቢመሰረትም፣ በእስራኤላውያን እና በፍልስጤማውያን መካከል የተጀመረው ግጭት ግን ከዚህ በጣም ብዙ አመታትን ወደሗላ ይመለሳል።በፈረንሣይ አብዮት ወቅት(1789-1799) ታዋቂነትን ያተረፈው እና በአብዮታዊ ጦርነቶች ወቅት በርካታ ስኬታማ ዘመቻዎችን በመምራት እ.ኤ.አ. ከ1799 እስከ 1804 የፈረንሳይ ሪፐብሊክ መሪ የነበረው

ናፖሊዮን ቦናፓርት፣ከኦቶማን ኢምፓየር ጋር በነበረው ጦርነት ወቅት(እ .ኤ.አ.በ 1799)ፍልስጤም ውስጥ አንድ የአይሁድ መንግስት እንድመሰረት  የሚል ሐሳብ አቀረበ ፡፡

በዚህ የናፖሊዮን ከኦቶማን ቱርክ ጋር በተደረገ ጦርነት የፈረንሳይ ጦር በመጨረሻ በዚያ ግንባር ድል ቢደረግም፣ነገር ግን በመካከለኛው ምስራቅ ጠንካራ የአውሮፓ ምሽግን ለማቋቋም ያደረገው ሙከራ ከ 41 አመታት በሗላ በእንግሊዝ ተግባራዊ ተደረገ።

የውጭ ጉዳይ ጸሐፊው ሎርድ ፓልመርተን ወደ ኢስታንቡል ለአምባሳደራቸው በጻፉት ደብዳቤ፣የግብፅ መሪ የነበረው ሙሐመድ ዓሊ በአካባቢው እየጨመረ የመጣውን ተፅእኖ ለመቃወም በሚል የማሳመኛ ምክናየት፣የቱርክ ሱልጣን ፍልስጤምን ለአይሁድ ስደተኞች ክፍት እንድያደርግ በዚያ(በኢስታንቡል)የሚገኘው የእንግሊዝ አምባሳደር ከፍተኛ ግፊት እንዲያደርግ አሳሰበ።

በዚያን ጊዜ በፍልስጤም የሚኖሩት ወደ 3,000 የሚጠጉ አይሁዶች ብቻ የነበሩ ቢሆንም፣እንደ ፈረንሳዊው አርበኛ ባሮን ኤድመንድ ዴ ሮዝቻል ያሉ ባለሀብቶች ሌሎች አይሁዶችን በመልቀም ፍልስጤም ውስጥ ከሚገኙት አይሁዶች ጋር ለመቀላቀል ስፖንሰር ማድረግ ጀመሩ።

በዚህም መሰረት በ1882 በፍልስጤም የአይሁድ ፈላሲያን ዋና መናኸሪያ የሆነችው"Rishon Lezion"(ሪዞን ለፅዮናዊያን)የተባለች ከተማ ተመሰረተች።

(በአሁኑ ግዜ "ሪዞን ሌዝዮን"ከቴል አቪቭ በስተደቡብ 8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ማዕከላዊ የእስራኤል የባሕር ዳርቻ ሜዳ ላይ ትገኛለች።)

ሜይ 16,1864 በ ቬይና አውስትሪያ ተወልዶ በ April .2,1937 በኔዘርላንድ የሞተው የኦስትሪያው ጸሐፊ ናታን በርንባም በ1885 "Zionism(ፅዮናዊነት"የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ግዜ ተጠቀመ።

(Full defination of Zionism:

an international movement originally for the establishment of a Jewish national or religious community in Palestine and later for the support of modern Israel(በፍልስጤም ውስጥ የአይሁድ ብሄራዊ ወይም የሃይማኖት ማህበረሰብ ለመመስረት እና ቆይቶም ዘመናዊ እስራኤልን ለመደገፍ ዓለም አቀፍ ንቅናቄ)Source:Merriam-Webster Dictionary.

