UMMA TOKEN INVESTOR

sid Hmdale Hmdale Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የሙእታህ ዘመቻ🌴| ይነበብ‼️

🍁🍁🍁🍁🍁🍁

በስምንተኛው አመተ ሂጅራ፡ በጁማደል አወል ወር ረሱል ﷺ ወደ ቡስራ አሚር የላኩትን መልዕክተኛቸው ሀሪስ ኢብኑ ዑመይርን የገደሉ ሰዎችን ለመበቀል ጦርን አዘጋጁ።

ረሱል ﷺ ዘይድ ኢብኑ ሀሪሳህ የጦሩ አሚር እንዲሆን፡ እሱ ከተገደለ ደግሞ ጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ፡ እሱ ከተገደለ ደግሞ ዐብደሏህ ኢብኑ ረዋሀ አሚር እንዲሆን አዘው፡ በአሏህ ስም ዝመቱ፡ የአሏህንና የናንተን ጠላቶችን ተፋለሙ ብለው ሸኙዋቸው።

ሙእሚኖች ሀሪስ ኢብኑ ዑመይር የተገደለበት ሙእታህ የተባለው ቦታ ሲደርሱ፡ ሩሞች እጅግ ብዙ ጦር አዘግጅተው ጠበቋቸው።

የሙስሊሙ ጦር 3,000 የነበረ ሲሆን የኩፋሮች ቁጥር 200,000 በአንዳንድ ዘገባ ደግሞ 150,000 ነበር።

በዚህ ወቅት ሶሀቦችም ወደ ረሱል ﷺ ተጨማሪ ጦር እንዲልኩ ሰው እንላክ? ወይስ በዚሁ ሁኔታ ቀጥታ ወደ ፍልሚያው እንግባ? በሚለው ጉዳይ ሲወያዩ ዐብደሏህ ኢብኑ ረዋሀ እንዲህ አለ፡

ህዝቦቼ ሆይ! ይህ የምትጠሉት ነገር'ኮ የወጣችሁለት ጉዳይ እኮ ነው። ሸሂድነት ፈልጋችሁ እኮ ነው የወጣችሁት። እኛ እኮ ያ ከፍ ያለው አሏህ ባተለቀን ዲን እንጂ ጠላቶቻችን' ኮ በጦር በዝግጅት፡ በጉልበት ወይም በሰራዊት ብዛት አንጋደልም፡ ደግሞም ጉዳዩ ከሁለት መልካም ነገሮች አንዱ ቢሆን እንጂ ሌላ አይደለም። ወይ አሸንፎ የበላይ መሆን፡ ወይም በአሏህ መንገድ ሸሂድ መሆን አላቸው🌴

ሶሀባዎችም ወሏሂ ኢብኑ ረዋሀ ትክክል ብሏል ብለው ወደ ፍልሚያው ገቡ።

ከባድ የሆነ ፍልሚያን ተፋልመው፡ ባንዲራ የያዘው አሚራቸው ዘይድ ኢብኑ ሀሪሳህ ሸሂድ ሆነ።

ከዛም ጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ ባንዲራውን ይዞ ሸሂድ እስኪሆን ድረስ ብርቱ ፍልሚያን ተፋለመ።

እሱ ሲገደል ደግሞ ዐብደሏህ ኢብኑ ረዋሀ ባንዲራውን ይዞ ሸሂድ እስኪሆን ድረስ ከባድ ፍልሚያን ተፋለመ።

ዐብደሏህ ኢብኑ ረዋሀ ሲገደል ግን ከፊል ሶሀባዎች ወደ ኋላ ለመመለስ አሰቡ።

ከዛስ?

ኢንሻላህ ቀጣዩና ስለ ሙእታህ ዘመቻ የመጨረሻው ክፍል፡ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ ሰይፉሏህ የተሰየመበትን ክስተት በአሏህ ፈቃድ በቀጣይ አቀርባለሁ።

ታሪካችን እንወቅ፡ ለልጆቻችን እናስተምር፡ እንደ ቀደምቶቻችን መሆን ባንችል እንኳ ለመመሳሰል እንሞክር።

✍ወንድማችሁ ዩኑስ ሀሰን አብራር ሙሀመድ።

٢٠ ربيع الأخر ١٤٤٥.

https://t.me/abufurat

https://ummalife.com/YunusHassen

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የፈለስጢንና እስራኤልን ጉዳይ በተመለከተ ስላለው እውነታና እኛ እንደ ሙስሊም ማድረግ ስላለብን ነገሮች ሸይኽ Ilyas Ahmed ትናንት እሁድ በኢማሙ አሕመድ መስጅድ በነበረው የፈታዋ ፕሮግራም ላይ ያስተላለፈው ሰፊ መልዕክት‼

ከግንዛቤ ፈጠራ ጀምሮ ብዙ ቁም ነገሮች ስላሉት ብታዳምጡትና ነገሩን ከስር መሠረቱ ለማያውቁ ይጠቅም ዘንድ ብታሰራጩት መልካም ነው።

©: Video Credit: Huda Multimedia

የቪድዮው ሳይዝ ለበዛባችሁ በድምፅ ብቻ ለማዳመጥ ከፈለጋችሁ!

https://t.me/MuradTadesse/32501

||

https://ummalife.com/MuradTadesse

t.me/MuradTadesse

59 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
sid Hmdale Hmdale Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group