sada ali shared a
Translation is not possible.

ዋዛ እና ቁምነገር

~

አልሙጊራህ ብኑ ዐብዲረሕማን ብኒ ሂሻም በቁስጠንጢኒያ ዘመቻ ላይ አንድ አይኑን ያጣል። ሙጊራህ በየደረሰበት ምግብ የሚያበላ ሰው ነበር። አንዴ እንደተለመደው ምግብ ደግሶ በቀረበበት አንድ አዕራቢይ መጣ። ሰውየው ምግቡን መብላቱን ጥሎ ሙጊራን በረጅሙ ትክ ብሎ ያየው ያዘ።

ሙጊራህ፡ "ምን ሆነሃል አዕራቢው?" አለው።

አዕራቢዩ፡ "የምግብህ ብዛት ይገርመኛል። አይንህ ግን አጠራጥሮኛል።"

ሙጊራህ፡ "ምንድነው ያጠራጠረህ?"

አዕራቢዩ፡ "ምግብ የምታበላ አንድ አይና ሆነህ እያየሁህ ነው። ይሄ የደጃል ምልክት ነው።"

ሙጊራህ፡ "ብላ ይልቅ አዕራቢው! ደጃል በአላህ መንገድ በመዝመት አይኑን አያጣም።"

📗 [ጀምዑል ጀዋሂር ፊልሙለሒ ወነዋዲር ]

እኛ ብንሆን አክብረን የጋበዝነው ሰው እንዲህ አይነት ነገር ቢያነሳብን በምን መልኩ እናስተናግደዋለን?

=

የቴሌግራም ቻናል፡-

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group