ይህ ከሆነ ከ10 አመት ገደማ በሗላ ማለትም በ1897 የኦስትሮ-ሃንጋሪ አይሁድ ጋዜጠኛ ቴወዶር ሄርዝል"DerJudenstaat(የአይሁድ መንግስት)"የተሰኘ መፅሃፍ በማሳተም የአይሁዶችን ወደ ፍልስጤም ምድር በመፍለስ የራሳቸውን መንግስት ለመመስረት ያላቸውን ተስፋ ይበልጥ አበረታታ፣አስተዋወቀም።

የእቅዱን(የተስፋውን)አዋጭነት ለመመርመር ሁለት የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች በሄርዝል ጓደኛ ማክስ ኖርዱ አማካኝነት ወደ ፍልስጤም ተልከውም ነበር።እነርሱም በዚያ የታዘቡትን ሁኔታ በምሳሌያዊ አነጋገር"The bride is beautiful but she is married to an other man!(ሙሽራይቱ ቆንጆ ናት ግን ከሌላ ወንድ ጋር ተጋብታለች!)በማለት ሪፖርት አቀረቡ።

የዚህ የአይሁዶች በፍልስጤም ምድር መንግስት የመመስረት ፅንሰ ሃሳብ እና እንቅስቃሴ(Ideology&Movement) ወይንም በአጭሩ"ፅዮናዊነት(Zionism) አራማጅ የሆኑት ናዛን በርንባም፣ቴዎዶር ሄርዝል እና ጓደኛው ኖርዱ ፣ተስፋ ሳይቆርጡ በ1897 በ ባዝል ስዊዘርላንድ የመጀመሪያውን የጽዮናውያን ኮንግረስ አደራጅተው ነፃ የአይሁድ ብሄረሰብ የመሆን ህልማቸው ላይ ለመወያየት እና የአውሮፓ መንግስታትን ድጋፍ ማግኘት ስለሚችሉበት ሁኔታ መከሩ፣ተመካከሩም።

ብሪታንያ እ.ኤ.አ. በ 1907 በመካከለኛው ምስራቅ የበላይነቷን ለማጎልበት ሰፊ ግዛት እንደሚያስፈልጋት በጥልቀት እያሰበች፣እያወጣች እያወረደች ነበር፡፡

የብሪታንያ ጽዮናዊ እንቅስቃሴ መሪ የነበረው ባዮኬሚስትሪ ተመራማሪ ቻይም ዌዝማን በጃፋ አቅራቢያ(ጃፋ ከቴልአቪቭ በስተደቡብ በኩል የምትገኝ ጥንታዊ ከተማ ናት)መሬት በመግዛት ላይ የሚሰማራ ኩባንያ ለማቋቋም ወደ ኢየሩሳሌምን ለመጀመሪያ ግዜ ጎበኘ። በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በሰሜን ፍልስጤም ማርጅ ቢን አመር ክልል 10,000 ዱኑምስ መሬት በመግዛት 60,000 የሚሆኑ የአካባቢው አርሶ አደሮችን ከአውሮፓ እና ከየመን የሚመጡ የአይሁድ ፈላሾችን ተቀብለው እንድያስተናግዱ አስገደደ።

(ዱኑምስ/dunums ማለት ከኤከር/acres ጋር የሚመሳሰል ጥንታዊ የመሬት ስፋት መለኪያ ነው።

ኤከር/acres ማለት ደግሞ 4,000 ስኩዌር አካባቢ የሚሆን የመሬት ስፋት መለኪያ ነው።)

ቀጥሎም በፍልስጤም ምድር ከግዜ ወደግዜ ቁጥራቸው እየበዛ የሄዱ የአይሁድ ፈላሽያን የሰፈራ መንደሮች ለመጠበቅ ሀሾመር የተባለ የአይሁድ የሚሊሻ ቡድን ተቋቋመ።

ይሄኔ ነበር እውቁ ፍልስጤማዊ ፋርማሲስት፣ጋዜጠኛ እና ምሁር #ናጂብ _ናስር የቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ ነው ብሎ ከፈረጀው የአይሁዶች ህገወጥ ወረራ ለማስጠንቀቅ #አልካርመል\" የተባለ ጋዜጣ ያቋቋመው።

ናጂብ ናስር የተወለደው #አይን_አይኑብ ተብሎ በሚጠራው የሊባኖስ ተራራማ መንደር እ.ኤ.አ. ጥር1 ቀን፣1865 ሲሆን ወደ አኼራ የሄደው/የሞተው ደግሞ ታህሳስ 28 ቀን፣1947 ነው።

