anwar anwar Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

anwar anwar shared a
Translation is not possible.

ትላልቅ መሰናክሎችን አትፍራ። ምክንያቱም  ከእነዛ ትላልቅ መሰናክሎች በስተጀርባ ትላልቅ ድሎች ይኖራሉና። ድሎቹን ለመጎናፀፍ ከፈለክ በአሏህ ታገዝ ቀጣዩ የአንተ ጥንካሬና ጥረት ነው።

         

Send as a message
Share on my page
Share in the group
anwar anwar shared a
Translation is not possible.

የእስራኤል ጦር የእዝ ሰንሰለቱ እየተበጣጠሰበት ይገኛል ። ይህም በመሆኑ የሎጀስቲክ እና የመሳሪያ አቅርቦቱ እየተቆራረጠ የእስራኤልን ጦር እንደፈለገ ማጥቃት እንዳይችል አስችሎታል !

ይህንን የእዝ መበጣጠስና የመሳሪያ እጥረት ለመፍታት እስራኤል ከላይ በአይሮፕላን የጦር መሳሪያ ለወታደሮቿ እያዘነበች ትገኛለች ። እስራኤል እንደዚህ አይነት ነገር ስታደርግ ከሂዝቡላህ ጦርነት በሗላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው !

እስራኤል እንደገለፀቺው ከሆነ እስካሁን 7 ቶን የጦር መሳሪያ ከአየር ላይ አውርዳለች ። ጦር መሳሪያው በፓራሹት ተደርጎ ወደምድር ይላክና መሬት ላይ ሲወድቅ ወታደሮቹ አንስተው እንዲጠቀሙት ነው ። እስራኤል ይህ ለማድረግ የተገደደቺው ጦሯ በሀማስ ጥቃት ለመንቀሳቀስና መሳሪያ ለማጓጓዝ ስለቸገረው ነው ። በርካታ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎቿ በሀማስ የወደሙባት እስራኤል በአየር መጣልን አማራጭ አድርጋዋለች ።

በሌላ በኩል ዛሬ ሀማስ በእስራኤል ጦር ላይ በከፈተው ከፍተኛ የመልሶ ማጥቃት የእስራኤል ጦር ከአልቀሳኢብ ሸሽቶ ወጥቷል ። የእስራኤል ጦር ወደሗላ ሲያፈገፍግም ሀማስ መሳሪያዎችንና መረጃዎችን ማግኘት ችሏል ።

እስራኤል ዛሬ እንደገለፀቺው ሀማስ በፈፀመው ወጥመዳዊ ጥቃት ሰባት ወታደሮቿን ማጣቷን ገልፃለች ። እስራኤል የምትጠቅሰው ቁጥር ከእውነተኛው ቁጥር በጣም ያነሰ መሆኑን ልብ ይሏል !!!

እስራኤል ወደ ጋዛ ስትገባ ሀማስ የምድር ውስጥ ዋሻዎቱ ውስጥ ተሸሽጎ የሚዋጋት መስሏት ነበረ ። እናም የዋሻ ውጊያ ለማድረግ አቅዳ ነበር የሄደቺው ። ግና የጠበቃት ሌላ ነው !

ሀማስ በዋሻ እየተሹለከለከ የሚዋጋ ሳይሆን ፊት ለፊት እየጠበቀ ወታደራዊ ኢላማዎቿን እያደባየ የሚዋጋ ትልቅ አቅምና የመዋጋት ሞራልን የታጠቀ መሆኑ እስራኤልን ብቻ ሳይሆን አባቷን አሜሪካን ጭምር አስደንግጧል ። ለዚህም አሜሪካ እስራኤልን እስከ መጪው ጥር ወር ድረስ የግደታ ጦርነቱን ማጠናቀቀ አለብሽ የሚል ግዴታን በእስራኤል ላይ መጣሏን New york times ያወጣው መረጃ ያሳያል።

እስራኤል እንኳንስ የዋሻ ውስጥ ውጊያ ልታካሒድ ይቅርና ዋሻዎቹን መቅረብ ራሱ ፈርታለች ። እስራኤል ዋሻዎቹን ለመቅረብ የሞከረቺው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ። አንዴ በወታደራዊ መሀንድሶችና በምሽግ ቴክኒሺያኖች ጭምር የታገዘ ወደ ዋሻዎቹ የመግባት ሙከራ አድርጋ ውጤቱም ለመግባት የሞከሩት ወታደሮቿ በቅፅበት ማለቃቸው ሆኗል ። ለሁለተኛ ጊዜ ታጋች ወታደሮቿን ለማስለቀቅ በሚል ያደረገቺው የመግባት ሙከራም ሰባቱን ወታደሮቿን ጨምሮ ታጋች ወታደሮቿን ካስጨረሰባት በሗላ ዳግመኛ ለመሞከር የነበራት ሞራል ተንከሽክሾ ፍርሀትን ለቆባታል ።

እናም ያላት አማራጭ ከሰማይ ቦንቦችን ማዝነብ ነው ። ግና ይህ የፍልስጤም ህፃናትን ይጨረስ እንደሆን እንጅ አሸናፊያ ሊያደርጋት እንደማይችል እሙን ነው ።

አረቦች እስራኤልን ይፈራሉ እስራኤል ደግሞ ሀማስን ትፈራለች !!

ድልም የሙጃሂዶች ይሆናይሆናል!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
anwar anwar shared a
Translation is not possible.

1, ረሱል ﷺ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች እየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ ﷺ አቡበክርንረ.ዐ "ያ አቡበከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት።

አቡበክርም ረ.ዐ "3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.ከአንቱን ጋር መቀመጥ፣

2.አንቱን ማየት፣

3.አንቱ ባዘዙዋቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ።

°

ዑመርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?"

"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ

1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣

2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣

3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ።

°

ዑስማንን ረ.ዐ ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን?

በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.ሰዎችን ማብላት፣

2.ሰላምታን ማብዛት፣

3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣

°

አልይን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?"

"በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.እንግዳን ማክበር፣

2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣

3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣

°

አባ ዘርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?"

"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :-

1.እርሃብን እወዳለሁ፣

2.በሽታን እወዳለሁ፣

3.ሞትን እወዳለሁ፣

ነብዩም ﷺ "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?"

አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣

በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣

ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ።

°

ነብዩ ﷺ " እኔም በዱኒያ ላይ

3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.ሽቶን እወዳለሁ፣

2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣

3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣

በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል አ.ሰ.ወ ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ

"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ

ነብዩም ﷺ "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት።

1.መልዕክትን ማድረስ፣

2. አማናን አደራን መጠበቅ፣

3.ሚስኪኖችን መውደድ፣

ጅብሪል አ.ሰ.ወ ተመልሶ ወደ ከሄደ በኋላ ረሱልና ﷺ ሱሃቦቻቸው ረዲየሏሁ አጅመኢን ከመቀመጫቸው ሳይነሱ

ተመልሶ መጣና አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:-

"አላህም ሱ.ወ. ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም ሱ.ወ እንዲህ ብሏል:-

በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣

2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣

3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ።

አላህ ሱ.ወ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ﷺ ሱሃቦች ረ.ዐ.አ የወደዱትን ያስወድደን!

°

ይህን ጣፋጭ ሐዲስ በማንበባችሁ ከፍ ያለ አጅር ታገኛላችሁ -ኢንሻ አሏህ።

ሼር በማድረግ ለሌሎች ብታካፍሉ ግን እነሱ ባነበቡት ልክ ለናንተም ሀሰናት ይፃፍላችኋል!

ኢንሻ አሏህ!!

አላህ አንብበው ከመጠቀሙት ያድርገን!!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group