አሜሪካ ስለምን የእስራኤል የነፍስ አባት መሆንን መረጠች ? ለመሆኑ ለአሜሪካ የእስራኤል አስፈላጊነትስ እስከምን ነው ?
👉 t.me/Seidsocial
ባለፈው ፅሁፌ አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገው ድጋፍ ምን ያክል ገደብ አልባና በሁሉም ዘርፍ በጣም ግዙፍ መሆኑን ለማሳየት ሞክሪያለሁ ። ዛሬ ደግሞ ለመሆኑ ለምን ሲባል ? የሚለውን ለማየት እሞክራለሁ ።
1 የእስራኤል የማይተካ ስትራቴጂካዊ ቦታነት
አንድ የአሜሪካ ሴናተር እስራኤልን ሲገልፃት " እስራኤል የአሜሪካ የጦር ጀት ተሸሚ መርከብ እንደማለት ናት " ይላታል ። አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ለምታካሒዳቸው ዘመቻዎች እና እንቅስቃሴዎች ሁሉ ቁልፏ ሀገር እስራኤል ናት ። በመካከለኛው ምስራቅ ብቸኛዋ ሙስሊም ያልሆነችውን እስራኤልን የሚያክል ሌላ ታማኝ ሀገር ለአሜሪካ ማግኘት ከባድ ነው ። ዛሬ ወዳጆቿዋ የሆኑት እነ ሳኡዲ ፣ ግብፅ ፣ ኢማራት ወዘተ አንድ ቀን መንግስታቸው ቢቀየር የአሜሪካ ጠላት ሆነው እንደሚነሱ ለመተንበይ የፖለቲካ ጠበብት መሆንን አይጠይቅም ። ስለዚህ እነርሱ ለጊዜ እና ጥቅም ስላስተሳሰራቸው እንጅ ለአሜሪካ አስተማማኝ የቀጠናው አጋር ሊሆኑ አይችሉም ። በዚያ ላይ ህዝቦቻቸው አሜሪካ ጠሎች ናቸው ።
እስራኤል ግን ከዚህ የተለየች ናት ። የፈለገውን ያክል መንግስታት ቢቀያየሩ የአሜሪካ ወዳጅ ከመሆን ውጭ ምርጫ ስለሌላት የአሜሪካን ጥቅም በመካከለኛው ምስራቅ ሳታወላውል ታስፈፅማለች ። ዜጎቿም አሜሪካን ኦንደጠባቂያቸው የሚያዩ በመሆኑ ለአሜሪካ ጥላቻ ያለው እስራኤላዊ የለም ። በመሆኑ በቀጠናው አሜሪካ እስራኤልን በማንም አትተካትም ።
2 የእስራኤል ሎቢዎች ( The Israel lobby )
John Mearsheimer እና Stephen Walt የተሰኙ የፖለቲካ ጠበብቶች በጋራ በፃፉት " The Israel lobby " በተሰኘ መፅሀፋቸው አሜሪካ በዚህን ያክል መልኩ ለእስራኤል ገደብ አልባ ድጋፍ የምታደርገው የእስራኤል ስትራቴጂካዊ አጋርነት ያን ያክል አስፈላጊ ሆኖ ሳይሆን የእስራኤል ሎቢዎች በአሜሪካ የሚሰሩት እጅግ ወደር አልባ የማግባባት ስራ ነው ይላሉ ።
በአሜሪካ ትልቁ የእስራኤል ሎቢ America Israel Public Affairs committee( #aipac ) ይሰኛል ። ይህ ድርጅት የአሜሪካ ህግ አውጪዎችን በማግባባት እና በማሳመን አሜሪካ ለእስራኤል ያደላ ውሳኔ እንድታሳልፍ የሚያደርገው ትልቁ ተቋም ነው ። ይህ ተቋም በአይሁዳውያን ባለሀብቶች በከፍተኛ ሁኔታ የሚደገፍ ከመሆኑም በላይ ከአሜሪካ ክርስቲያኖች በተለይ ከኢቫንጀሊካኖች ከፍተኛ ድጋፍ ይደረግለታል ። እናም ይህ ተቋም ከባለስልጣናት እስከ ሚዲያዎች ለእስራኤል ያደላ ውሳኔዎችና የሚዲያ ዘመቻዎች እንዲደረጉ ከፍተኛ ግፊት ያደርጋል ።
በዚህ የማይስማሙ የፖለቲካ ሊሂቃን ደግሞ ዋናው የእስራኤል ስትራቴጂካዊ አጋርነት እና የአሜሪካ ጥቅም አስከባሪነት እንጅ የሎቢ ድርጅቶች ተፅእኖ አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ ።