ናጅብ ትምህርቱን የተከታተለው በሊባኖስ ሲሆን፣በ19ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ አካባቢ ቤተሰቦቹ የትውልድ መንደሩን ለቀው ወጡ።

ናጅብ በሃይፋ የአል-ካርሚል ጋዜጣ መስራች ሲሆን በ1908 ተጀምሮ በናስር መሪነት ወረቀቱ የጽዮናዊያንን እንቅስቃሴ በመቃወም በ1911 የመጀመሪያውን መጽሐፍ በአረብኛ ማሳተም ችሏል።

የአንደኛው የዓለም ጦርነት መከሰት ብሪታንያ በፍልስጤም ውስጥ የተባበረ ሃይል(allied powers)ለመፍጠር የነበራት ፍላጎት በሙስሊሞች ላይ እምነት እንዳትጥል ያደረጋት ሲሆን፣ይህም በስዊዝ ካናል ላይ ያላትን የበላይነት ለማጠናከርም ጭምር ነበር።

እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 1915 የእንግሊዝ ሊበራል ፓርቲ የምክርቤት እንደራሴ የነበረው አይሁድ ፖለቲከኛ ሄርበርት ሳሙኤል፣በካቢኔ አባላት መካከል የተሰራጨ እና ድጋፍ የተሰጠበት፣አገሪቱ ቀስ በቀስ በእንግሊዝ ግዛት ጥበቃ ስር የራስ ገዝ የአይሁድ መንግስት የምትሆንበትን እቅድ የከተበበትን"የፍልስጤም የወደፊት እጣፈንታ"የተሰኘ ሚስጢራዊ ማስታወሻውን በካቢነው አስነበበ።

የኦቶማን አገዛዝ ውድቀት በተከሰተበት ግዜ፣የብሪታንያን እና የፈረንሳይን የቅኝ ግዛት ድንበር የወሰነ(የለዬ)የ#ሳይክስ_ፒኮት ስምምነት ተፈረመ።ይህም የሳሙኤል ምክሮችን በተመለከተ ዲፕሎማቶቹ ሲር ማርክ ሲክስ እና ፍራንኮስ ጆርጅ-ፒኮት በግል ከተወያዩ በሗላ ነበር።

የእንግሊዝ መንግሥት ባልፎር መግለጫ በዴቪድ ሎይድ ጆርጅ የውጭ ጉዳይ ጸሐፊ አርተር ባልፎር እና በአይሁድ ማኅበረሰብ መሪዎች በሆኑት

1ኛ:ዋልተር ሮዝችልድ፣ 2ኛ:ባሮን ሮዝቻይል መካከል ፍልስጤም ውስጥ “ለአይሁድ ሕዝብ ብሔራዊ ቤት” ለመመስረት ድጋፍን በመደበኛነት በማወጅ እ.ኤ.አ ኖቬምበር 9 ቀን 1917 ብዙዎች የመስጠት ሕጋዊ መብት የለውም ብለው በሚከራከሩት መሬት ላይ የባለቤትነት መብት የሚሰጥ ነበር።

የፅዮናዊነት(Zionism)እንቅስቃሴ መሪዎች የነበሩት ሩትስቻል፣ሳሙኤል፣ ሲክስ እና ዌይዝማን ከአንድ ወር በኋላ በሎንደን የካቢኔ ስብሰባ ላይ ቀርበው ስላለው ሁኔታ ንግግር አደረጉ ፡፡

