yusuf mukemil Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

yusuf mukemil пайларӗ
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

የመጨረሻው የመስጂደል አቅሳ ጠባቂ

Mahi mahisho

ይህንን ታሪክ ስተረጉም ዕንባ እየተናነቀ የራሴ ልብ ሰላም ነስቶ በብረት ክንድ ይደልቀኛል። የዕንባ ከረጢቴ ዘለላ ዘለላ ዕንባን እያረገፈ ሆድ ያስብሰኛል። እንዲህ ዓይነት የኢስላም ዘቦች ማለፋቸው እያስገረመ ያስለቅሰኛል። ቁጭት፣ ብሶት፣ ንዴትና ሀዘን ተፈራርቀው እኔስ ለኢስላም ምን አበረከትኩ ያስብለኛል።

እርሱ ኢየሩሳሌምን ለቆ ወደ ሀገሩ ቱርክ እንዲመለስ በታዘዘ ጊዜ “በይተል መቅዲስ ከሁሉ ነገሬ በላይ ነች ሦስተኛውን ቅዱስ ስፍራ ትቼ ብሄድ ረሱል ያዝኑብኛልና ፈፅሞ ይህን ቦታ ለቅቄ አልሄድም" ነበር ያለው።

“ኢልሃን በርዳክጂ” የተሰኘ የቱርክ ጋዜጠኛ “አቅሳ መስጂድ ግቢ ውስጥ አውቀዋለሁ” በሚል ርዕስ ታሪኩን እንዲህ ሲል ያካፍለናል:-

“አየሩ ሞቃታማ ነበር ሰውነቴ በላብ ተዘፍቋል። ፎቶግራፍ እያነሳሁ ወደ ላይኛው አደባባይ ወደ አስራ ሁለት ሺህ ሻማዎች ግቢ ወጣሁ፡፡ ከመግቢያው በራፍ አካባቢ በዘጠናዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኝ አንድን ሰው ተመለከትኩ። ልብሶቹ ቆሽሸዋል። ስጋ የለውም በአጥንቱ ቀርቷል። ማደሪያ የለው እዚያው ግርግዳውን ተደግፎ አረፍ ይላል። ከርሃብ መፈራረቅ ብዛት ሆዱ ከጀርባው ጋር ሊጣበቅ ተቃርቧል። ያደፉ ልብሶችን ያጠለቀ ፀጉሩና ፂሙ የተንጨባረሩ ጥቁርቁር ያለ ፊት ድህነት አጎሳቅሎ ያጠወለገው ሰው ይታያል።

አጠገቤ ከነበሩት ሰዎች አንዱን ጠርቼ ይህ ሰው ማነው? በማለት ጠየቅኩት "እብድ ነው እዚህ እንደ ሃውልት ቆሞ ለዓመታት ኖሯል። ማንንም አያናግርም። እሱ የሚመለከተው መስጂዱን ብቻ ነው" የሚል መልስ ቸረኝ።

ተጠጋሁትና ሰላምታ አቀረብኩለት። ዞረና ተመለከተኝ ዓይኖቹን ወደ መስጂዱ አቅጣጫ እየመለሰ "ሰላም ላንተ ይሁን" አለኝ። ይበልጥ ተጠጋሁትና ስለ ማንነቱ ጠየቅኩት፡፡ ሐዘን ባጠወለገው ፊቱ ጥርሱን ፈልቅቆ እንዲህ ሲል ታሪኩን አጫወተኝ

"እኔ የአስራ አንደኛው የመሣሪያ ጥበቃ ቡድን መሪ ስምንተኛው ሻለቃ የኦቶማን ጦር ስድስተኛው አምድ ኮረኔል ሐሰን አልግህዳርሊ ነኝ"

"ኦቶማን ኢምፓየር እየተጠቃ በነበረበት በዛን ወቅት በይተል መቅዲስ እንዳይዘረፍ ሰራዊታችን ተመደበ፡፡ የእንግሊዝ ጦር መስጂደል አቅሳን እንደተቆጣጠረ እኔም ጓደኞቼም ተይዘን በአንድ ክፍል ታጎርን"

ወደ ሀገሬ እንድመለስ ትዕዛዝ ሲሰጠኝ የካፒቴን ሙስጠፋ ንግግር ትዝ አለኝ

"ኢስላማዊው መንግስት በመፈረካከስ ላይ ነው። የተከበረው ሰራዊታችንም እየሸሸ ነው። አመራሩ ወደ ኢስታንቡል እንድመጣ ጠርቶኛል። በይተል መቅዲስ የሱልጣን ሰሊም አደራ ነው። ኢየሩሳሌምን ሸሽቶ የሄደ የመጀመሪያው ጦር እንዳንሆን ተጠንቀቁ፡፡ አደራ የእስልምናን ክብር ከእግራችሁ በታች እንዳታስቀምጡት"

ይህ ቃል ታወሰኝ በፍልስጤም ያሉ ወንድሞቻችን ኢስላማዊው ጦር ኦቶማን ኢምፓየር ጥሎን ሄደ እንዳይሉና እርዳታን የነፈግናቸው እንዳይመስላቸው በማሰብ ብቻዬን እዚያው ቆየሁ፡፡ ከአራት መቶ ዓመታት በኋላ የአል-አቅሳ መስጂድ እንዳያነባ ሰጋሁ። በዚህ ሁኔታ ዓመታቶች እንደ ዐይን ብልጭታ አለፉ። ሃምሳ ሶስት ነበርን። ጠላቶቻችንን ተጋፍጦ ማሸነፍ ሳይቻለን ቀርቶ የሁሉም ጓደኞቹ እጣ ፈንታ ሸሂድነት ሆነ"

