kaludo abdu Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

kaludo abdu shared a
Translation is not possible.

👉ዳሰሳ ጋዛ...

ሐማስ "አል አቅሳ ማዕበል" በሚል ስያሜ የጀመራው ወታደራዊ ዘመቻ በትላንትናው ዕለት 4ኛ ወሩ ላይ ደርሷል፡፡ በጦርነቱ መጀመሪያ ቀን ሐማስ እጅግ ያልተጠበቀ አስገራሚ ጥቃት በአስራኤል ወታደሮች እና ወታደራዊ ይዞታዎች እንዲሁም ህገ-ወጥ ሰፈራዎች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በአየር በምድር እና በባህር መፈፀሙን ተከትሎ በአንድ ቀን ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ጽዮናዊያንን ገድሏል ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩትን አቁስሏል፡፡

ከዘመቻው ጅማሮ በኋላ እስራኤል መጠነ ሰፊ ዘመቻ በሁሉም አማራጮች የጀመረች ሲሆን በተለይም በመኖሪያ ቤቶች ላይ የምትፈፅመው የአየር ላይ ጥቃት ንፁሃንን በእጅጉ የፈጀ ሆኗል በተጨማሪም አስፈላጊ ሰብአዊ ቁሳቁስ ወደ ጋዛ እንዳይገባ በማድረግ ሰብአዊ ቀውሱን እያባባሰችው ትገኛለች፡፡

በየመን ኢራቅ እና ሊባኖስ የሚገኙ ኢስላማዊ የተቃውሞ ቡድኖች የሐማስን ዘመቻ ተከትሎ የተናበበ ጥቃት በእስራኤል እና አጋሮቿ ላይ የጀመሩ ሲሆን ይህም የጦርነቱን አድማስ አስፍቶት እስራኤል እና አጋሮቿን ለበርካታ ጥቃት ተጋላጭ አድርጓቸዋል በተለይም በቀይ ባህር ላይ የንግድ መርከቦቻቸው እንዳይንቀሳቀሱ እና በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የጦር ሰፈሮቻቸው ላይ የማያባራ ጥቃት እንዲደርስባቸው ያደረገ ሲሆን በዚህም መርከቦቻቸው ሲቃጠሉ ወታደሮቻቸውም ሲገደሉ አይተናል፡፡

እስራል ሐማስን የማዳከምም ሆነ የማጥፋት ሀሳቧ የሚሳካ እንዳልሆነ እየታየ ሲሆን ሁሉም የፍልስጤም ተዋጊ ቡድኖች የእስራኤል ወታደሮችን ከቅርብ ርቀት በቀጥታ ኢላማ ሲያደርጉ የሚያሳ መረጃዎችን የፍልስጤም ተቃውሞ ቡድኖች ይፋ እያደረጉ ነው በዚህም እስካሁን 13000 በላይ የእስራል ወታደሮች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን 700000 ሺህ በላይ ጥምር ዜግነት ያላቸው እስራኤላዊያን ሀገራቸውን ለቀው ሸሽተዋል 500000 በላይ ሰፋሪዎችም ተፈናቅለዋል፡፡

ትላንት አዳሩን አሜሪካ በፈፀመችው ጥቃት የኢራቅ ኢስላማዊ ተቃውሞ (ከታኢብ ሂዝቦላህ) አዛዥ ሃጂ ሙጃሂድ አቡ ባቂር አል-ሳዲ እና አርካን አል-አላዊ ንዲሁም ሌሎች ባልደረቦቻቸው ሸሂድ ሆነዋል። ይህን ተከትሎ የኢራቅ ኢስላማዊ ተቃውሞ ደጋፊዎች በባግዳድ የሚገኘውን የአሜሪካን ኤምባሲ እንዲያውሩ የጠየቁ ሲሆን ወደ ባግዳድ አረንጓዴ ዞን (የአሜሪካ ኤምባስ) የሚወስዱ መንገዶች እና ኬላዎች በሙሉ ተዘግተዋል።

የአቡ ባቂር አል- ሳዲ ግድያን ተከትሎ አማን ንቅናቄ፣ አል ኑጃባ ንቅናቄ እና ከታኢብ ሂዝቦላህ በአሜሪካ ላይ ከባድ በቀል እንደሚኖር ዝተዋል፡፡

ለአምስተኛ ጊዜ በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ያደረጉት አንቶኒ ብሊንከን በአረብ ሀገራት የጠበቃቸው መስተንግዶ እንዳሰቡት ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ከጦርነቱ በፊት ለእስራኤለ እውቅና ለመስተት ተቃርባ የነበረችው ሳዑዲ አረቢያ እስራኤል ጦርነቱን አቁማ ከጋዛ ከፍልስጤም ግዛት እስክትወጣ ምስራቃዊ እየሩሳሌምን ዋና ከተማዋ ያደረገች ሀገረ ፍልስጠየም እስክትመሰረት ድረስ ከእስራኤል ጋር ምንም አይነት ድፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደማትጀምር ለብሊንከን ቁርጡን ተናግራለች፡፡

ጫና የበዛባቸው አንቶኒ ብሊንከንም ከማህሙድ አባስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ሀገራቸው የሁለት ሀገር መፍትሔን ለመተግበር እና ለጋዛ ሰብአዊ እርዳታ ቁርጠኛ ነን ብለዋል፡፡ ብሊንከን ከኔታንያሁ ጋር በነበራቸው ቆይታም ሓማስ ጥቅምት 7 የፈፀመው ድርጊትን አውግዘው እስራኤል በምላሹ የምታደርገውን ዘመቻም ኢ-ሰብአዊ ሲሉ ገልጸውታል ሐማስ ባቀረበው የእርቅ ሃሳብ ላይም መቀራረብ እንደሚኖር ተስፋ አልኝ ብለዋል፡፡

የአርጀንቲናው ቀኝ ዘመም ፓርቲ ምርጫ ማሸነፉን ተለከትሎ ፕሬዝዳንት ጃቪየር ሚሌይ የእስራኤልን ጉብኝት ሲጀምሩ አገራቸው ኤምባሲዋን ወደ እየሩሳሌም ለማዛወር ማቀዷን አስታውቀዋል ይህን ተከትሎ የፍልስጤም መንግስት እና ሌሎች በርካታ ሀጋራት ድርጊቱን አውግዘውታል።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group