በሌላ በኩል የአንደኛውን የዓለም ጦርነት ፍፃሜ ተከትሎ፣የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዊድሮው ዊልሰን ወደ 90 አካባቢ አይሁድ ያልሆኑ የህዝብ ምሁራንን፣በኦበርሊን(ኦሃዮ)ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ሄንሪ ሲ ኪንግ እና በቺካጎው ነጋዴ ቻርለስ አር ክሬን የሚመራ ኮሚሽን በማቋቋም፣ከሰኔ 10 እስከ ሃምሌ 21 ቀን 1919 ባለው ጊዜ ውስጥ ሶርያ እና ፍልስጤምን ተዘዋውረው ከአከባቢው ነዋሪዎች አቤቱታዎችን በመጠየቅ እዚያ ያለውን ሁኔታ መረጃ የሰበሰቡ ሲሆን፣እንደታዘቡትም እጅግ ብዙ አረቦች፣ከማንኛውም የፈረንሳይ እና የእንግሊዝ ተልእኮ ነፃ የሆነ መካከለኛው ምስራቅን እንደሚፈልጉ ያረጋገጡ ሲሆን፣ከተቀበሉት 1,875 ያህል አቤቱታዎች መካከል 72% የሚሆነው አቤቱታ፣ፍልስጤም ውስጥ ለአይሁድ ብሄራዊ መኖሪያ መንግስት ለመመስረት የሚደረገውን ጽዮናዊያን እቅድ በፅኑ የኮነኑ እና የተቃወሙ ነበሩ።

ታዛቢዎቹም በዚህ በአካል ባረጋገጡት ዳሰሳ መሰረት፣የጽዮናውያንን አረቦችን የማፈናቀል እንቅስቃሴ በመቃወም፣ ኮሚሽኑ ፍልስጤም ውስጥ በሚገኘው የጽዮናዊነት ፍልሰት ፕሮግራም ላይ ከባድ ለውጥ እንዲያደርግ ሲል ምክረሃሳብ አቀረበ።

ነገር ግን እስከ 1922 ድረስ ያደረጉት መደምደሚያ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ሰሚ ጆሮ አላገኘም ነበር።

በ1919 በፓሪስ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ በሌተናል ኮሎኔል ቴ ሎውረንስ አሸማጋይነት፣በጽዮናዊው ልዑክ መሪ በዌዝማን እና በአረብ አቻቸው ልዑል ፋሲል ቢን ሁሴን መካከል ስምምነት ተደረገ፡፡ስምምነቱም በፍልስጤም ውስጥ አንድ ነፃ የአይሁድ ሃገር እና አንድ ነፃ የአረብ ሀገር መመስረት የሚል ነበር፡፡

እ.አ.አ. በ 1922 የተባበሩት መንግስታት ሊግ እንግሊዝ ፍልስጤምን እንድታስተዳድር መብት የሰጠ ሲሆን፣በተጨማሪም እብራይስጥን እንደ አንድ መደበኛ ቋንቋ እውቅና እንድኖረው፣የአይሁድ የትምህርት ስርዓት እና የአይሁድ ጦር እንድቋቋም ፈቃድ ሰጠ ፡፡ ብዙም ሳይቆይ የዕብራይስጥ ዩኒቨርሲቲ እና ሂስታድሩት የተሰኘ የሠራተኛ ማኅበር በ1925 ተመሰረተ።

በዚህ ሁኔታ አስርት ዓመታት የቀጠሉ ሲሆን፣በነበሩት አመታት በርካታ ፍልስጤማዊያን፣በብሪታንያ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጡንቻ የተደገፈውን ወረራ በመንቀፍ የብዙኃን ተቃውሞዎች እዚህም እዚያም  መከሰት ጀመሩ ፡፡

ባልፎር ኢየሩሳሌምን በጎበኘበት ወቅት በርካታ ፍልስጤማዊያን ከፍተኛ ተቃውሞ በማድረጋቸው በተፈጠረ ግጭት 250 የሚጠጉ አይሁዶች እና ሙስሊሞች የተገደሉ ሲሆን፣በ1929 በተነሳው የአልቡራቅ አመጽ(ثورة البراق)

በመባል በሚታወቀው ከባድ አመፅ እና ታቃውሞ የተወሰኑ ሙስሊሞችን ጨምሮ በጣም በርካታ አይሁዶች ተገድለዋል። በሌላ በኩል ለምሳሌ ሶስት ሙስሊም ወንዶች በሳሙኤል ተተኪው ሰር ጆን ቻንስለር የተገደሉ ሲሆን፣ይህም በተፈጠረው አለመረጋጋት እንደ መከላከያ ለመከላከል የታሰበ የጭካኔ ድርጊት ነበር፡፡

ግን የተቃውሞው ሂደት በ1933 ወደ ትኩሳት ደረጃ በመድረሱ ብዙ የአይሁድ መጤዎች ፍልስጤምን ለራሳቸው መኖሪያ ቤት ለማድረግ በ1931 እ.ኤ.አ. 4,000 የነበሩት ፈላሲያን በ1935 ወደ 193,000 ደረሱ።በዚያው አመት ይህን የአይሁዶች አሳሳቢ ፍሰት የሚቃወም የሙስሊሙ አብዮታዊ መሪ ሸይኽ ኢዘድን አል-ካሳም፣ከጄኒን በላይ ባሉ ኮረብታዎች በእንግሊዝ ወታደሮች ተገደሉ።

እ.ኤ.አ. በ1936 የእንግሊዝን የቅኝ አገዛዝ የተቃወመው የባልፎር መግለጫ አዋጅ ያስከተለው ተቃውሞ የስድስት ወር የአጠቃላይ አድማ አስከተለ ፡፡

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የናዚ ጀርመን መሪ የነበረው አዶልፍ ሒትለር፣ከ1939 እስከ 1945 ስድስት ሚሊዮን የሚሆኑ አይሁዶችን በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ በማጎር የጨረሰበት ክስተት ተከሰተ።

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተጀምሮ አሜሪካ ወደ ግጭቱ ከገባች ብዙም ሳይቆይ የአሜሪካ እና የፅዮናውያን ግንኙነቶች በ1942 በኒው ዮርክ በሚገኘው ቢልትሞር ሆቴል በተካሄደው ኮንፈረንስ ይበልጥ የተጠናከረ ሲሆን፣ በዚህም ኢርጉን በመባል የሚታወቀው የታጠቀ የጽዮናውያን ጦር ፍልስጤም ውስጥ ተነስቶ የአከባቢውን የአረብ ቡድኖች ማጥቃት ጀመረ።

ይህ"ኢርጉን"የተባለው እርጉም የአይሁድ አሸባሪዎች ቡድን፣ሐምሌ 22 ቀን 1946 ኢየሩሳሌም በሚገኘው በኪንግ ዴቪድ ሆቴል ፣91 ሰዎች የሞቱበትን የቦንብ ፍንዳታ አደረሰ። ቀጥሎም ከሁለት አመት በሗላ እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 9 ቀን 1948 ከሌላ ድርጅት (ሊሂ (ወይም ስተርን ጋንግ) ጋር በመተባበር፣"ድር ያሲን"በተባለ ስፍራ 107 ሰዎች የተገደሉበትን የቦንብ አደጋ አደረሰ።

በዚያው ክረምት "ሊሂ" የተባለው የአይሁድ አሸባሪ ቡድን፣የተባበሩት መንግስታት ያወጣውን የስምምነት መርህ ለማግባባት የተላከውን የስዊድን ዲፕሎማት ፎልክ በርናዶትን በመግደል፣አይሁዶች መቸም ቢሆን ሰላም የማይፈልጉ የጦር ነጋሪት ጎሳሚዎች መሆናቸውን በይፋ አሳወቁ።

እ.ኤ.አ በ 1945 በአውሮፓ እና በፓስፊክ የተባበሩት ሃይሎች(Allied powers) ጦርነቱን ማሸነፋቸውን ተከትሎ አሸናፊዎቹ  የፍልስጤምን አመፅ ለማቆም በሚመስል ፊታቸውን ወደ መካከለኛው ምስራቅ አዞሩ።

የነባር ፍልስጤማውያንን እና የሰፋሪ አይሁዶችን አለመግባባት ለመፍታት በተ/መ/ድ የቀረበው የሁለት-መንግስት ምስረታ  የመፍትሄ ሃሳብ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ1947 በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ(Assembly) ውሳኔ ሲሆን፣ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምዕራብ በኩል ከፍልስጤም አዲስ መንግስት እንድመሰረት  ሀሳብ አቀረበ፡፡

የውሳኔ ሃሳቡ የተነሳው ከአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ጫና የተነሳ ነው ተብሎ ከተነገረ በኋላ ፍልስጤማውያኑ ውሳኔውን ውድቅ አደረጉት።