ዓይኖቹ በዕንባ ተሞልተው ዕንባው ግንባሩ ላይ ከሚወጣው ላብ ጋር ተቀላቀለ።

"ልጄ እባክህ ስትመለስ ወደ ሳንጃክ ቶካት መንደር አቅና። የካፒቴን ሙስጠፋ መኖርያ እዚያ ነው፡፡ አማናውን የተቀበልኩት ከርሱ ነው። ስታገኘው እጆቹን ሳምልኝና እንዲህም በለው። አንድ ወታደርህ ባስቀመጥከው እዚያ ቦታ መስጂደል አቅሳን እየጠበቀ ነው በትዕዛዝህ መሠረት ካስቀመጥከው ቦታ አልተነቃነቀም። መስጂደል አቅሳን ከመጠበቅ ስራው ለአፍታም ተዘናግቶ አያውቅም ዱዓህን ይከጅላል በለው"

ጋዜጠኛው ንግግሩን ይቀጥላል

"ቱርክ እንደተመለስኩ ወደ ሳንጃክ ቶካት መንደር አመራሁ ከብዙ ጥረት በኋላ የአለቃውን አድራሻ አገኘሁ፡፡ ከብዙ ዓመታት በፊት መሞቱ ተነገረኝ።

የተመቻቸውን የትውልድ ሀገሩን ኑሮ ትቶ አል-አቅሳ መስጂድን እየጠበቀ ዓይኑን ከመስጂዱ ላይ ሳይነቅል እዚያው በተቀመጠበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1982 ወደ አኼራ ነጎደ፡፡

ለአመታት ፀሐይና ብርዱ እየተፈራረቀብን ለኢስላም ዘበኛ ልንሆን ይቅርና በታዘዝነው የኢስላም ህግጋት ላይ ቀጥ ያልን ስንቶቻችን ነን የተመቻቸ ኑሮውን ትቶ ተቦሳቁሎና ተርቦ ለኢስላም ዘብ የቆመን ፈልጋችሁ አምጡልኝ።

በታሪክ መዝገብ ላይ በጥሩ ተዘከር

image
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас
yusuf mukemil пайларӗ
7 уйӑх Куҫарас
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

9ኙ.ሚስጥሮች.tt

📚 ቁርኣንን ለመሓፈዝ 9 ሚስጥሮች

🌀1ኛው ሚስጥር : ለቁርኣን ሒፍዝ ከፍተኛ የሆነ ጉጉት ፣ ፍላጎትና ተነሳሽነት ሊኖርህ ይገባል ፣

🌀 2ኛው ሚስጥር : ኢኽላስ (ለአሏህ ብቻ ብሎ መሐፈዝና) አሏህ ቁርኣን ሂፍዝን እንዲያገራልህ ሁሌም ዱዓ ማድረግ ፣

🌀 3ኛው ሚስጥር : ሀላፊነቱን ራስህ ውሰድ ፣ ምክንያት አታብዙ (እድሜህ ቢገፋ ፣ የማስታወስ አቅምህ ቢያንስ...)

🌀 4ኛው ሚስጥር : በአቅምህ ልክ ሀፍዝ እንዲሁም በአንድ ሙስሓፍ (አንድ ተመሳሳይ ገፅ ያለው የቁርኣን እትም) ብቻ ተጠቀም።

🌀 5ኛው ሚስጥር : ለሒፍዝ ተስማሚማ ተዛማች ጊዜና ቦታ ምረጥ (ስሁርና ፈጅር ወቅቶች የተሻሉ ሲሆኑ ማታ አይመከርም ፣ ቦታም ፀጥታ ያለበት ብዙ ቀልብን ሳቢ የሆኑ ነገራቶች የሌሉበት ቢሆን ይመከራል)

🌀 6ኛው ሚስጥር : 3ቱንም ዋና የሒፍዝ ሞተሮችን አንቃቸው - አይንህን ጆሮህንና ልብህን ክፍትና ንቁ አድርገህ መሓፈዝ ይኖርብሀል ፣ አንድኛቸውንም ከተውካቸው መሀፈዝህ ትርጉም አልባ ይሆናል።

🌀 7ኛው ሚስጥር : በተደጋጋሚ ማጥናትና ሙራጀዓ ማድረግ አትዘንጋ ፣ (ቀኑን ሙሉ እና ከመኝታ በፊት በኦድዬ በማዳመጥ ፣ እንዲሁም በየ ትርፍ ሶላቶች ላይ በመቅራት ሙራጀዓ ላይ ተጠባከር)

🌀 8ኛው ሚስጥር : ቋሚማ ወጥ የሆነ ፕሮግራም ይኑርህ ፣ በየቀኑ ምን ያክል ተሀፍዛለህ? ምን ያክሉን ሙራጀኣ ታደርጋለህ? መቼ ሂፍዝ ትጨርሳለህ? ወጥ የሆነና ቋሚ ፕሮግራምና እቅድ ይኑርህ

🌀 9ኛው ሚስጥር : ከወንጀል ራስህን አርቅ እንዲሁም አሏህ እንዲያገራልህ ሁሌም ዱዓ በማድረግ ላይ አትስነፍ።

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈

© ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል

✍ በOnline ተመዝግቦ ቁርኣን ለመማር በዚህ ሊንክ ያመልክቱ 👇

@FurqanOnlineQuran

Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас