#ልዩ_ልዩ_አጀንዳዎችና_ጣፋጭ_መልዕክቶች
#ክፍል_22
#ሐዲሥ 370 / 1835
አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ \"ሦስት ሰዎችን አላህ በዕለተ ቂያማ አያናግራቸውም። አያያቸውም። አያጠራቸውም። ለነርሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው። በበረሃማ መሬት ላይ ትርፍ ውሃ እያለው ለተጓዥ የከለከለ፣ ከዐስር ሶላት በኋላ ሸቀጡን የሸጠና ለገዥ በዚህ ዋጋ ነው የሸጥኩልህ በማለት በአላህ የማለ፣ ገዥውም አምኖ የተጠየቀውን ዋጋ የከፈለው፣ የተዋዋሉት ግን በዚያ እርሱ ባለው ዋጋ ያልሆነ፣ እንዲሁም አንድን የሙስሊም መሪ ለዓለማዊ ጥቅም ሲል፥ ማለትም ዓለማዊ ጥቅም ከሰጠው ቃል ኪዳኑን ሊሞላ ካልሰጠው ግን ሊያፈርስ በማሰብ ቃል የተጋባ።\" (ቡኻሪና ሙስሊም)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ እነዚህ ተግባራት እኩይ ናቸው። ከታላላቅ ወንጀሎችም ይፈረጃሉ። የመጀመሪያው የሰውን ልጅ ስቃይ አለመጋራት ነው። በበረሃማ ቦታ ውስጥ ትርፍ ዋሃ እያለ በጉዞ ላይ ለሆነና ውሃው በጣም ለሚያስፈልገው ሰው ለመስጠት አለመፍቀድ ግዙፍ የጭካኔና ለሰው ስቃይ ደንታ ቢስ የመሆን ተግባር ነው።
2/ ሁለተኛ የአላህን ስም የሸቀጡ ማሻሻጫ ማድረጉ ሳያንስ በሐሰት መማሉ ሌላ ጥፋት ነው። ለዚያውም መላኢኮች በሚሰበሰቡበትና በሚተካኩበት ከዐስር በኋላ ባለ የተከበረ ወቅት። በእርግጥ ሽያጭ ላይ የሐሰት መሐላ በየትኛውም ጊዜ ቢሆን የከበደ ወንጀል ነው።
3/ ሦስተኛው የሙስሊሞችን መሪ ማታለል ነውና ከሚያደርሰው ማኅበራዊና ፖለቲካው ቀውስ አንጻር ከፍተኛ ጥፋት ተደርጓል።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1