በወቅቱ  ከአጠቃላይ የፍልስጤም ግዛት ውስጥ ከ5.5% የማይበልጥ መሬት የነበራቸው አይሁዶች(እርሱንም በቅሚ ነው)፣ተ/መ/ድ ያቀረበው ፍልስጤምን እኩል የመካፈል አንዳችም መብት የላቸውም በማለት ነባሮቹ ፍልስጤማውያን የተ/መ/ድን ፍርደገምድል ውሳኔ አጥበቀው ኮነኑ። በሌላበኩል ይህ የተ/መ/ድ ውሳኔ ያስፈነጫቸው አይሁዶች፣ደስታቸው ወደር አልነበረውም።

በመሆኑም ጦርነቱ ይበልጥ ተጠናክሮ ቀጠለ።

#የኢስራኤልናፍልስጤምግጭት_መቼ_እና_እንደት_ጀመረ??

#ታሪካዊዳራ___ክፍል③

"ኢስራኤል በተ/መ/ድ እንደ ሃገር እውቅና ካገኘችበት  እ.ኤ.አ.1947 ጀምሮ እስከ ዘመነ ትራምፕ ድረስ ያለው ሁኔታ!!"

____

#የ1947ቱ የተ/መ/ድ የፀጥታው ምክርቤት #ኢፍትሐዊ ውሳኔ፣በርካታ ፍልስጤማዊያንን ክፉኛ ያስቀየመ ከመሆኑም ባሻገር በርካቶችን ተወልደው ካደጉባቸው መንደሮች እንድፈናቀሉ ምክናየት ሆነ።

ይህ ኢፍትሐዊ ውሳኔ የተላለፈበትን ቀን ፍልስጤማውያን በየአመቱ “በናክባ ቀን”አስበውት ይውላሉ።ይህም “ጥፋት” ለሚለው የአረብኛ ቃል የተሰየመ ሲሆን ፍልስጤማውያን ለቀው እንዲወጡ የተገደዱባቸውን ቤቶች ቁልፍ  በማመልከት #አሁንም_ተመልሰው_እንደሚኖሩባቸው_ተስፋ_ያልቆረጡባቸውን_ግዛቶች ለመዘከር የታሰበ ነበር።

እ.ኤ.አ. በ1948 የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ፍልስጤማውያን “ #ወደቤታቸው_ተመልሰው_ከአይሁድ_ጎረቤቶቻቸውጋር_በሰላም_ለመኖር_የሚፈልጉሁሉ_በተቻለፍጥነት_ይህን_የማድረግመብት_ሊኖራቸው_እንደሚገባ” በመገንዘብ #ውሳኔ194ን አፀደቀ ፡፡  እስራኤል ምንም እንኳን ይህ በሃይልና በዙልም ከመኖሪያ ቤታቸው ያስለቀቋቸው ነባር ፍልስጤማውያን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰው ከቤታቸውና ከቀያቸው አስለቅቀው የራሳቸውን መንግስት ከመሰረቱ መጤ አይሁዶች ጋር በጉርብትና እንድኖሩ በሚል ተ/መ/ድ ያወጣውን ውሳኔ፣አድሱ የኢስራኤል መንግስት በቅፅበት ፈቃጅና ከልካይ ሁና" #የፍልስጤሞች_ወደዚህ_መመለስ_ለአዲሱ_የአይሁድ_መንግስት_ተፈጥሮአዊስጋት ነው!"በሚል ሀሳብ ውሳኔውን ላለመቀበልም ዳዳት!

ከአንድ ዓመት በኋላ ለተፈናቀሉ"ፍልስጤማውያን" ወገኖች ድጋፍ ለመስጠት በቅርብ ምስራቅ የሚገኙ የፍልስጤም ስደተኞች #የተባበሩትመንግስታት_የእርዳታ_ስራዎች_ኤጄንሲ( #unrwa)ተቋቋመ።

በእነዚያ ሁለት ክስተቶች መካከል ባለው ጊዜ እስራኤል #ከአጎራባች አረብ አገሮች ማለትም ከሊባኖስ፣ከሶሪያ ፣ከጆርዳን እና ከግብፅ ጋር የጦር መሣሪያ ስምምነቶችን ተፈራረመች።

ከዚያም እ.ኤ.አ.በ1950 ዮርዳኖስ የዌስት ባንክ አስተዳደራዊ ቁጥጥርን ስትወስድ፣ግብፅ ደግሞ ጋዛን እንድትወስድ ተደረገ።

ይህ ስምምነት እስራኤል እነዚህን ግዛቶች ከዮርዳኖስና ከግብፅ አስለቅቃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ እስከጀመረችበትና በዚህም #የ6ቀኑ_የአረብ_ኢስራኤል_ጦርነት እስከተጀመረበት ግዜ ድረስ ቆየ።

(የ6ቱን ቀን የአረብ-እስራኤል ጦርነት ሂደት በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለሁ ኢንሻ አሏህ)

ከዚያ በፊትም ብጥብጡ አልፎ አልፎ ቀጥሎ የነበረ ሲሆን፣በ1956 በቃልኪሊያ፣በኩፍርቃሲም እና በሃን ዩኒስ መንደሮች ውስጥ፣እንድሁም በ1966 አስሳሙ በተባሉ ቦታዎች እልቂቶች ተከስተዋል።

#በ1964 #የፍልስጤም_ነፃ_አውጪ _ድርጅት(PLO)ካይሮ ውስጥ የተቋቋመ ሲሆን፣ከሰላማዊ ትግል ይልቅ በትጥቅ አብዮት “ፍልስጤም ነፃ ለማውጣት”የተመሰረተ ነበር።እስራኤልናአሜሪካ ድርጅቱን በአሸባሪነት ቢፈርጁትም፣የፍልስጤም ህዝብ ብቸኛ ተወካይ መሆኑን የአረብሊግ በ1974 እውቅና ሰጠው።

የእስራኤል ወታደራዊ ጦር በጋዛ ሰርጥ፣ በዌስትባንክ፣በጎላን ከፍተኛቦታዎች እና በግብፅ ሲናይ በረሃ፣በ1967 ከፍተኛ ደም መፋሰስ ያስከተለ ሲሆን፣የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት በሃይል ተይዘዋል ብለው ካሰቡዋቸው ግዛቶች እስራኤል ጦሯን እንድታወጣ በማዘዝ #ውሳኔ242 ቢያፀድቅም፣እስራኤል ከቆብ አልቆጠረችውም ነበር።

እስራኤል በ1970 በዮርዳኖስ ውስጥ ከፍልስጤማውያን ወታደሮች ጋር በጥቁሯመስከረም(Black September)ተጨማሪ ውጊያ ማድረጓን ተከትሎ፣"የፀጥታው¡"ምክርቤት የተኩስ አቁም ጥሪ በማቅረብ እና እስራኤል ከ 1967ቱ ወረራ እንድትመለስ በመጠየቅ #ውሳኔ338 አስተላለፈ።

አሁንም እስራኤል እምቢ አለች!

በፍልስጤማውያን"የመሬትቀን"ተብሎ የሚዘከርበት፣ማርች30ቀን1976፣ የእስራኤልን የመሬት ወረራ በመቃወም ከገሊላ ባህር እስከ ኔጌቭ ድረስ ባሉ ከተሞች አመጽ፣አድማ እና ተጨማሪ የኃይል እርምጃዎችን አስከተለ።

እ.ኤ.አ.መስከረም17ቀን 1978፣የእስራኤሉ ጠ/ሚ #ሜናም_ቤገን ከግብፁፕሬዝዳንት #አንዋር_ሳዳት ጋር በፕሬዚዳንት በጂሚ ካርተር ማረፊያ የካምፕ ዴቪድ ስምምነቶችን ለመፈራረም ተገናኙ። ስምምነቱ በሁለቱ ሃገሮች(እስራኤልናግብፅ)መካከል ግንኙነታቸውን ያጠናከረና #የሰላምኖቬል_ሽልማት ያስገኘላቸውሲሆን፣በሌላ በኩል ግን ስምምነቱ የባለጉዳዮቹ ፍልስጤማውያን ውክልና የሌለበት በመሆኑ፣ግጭቱን ከማባባስ የዘለለ የፈየደው አንዳችም ነገር አልነበረም።

የእስራኤል ጦር በጋዛ የሚገኙ 4 ሲቪል ፍልስጤማዊያንን በግፍ በመግደሉ ምክናየት፣December 8, 1987 በፍልስጤምግዛቶች ውስጥ በአይነቱየመጀመሪያ የሆነ ከባድሁከት( #the_first_intifada)ተነስቶ እስከ መስከረም13,1993 ድረስ ቆየ።

