UMMA TOKEN INVESTOR

About me

ሙስሊም ነህ ማለት.. §ኣንድ አምላክ ታመልካለህ፣ ኣንድ መመሪያ (ቁርዓን)ን ትከተላለህ፣በተላኩ ነቢያቶች ነብይነት ታምናለህ በነሱም አታበላልጥም ወደ ኣንድ ቂብላ ዞረህ ትሰግዳለህ ....ኢስላም ዩኒቨርሳል ባህሪው በመላው አለም ሁሉም ሙስሊም ወጥ አምልኮ እና ስርዓት ይከተላል ❤ኢስላም§ ❤ አሰላሙ አለይኩም ታዳሚዬ

Translation is not possible.

መህዲ ማነው?

‹‹መህዲ›› በመጨረሻው ዘመን ከደጃልና ዒሳ መምጣት አስቀድሞ የሚነሳ ታላቅ ‹‹ኸሊፋ›› ነው። ‹‹መህዲ›› የማዕረግ ስሙ ሲሆን ‹‹ሁዳ›› ከሚለው ቃል የተገኘና ‹‹የተመራ ቅን ኸሊፋ›› ማለት ነው። መጠሪያ ሙሉ ስሙ ደግሞ ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ አል-መህዲ›› ነው።

ስለ መህዲ በቁርኣን የተነገረ ምንም ነገር አናገኝም። መረጃዎቹ በሙሉ ከሐዲስ የተገኙ ሲሆን ከሃያ በላይ የተረጋገጡ ዘገባዎች ይገኛሉ። ብዙ የሱንና ዑለማዎች ስለ መህዲ የፃፉ ሲሆን ቲርሚዚና አቡ-ዳውድ ራሱን የቻለ ምዕራፍ ሰጥተውታል።

ከሁሉም ታዋቂው ሐዲስ አቡ-ዳውድ የዘገቡት ሲሆን ነቢዩ (ዐሰወ) እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ትንሳኤ ሊቆም አንድ ቀን ቢቀረው እንኳን አላህ ከቤተሰቤ የሆነን፤ ስሙ ከእኔና ከአባቴ ጋር የሚመሳሰል መሪን ሳያስነሳና በበደል የተዋጠችውን ምድር በፍትህ ሳይሞላት አይተዋትም።››

(አቡ-ዳውድ 4282)

ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው መህዲ የነቢዩ (ዐሰወ) ቤተሰብ ነው። ስሙም የነቢዩን (ዐሰወ) እና አባታቸውን የያዘ ሲሆን ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ›› ወይም ‹‹አህመድ ኢብን አብዱላህ›› ነው። የሚመጣውም ዓለም በዙልም በተዋጠችበት በመጨረሻው ዘመን ሲሆን የአላህን ቃል ከፍ በማድረግ ፍትህን ያነግሳል።

ኡሙ ሰላማ (ረዐ) እንደተናገረችው ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ በፋጡማ በኩል የሚገኝ ቤተሰቤ ነው።›› ብለዋል። ኢብኑል ቀይም ይሄንን ሐዲስ ሲያብራሩ ‹‹መህዲ የሐሰን ዘር ሲሆን አል-ሐሰን ለሙስሊሙ አንድነት ሲሉ ኸሊፋነታቸውን አሳልፈው በመስጠታቸው ምክንያት አላህም በመጨረሻው ዘመን ከቤተሰባቸው ታላቅ ኸሊፋ በማስነሳት ክሷቸዋል።›› ሲሉ ፅፈዋል።

(አቡ-ዳወድ 11/373)

አቡ-ሰዓድ አልኩድሪ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ (ዐሰወ) ስለ መህዲ ገፅታ ሲናገሩ ‹‹ቁመቱ ረጂም፣ ትከሻው ሰፊ፣ አፍንጫው አጠፍ ያለ ነው።›› ብለዋል።

(አቡ-ዳውድ 4265)

መህዲ የሚነሳበትን ቦታ በተመለከተ የተለያዩ ዘገባዎች አሉ። ከፊሎቹ ከሻም ከፊሉ ከኹራሳን ሌላው ደግሞ ከመዲና እንደሆነ ይናገራሉ። ኢብን ከሲር የሁሉንም ሐዲሶች ጥቅል ሀሳብ ሲያስቀምጡ ‹‹የሚነሳው ከምስራቅ ነው። ከዚያም ወደ መካ ይሄዳል። ሰዎችም በከዓባ ዙሪያ ቃልኪዳን ይገቡለታል።›› ብለዋል። እንዲሁም በሌላ መጽሐፋቸው ‹‹በሐዲስ በተጠቀሰው መሰረት ባንዲራው ጥቁር ነው።›› በማለት አብራርተዋል።

(አልቢዳያህ ወልኒያህ 19/63፤ አልፊታን ወልመላሂም 1/49)

ኢማም አህመድ እንደዘገቡት መህዲ መሪነት ሲመረጥ ፍላጎቱም ክህሎቱም አልነበረውም። እናም ‹‹አላህ በአንድ ሌሊት ይመራዋል።›› ብለዋል (ዐሰወ)። ኢብን ከሲር ሐዲሱን ሲያብራሩ፡- ‹‹ይህ ማለት አላህ ይረዳዋል፣ ከዚህ በፊት ያልነበረውን ችሎታም ይሰጠዋል ማለት ነው።›› ብለዋል።

(አህመድ 2/58/ አልፊታን ወልመላሂም 1/29)

መህዲ ኸሊፋነትን ከተረከበ በኋላ ሙስሊም አገራትን በአንድ በማፅናት በቀደመው ኢስላማዊ አስተዳደር ስር ያስገባቸዋል። ከዚያም በቡኻሪ እና ሙስሊም (2897) እንደተዘገበው ከሮማውያን ጋር የመጨረሻው ታላቁ ጦርነት ‹‹አል-መልሃማ አል-ኩብራ›› ይካሄዳል። ሙስሊሞችም ዳቢቅ ላይ ድል ደርጋሉ። ከዚህ በፊት ያልተከፈቱ አገራትንም ይከፍታሉ። ከዚያ በኋላ ሙስሊሞች በየትኛውም ኃይል አይሸነፉም። አላህ አማኞችን ከፍተኛ የሀብት መትረፍረፍ ይባርካቸዋል።

ሸይህ ዑመር ሱለይማን አል-አሽቀር ሐዲሱን መሰረት በማድረግ እንደተናገሩት ‹‹ይህ ጦርነት ከባድ ውድመትን ስለሚያስከትል ዓለም አሁን ካለችው ስልጣኔ ወደኋላ በመመለስ እንደ ጥንቱ በጦር በጋሻ በፈረስ መጠቀም ይጀምራሉ።›› ብለዋል።

(አል-ቂያማህ አስ-ሱግራ 275)

መህዲ ታላቅ ጦርነት አድርጎ ሙስሊሞችን የበላይ ቢያደርግም ጊዜው የቂያማህ ቀን መቃረቢያ በመሆኑ ከባባዶቹ ፊትናዎች ይከሰታሉ። ከእነዚህም መካከል ቀዳሚው የደጃል መነሳት ነው። እሱን ተከትለው የዕጁጅና መዕጁጆች ከጉድጓዳቸው ይወጣሉ። በዚህ ጊዜ አላህ ዒሳን (ዐሰ) ለእርዳታ ይልከዋል።

በሐዲስ እንደተጠቀሰው ዒሳ (ዐሰ) ወደ ምድር የሚወርደው በፈጅር ሰላት ወቅት ነው። ነቢዩ (ዐሰወ) ስናገሩ ‹‹መህዲ ዒሳን አሰግደን ይለዋል። ዒሳም እናንተ መሪዎች መሆናችሁ ከቂያማህ ምልክቱ ነውና አንተ አሰግደን ይለዋል። ዒሳም ከመህዲ ኋላ ተከትሎ ይሰግዳል።›› ብለዋል።

(ሙስሊም 225)

ከዚያ በኋላ ዒሳ ከሙስሊሞች ጋር በመሆን የዕጁጆችንና ደጃልን በመጋደል በአላህ ዕርዳታ ያጠፋቸዋል። ነቢዩ (ዐሰወ) እንደተናገሩት ‹‹ሙስሊሞች ለሰባት ዓመታት ያህል የየዕጁጆችን አጥንት ቀስትና ጋሻ ለማገዶነት ይጠቀሙበታል።

መህዲ በኸሊፋነት የሚቆይባቸው ዓመታት ‹‹ሰባት›› እንደሆኑ አብዛኛዎቹ የሐዲስ ምሁራን ይናገራሉ። ከእነሱ መካከል አንዱ የኢብኑ ማጃህ ሲሆኑ ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ ሰባት አጭር ጊዜያትን ይቆያል።›› ማለታቸውን ዘግበዋል።

(ኢብን ማጃህ 4039)

አል-መህዲ እስኪመጣ ሙስሊሙ ጂሐድን በመተው መጠበቅ ይኖርበታል? ለሚለው ጥያቄ ሸይህ ሙሐመድ ሷሊህ አል-ሙነጂድ በፈትዋ ገፃቸው እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ከጂሐድ መዘንጋት ከከባባድ ወንጀሎች አንዱ ነው። አላህ ያዘዘው ሁሉም የራሱን ግዴታ እንዲሞላ ነው። መህዲ የራሱ ጂሐድ አለው። ይሄም ህዝብ የራሱን ጂሐድ ማድረግ ግዴታው ነው። አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ብሏል፡-

‹‹ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚሆን ድረስ ተጋደሏቸው። ቢከለከሉም አላህ የሚሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነው።››

(አንፋል፡ 39)

©tehwidsuna

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የፍልስጤም ህፃናት ሰቆቃ..😭😭

17 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

10 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የመጨረሻው የመስጂደል አቅሳ ጠባቂ

Mahi mahisho

ይህንን ታሪክ ስተረጉም ዕንባ እየተናነቀ የራሴ ልብ ሰላም ነስቶ በብረት ክንድ ይደልቀኛል። የዕንባ ከረጢቴ ዘለላ ዘለላ ዕንባን እያረገፈ ሆድ ያስብሰኛል። እንዲህ ዓይነት የኢስላም ዘቦች ማለፋቸው እያስገረመ ያስለቅሰኛል። ቁጭት፣ ብሶት፣ ንዴትና ሀዘን ተፈራርቀው እኔስ ለኢስላም ምን አበረከትኩ ያስብለኛል።

እርሱ ኢየሩሳሌምን ለቆ ወደ ሀገሩ ቱርክ እንዲመለስ በታዘዘ ጊዜ “በይተል መቅዲስ ከሁሉ ነገሬ በላይ ነች ሦስተኛውን ቅዱስ ስፍራ ትቼ ብሄድ ረሱል ያዝኑብኛልና ፈፅሞ ይህን ቦታ ለቅቄ አልሄድም" ነበር ያለው።

“ኢልሃን በርዳክጂ” የተሰኘ የቱርክ ጋዜጠኛ “አቅሳ መስጂድ ግቢ ውስጥ አውቀዋለሁ” በሚል ርዕስ ታሪኩን እንዲህ ሲል ያካፍለናል:-

“አየሩ ሞቃታማ ነበር ሰውነቴ በላብ ተዘፍቋል። ፎቶግራፍ እያነሳሁ ወደ ላይኛው አደባባይ ወደ አስራ ሁለት ሺህ ሻማዎች ግቢ ወጣሁ፡፡ ከመግቢያው በራፍ አካባቢ በዘጠናዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኝ አንድን ሰው ተመለከትኩ። ልብሶቹ ቆሽሸዋል። ስጋ የለውም በአጥንቱ ቀርቷል። ማደሪያ የለው እዚያው ግርግዳውን ተደግፎ አረፍ ይላል። ከርሃብ መፈራረቅ ብዛት ሆዱ ከጀርባው ጋር ሊጣበቅ ተቃርቧል። ያደፉ ልብሶችን ያጠለቀ ፀጉሩና ፂሙ የተንጨባረሩ ጥቁርቁር ያለ ፊት ድህነት አጎሳቅሎ ያጠወለገው ሰው ይታያል።

አጠገቤ ከነበሩት ሰዎች አንዱን ጠርቼ ይህ ሰው ማነው? በማለት ጠየቅኩት "እብድ ነው እዚህ እንደ ሃውልት ቆሞ ለዓመታት ኖሯል። ማንንም አያናግርም። እሱ የሚመለከተው መስጂዱን ብቻ ነው" የሚል መልስ ቸረኝ።

ተጠጋሁትና ሰላምታ አቀረብኩለት። ዞረና ተመለከተኝ ዓይኖቹን ወደ መስጂዱ አቅጣጫ እየመለሰ "ሰላም ላንተ ይሁን" አለኝ። ይበልጥ ተጠጋሁትና ስለ ማንነቱ ጠየቅኩት፡፡ ሐዘን ባጠወለገው ፊቱ ጥርሱን ፈልቅቆ እንዲህ ሲል ታሪኩን አጫወተኝ

"እኔ የአስራ አንደኛው የመሣሪያ ጥበቃ ቡድን መሪ ስምንተኛው ሻለቃ የኦቶማን ጦር ስድስተኛው አምድ ኮረኔል ሐሰን አልግህዳርሊ ነኝ"

"ኦቶማን ኢምፓየር እየተጠቃ በነበረበት በዛን ወቅት በይተል መቅዲስ እንዳይዘረፍ ሰራዊታችን ተመደበ፡፡ የእንግሊዝ ጦር መስጂደል አቅሳን እንደተቆጣጠረ እኔም ጓደኞቼም ተይዘን በአንድ ክፍል ታጎርን"

ወደ ሀገሬ እንድመለስ ትዕዛዝ ሲሰጠኝ የካፒቴን ሙስጠፋ ንግግር ትዝ አለኝ

"ኢስላማዊው መንግስት በመፈረካከስ ላይ ነው። የተከበረው ሰራዊታችንም እየሸሸ ነው። አመራሩ ወደ ኢስታንቡል እንድመጣ ጠርቶኛል። በይተል መቅዲስ የሱልጣን ሰሊም አደራ ነው። ኢየሩሳሌምን ሸሽቶ የሄደ የመጀመሪያው ጦር እንዳንሆን ተጠንቀቁ፡፡ አደራ የእስልምናን ክብር ከእግራችሁ በታች እንዳታስቀምጡት"

ይህ ቃል ታወሰኝ በፍልስጤም ያሉ ወንድሞቻችን ኢስላማዊው ጦር ኦቶማን ኢምፓየር ጥሎን ሄደ እንዳይሉና እርዳታን የነፈግናቸው እንዳይመስላቸው በማሰብ ብቻዬን እዚያው ቆየሁ፡፡ ከአራት መቶ ዓመታት በኋላ የአል-አቅሳ መስጂድ እንዳያነባ ሰጋሁ። በዚህ ሁኔታ ዓመታቶች እንደ ዐይን ብልጭታ አለፉ። ሃምሳ ሶስት ነበርን። ጠላቶቻችንን ተጋፍጦ ማሸነፍ ሳይቻለን ቀርቶ የሁሉም ጓደኞቹ እጣ ፈንታ ሸሂድነት ሆነ"

ዓይኖቹ በዕንባ ተሞልተው ዕንባው ግንባሩ ላይ ከሚወጣው ላብ ጋር ተቀላቀለ።

"ልጄ እባክህ ስትመለስ ወደ ሳንጃክ ቶካት መንደር አቅና። የካፒቴን ሙስጠፋ መኖርያ እዚያ ነው፡፡ አማናውን የተቀበልኩት ከርሱ ነው። ስታገኘው እጆቹን ሳምልኝና እንዲህም በለው። አንድ ወታደርህ ባስቀመጥከው እዚያ ቦታ መስጂደል አቅሳን እየጠበቀ ነው በትዕዛዝህ መሠረት ካስቀመጥከው ቦታ አልተነቃነቀም። መስጂደል አቅሳን ከመጠበቅ ስራው ለአፍታም ተዘናግቶ አያውቅም ዱዓህን ይከጅላል በለው"

ጋዜጠኛው ንግግሩን ይቀጥላል

"ቱርክ እንደተመለስኩ ወደ ሳንጃክ ቶካት መንደር አመራሁ ከብዙ ጥረት በኋላ የአለቃውን አድራሻ አገኘሁ፡፡ ከብዙ ዓመታት በፊት መሞቱ ተነገረኝ።

የተመቻቸውን የትውልድ ሀገሩን ኑሮ ትቶ አል-አቅሳ መስጂድን እየጠበቀ ዓይኑን ከመስጂዱ ላይ ሳይነቅል እዚያው በተቀመጠበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1982 ወደ አኼራ ነጎደ፡፡

ለአመታት ፀሐይና ብርዱ እየተፈራረቀብን ለኢስላም ዘበኛ ልንሆን ይቅርና በታዘዝነው የኢስላም ህግጋት ላይ ቀጥ ያልን ስንቶቻችን ነን የተመቻቸ ኑሮውን ትቶ ተቦሳቁሎና ተርቦ ለኢስላም ዘብ የቆመን ፈልጋችሁ አምጡልኝ።

በታሪክ መዝገብ ላይ በጥሩ ተዘከር

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group