3 ሀይማኖታዊ ምክንያቶችና ኢስላም ጠልነት
እንደውም ትልቁ ምክንያት ይህ ይመስላል ። በአሜሪካ ትልቁን የአማኞች ቁጥር የሚሸፍኑት የኢቫንጀሊካን ፕሮቴስታንት አማኞች በኢስላም ጠልነት ተወዳዳሪ የላቸውም ። ከ 70% በላይ የሚሆነው አሜሪካዊ የኢቫንጀሊካን አማኝ አንድም ሙስሊም በአሜሪካ ማየት አይፈልግም ። እነዚህ አሜሪካዊያን የኢስላም ጠላት ካሉት ጋር ሁሉ ጥምረትና ወዳጅነት ይፈጥራሉ ። በኢስላምና በሙስሊሞች ላይ ጠላትነት ላወጀ ሁሉ እነርሱ ወዳጅነትን ያውጃሉ ።
ኢቫንጄሊካኖች እስራኤልን የአረቦችና ሙስሊሞች ቀንደኛ ጠላት አድርገው ነው የሚቆጥሩት ። በመሆኑ ለእስራኤል አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ልታደርግ ይገባታል ብለው በፅኑ ያምናሉ ። እናም የእስራኤል ጉዳይ ከነርሱ ጋር ቁልፍ ከሚባሉ ጉዳዮች አንዱ ነው ። የምርጫ ቅስቀሳ ወቅትም ከግምት ከሚገቡ ነገሮች ከቀዳሚዎቹ ለእስራኤል የሚደረግ የፖሊሲ ድጋፍ ነው ።
የአሜሪካ ባለስልጣናት ሰፊውን የኢቫንጀሊካን ክርስቲያን አማኝ ድምፅ ለማግኘት ለእስራኤል ያዳላ ኦና አረብና ሙስሊሞችን የሚጎዳ ፖሊሲ ይዘው ይቀሰቅሳሉ ።
ኢቫንጀሊካኖች ሙስሊሞችን ኢየሩሳሌምን የወረሩ ፀረክርስቲያኖች ናቸው ብለው ሲያምኑ እስራኤልን ደግሞ ቅዱሶችን ቦታዎች ለማስመለስ የምትታገል በእግዚአብሔር የተላከች ሀገር አድርገው ነው የሚስሉት ። የኢስላም ጥላቻ አሜሪካ ይህንን የበደል ድጋፍ እንድታደርግ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ቀዳሚው ነው ።
4 በአሜሪካ የሚኖሩ አይሁዳዊያን
በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ከ 7 ሚሊዮን በላይ አይሁዳዊያን ይኖራሉ ። እነዚህ አይሁዳዊያን ከ 100 አመታት በፊት ከአውሮፓ በተለይም ከጀርመን እና ከምስራቅ አውሮፓ ፈልሰው የሄዱ ናቸው ።
አይሁዳዊያኑ አሜሪካ ከገቡ በሗላ ማንነታቸውን ወደ አሜሪካዊነት ቀይረው ህብረተሰቡን በመቀላቀላቸው አሜሪካዊ ተደርገው ለመወሰድ ጊዜ አልፈጀባቸውም ። ከዚያም አልፎ እነርሱ አሜሪካ በምታደርጋቸው ጦርነቶች ውስጥ በቀዳሚነት በመሰለፍ የአሜሪካን ልብ ማሸነፍ ቻሉ ።
በአንደኛው የአለም ጦርነት ወቅት እንኳ ከ 500,000 በላይ አይሁዳዊያን በአሜሪካ ጦር ውስጥ ተሰልፈው ተዋግተዋል ። ያ ማለት ለጦርነት ብቁ አሆኑ አይሁዳዊያን ውስጥ አብዛኛው ጦርነቱን ተቀላቅሏል ። ይህም የአሜሪካን ልብ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል ።
ጠንካራ ማህበራዊ አደረጃጀት ያላቸው አይሁዳዊያኑ በፖለቲካው ዘርፍ ንቁ ተሳታፊ በመሆናቸው እጩ ተወዳዳሪዎች የነርሱን ድምፅ ለማግኘት ሲሉ የእነርሱን ፍላጎቶች በተለይ ከእስራኤል ጋር ተያይዞ ያለውን ለማስፈፀም በስፋት ይንቀሳቀሳሉ ።
አብዛኛው አይሁዳውያን የዲሞክራቶች ደጋፊ