በ1993 #የኦስሎI_ስምምነት(Oslo1) በእስራኤል ጠ/ሚ #ይስሃቅ ራቢንና የ PLO ሊቀመንበር #ያሲር_አራፋት የተፈረመ ሲሆን፣የፍልስጤም ጊዜያዊ የራስገዝ አስተዳደር እንድመሰረትና  የእስራኤል ጦር ከተ/መ/ድ እውቅና ውጭ በሃይል ከያዛቸው ቀጠናዎች እንዲወጣ ተደረገ፡፡ነገር ግን ኢስራኤል ስምምነቱን በማፍረሷ

#ሁለተኛው_የኦስሎ_ስምምነት(Oslo2)እ.ኤ.አ.በ1995 ተደረገ።በዚህም በተወሰኑ የዌስትባንክ እና የጋዛ አካባቢዎች የፍልስጤም የራስ ገዝ አስተዳደርን እውቅና ቢሰጥም፣የፍልስጤምን ሉኣላዊ ሃገርነት ግን አሁንም አላፀደቀም ነበር።

በመስከረም28,2000 #ሁለተኛውከባድ አመፅ( #the second Intifada)የተቀሰቀሰ።ዋነኛ ምክናየቱ የእስራኤል ጠ/ሚ #አርኤል_ሻሮን #በአልአቅሷ መስጅድ ጉብኝት ማድረጉ ነበር።

በ2002 እስራኤል ዌስትባንክን ወረረች።ይህም #በ2004_ከያሲር_አራፋት_ሞት ጋር ተዳምሮ ፍልስጤማውያንን ክፉኛ ጎዳቸው።

በ2006 በፍልስጤም በተካሄደ ምርጫ #ሃማስ አብላጫ ድምፅ በመያዝ አሸነፈ።ሆኖም በምርጫ የተሸነፈው ፋታህ(PLO)ውጤቱን ባለመቀበሉ ሃማስናፋታህ #የርስበርስ_ጦርነት አደረጉ።በመጨረሻም ሃማስ ጋዛን ሲቆጣጠር፣ፋታህ ደግሞ ዌስትባንክን ያዘ።

በ2006 እስራኤል በሊባኖስ በሚገኘው"ሂዝቦላህ"የተባለ ቡድን ላይ ጦርነት አወጀች።

አስከትላም  በጋዛ በሚገኘው ጅሃድስት ቡድን(ሃማስ)ላይ፣ኦፕሬሽን ካስት ሊድ(2008)፣ኦፕሬሽን የመከላከያ ዓምድ(2012) እና የኦፕሬሽን መከላከያ ጠርዝ(2014)ን ጨምሮ በጋዛ ውስጥ በተደጋጋሚ ጥቃት መሰንዘር ጀመረች፡፡  ይህ ሳያንሳት በ2017 እና በ20018፣ፍልስጤማውያን የናክባ ቀን በሚያስቡበት እለት፣በተ/መ/ድ #የጦርወንጀሎች_ምርመራ የሚያስጠይቅ የሆነ ከባድጥቃት አደረሰች።

በ2017በአሜሪካ በተደረገው ምርጫ #ዶናልድ_ትራምፕ መመረጥ ሁኔታውን ዳግም አገረሸው።ለዚህም ዋነኛ ማሳያ ትራምፕ የአሜሪካን ኤምባሲ #ከቴልአቪቭ_ወደ_ኢየሩሳሌም ማዘወሩ ነበር፡፡ትራምፕ ዓለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ፣ #የጎላን ከፍተኛቦታዎችን የእስራኤል መሆናቸውንም አፀደቀ።

ይህም አልበቃ ብሎት አሜሪካ ለUNRWA የምትመድበውን የገንዘብ ድጋፍም አቋረጠ።🔚

የመረጃ ምንጮቼ:

#አልጀዚራ #ቢቢሲ #ዊኪፔድያ

#ኢንሳይክሎፔድያብሪታኒካ #ዘጋርድያን #ሂስትሪዶትኮም እና ሌሎችም ናቸው።

t.me/Seyfel_Islam

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Sultan Bushira Сhanged his profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group