ስለጋዛ አዳድስ መረጃዎችን ለማጋራት ያክል
፨ በዛሬው እለት እስራኤል ወደ ራፋህ ለመግባት ስትዋጋ ነው የዋለቺው ። በዚህም የራፋህ መግቢያ በርን ተቆጣጥራለች ። ሀማስም የመከላከል ጦርነት ሲያደርግ ነው የዋለው ።
ይሁን እንጅ አሜሪካ በሰጠቺው መግለጫ የራፋሁ ጦርነት ሙሉ ወረራ አይደለም የእስራኤል ጦርም ራፋህን ሙሉ ለሙሉ አይወርም የሚል ማስተባበያ ሰጥታለች ። እስራኤል በበኩሏ የራፋህ ጦርነቱን እያካሔድኩ ያለሁት በሀማስ ላይ ጫና ለማሳደርና ምርኮኞቹ እንዲለቀቁ ለማድረግ ነው የሚል መግለጫ ሰጥታለች ። የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንትም ከጦር ሜዳው ተገኝቶ ምርኮኞች የማይለቀቁ ከሆነ ራፋህን እስከ ጥግ እንዘልቃለን ብሏል።
👉 ጀርመንን ጨምሮ በርካታ የአለም ሀገራት እስራኤል የራፋህ ዘመቻዋን በአስቸኳይ እንድታቆም አሳስበዋል ። እስራኤል ከዚህ በተጨማሪ የእርዳታ ቁሳቁሶች ወደ ጋዛ እንዳይገቡ የምታደርገውን ክልከላ በአስቸኳይ እንድታቆም እናሳስባለን ስትል ጀርመን ገልፃለች ።
👉 የፍልስጤማውያን የድጋፍ ሰልፍ ከአረብ ሀገራት ውጭ በመላው አለም ተቀጣጥሎ ሲውል የምስራቅ አውሮፓዋ ግሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የፍልስጤም ድጋፍ ሰልፍን አስተናግዳለች ። በዋና ከተማዋ አቴንስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግሪካዊያን የፍልስጤምን ባንድራ ይዘው የወጡ ሲሆን የግሪክ ፖሊስ ሰልፈኞቹን በአስለቃሽ ጭስ ለመበተን ሲታገል ነው የዋለው።
ከዚያ ውጭ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመፅ ዛሬ የበርሊን ዩኒቨርስቲን ሲንጠው ነው የዋለው ። የጀርመን ፀጥታ ሀይሎች ሰልፈኞችን ለመበተን ቢጥሩም አልተሳካላቸውም ። በአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች የሚደረገው ተቃውሞም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው ። ከስዊድን እስከ ኖርዌይ የፍልስጤማውያን የድጋፍ ድምፅ እየተስተጋባ ይገኛል ።
👉 የሀማስም የእስራኤልም ተደራዳሪዎች ግብፅ ካይሮ ገብተዋል ። የ CIA ዋና ዳይሬክተርም ድርድሩን ለመከታተል ካይሮ ናቸው። ሀማስ " ኳሷ ያለቺው በእስራኤል እጅ" ነው ያለ ሲሆን ቤኒያማን ኔታኒያሁ የሚያደርገው የእብደት ድርጊት አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን ማረጋገጫ ነው ብሏል ።
አሜሪካ በበኩሏ ሀማስና እስራኤል ልዩነቱን አጥብበው ለስምምነት እንዲደርሱ አሳስባለች ። የሗይታውስ ቃልአቀባይ ጆን ኪርባይ ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ሁለቱም ወገኖች ወደ ድርድር መምጣታቸው ትልቅ እርምጃ ነው ያለ ሲሆን ልዩነቶች ጠበው የተኩስ አቁሙ እንደሚፈፀም ያለውን እምነት ገልጿል ።
👉 የአሜሪካ የኳታርና የግብፅ አደራዳሪዎች በአሁኑ ሰአት ሰፊ ውይይት እያደረጉ ሲሆን እዚያው ከሚገኙት ከሀማስና ከእስራኤል የልኡካን ቡድኖች ጋርም እየተነጋገሩ ይገኛሉ ።
አላህ ለፍልስጤማውያን የሚበጀውን ነገር ይምረጥላቸው !
t.me/Seidsocial