abdurehman sherif Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ئەم لاوازبوونەی ئەبو عوبەیدە تەبیعییە، ئەمە سوونەتی جیهادی ئەم ئوممەتە بووە لەبەری هەتا دوای..ئەسحاب لەڕێی جیهادا هەبووە کە گەڵا و گیایان خواردە، تەنانەت ئەفەرموون کە وەک پیسی ئاژەڵ، پیسییان داناوە لەتاو گەڵا و گیا خواردنی زۆر، خەفەتیشی ناوێ چونکە ئەمە ڕێیەکە و خۆی هەڵیبژاردووە وە بەدڵنیاییەوە خوا جێینەهێشتوون کە ئێمە وا لەدوورۆ ئەیانبینین

حزووری سەکینەتی ئیلاهی، شتێکە لای ئێمەوە دەرناکەوێ

ئەوان گوناح نین، ئێمە گوناحین ڕسوا و ڕووڕەش

خەم بۆ ئێمەیە نەک ئەوان، خەمە گەورەکەش ئەوەیە زەلام لەدووڕەوە بە سکی تێر و چاوی ئاوساوی زۆر خەوییەوە قسەی زل بکا و بڵێ بۆ واناکەن و بۆ ئاواکەن؟ ئەمە چییە تەنازول ئەکەن لە فڵان و فڵان شتا؟...کورە تەریق بەرۆۆ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🚢በቀይባህር ዉስጥ የሚዋኙት የመኖች ብቻ ናቸው!

‼️ የየመን ሁቲዎች ነገር

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

.

#የአቅል_አይምሮ_ትዝብት_ለrn05

.

እንዴት አላችሁት ጃል?! ዛሬ ደግሞ እስኪ ትንሽ ስለ የመን ሁቲዎችና የቀይባህር ጉዳይ ትዝብቴን ላዉጋችሁ!

.

የጋዛ ጦርነት ከተነሳ ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ሀገረመንግስታት እስራኤል የምትወስደው በጅምላ ህዝብን የመግደልና የማጥፋት ዘመቻ እንዳላስደሰታቸው ተናግረዋል! እንደ አሜሪካ ያሉና ጥቂት ሃያላን ሃገሮች ደግሞ እስራኤልን “አበጀሽ!” ብቻ ሳይሆን የገንዘብ የጦርና የሞራል ድጋፍ በግልጽ ሲሰጡ ተስተዉለዋል፡፡ የአለም ህዝብ ግን በአብዛኛው የሚያየዉና የሚሰማው ነገር እንዳላስደሰተው በየቀኑ እየወጣ ቢገልጽም ገንዘቡና ሃይሉ ያለው በመንግስታቱ እጅ በመሆኑ የሚሆነዉን ከመጥላት በቀር ሊያስቀረው አልቻለም፡፡

.

ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው የተባሉት የአረብና የሙስሊም ሃገራት ደግሞ ሽምግልና ከመቀመጥ እስራኤልን ከመኮነን በቀር እስራኤል ፍጅቷን አላቆምም ካለች በነሱ በኩል ሊደርስባት የሚችል ነገር ስለመኖሩ እንኳን በድርጊት በቃላትም ደረጃ ሲናገሩ አይሰማም፡፡ አንድ ሰሞን ያዙኝ ልቀቁኝ ስትል የነበረችው ቱርክ ኢንኳ ሌላው ቢቀር ከአዘርባዝጃን ተነስቶ ድንበሯን አቋርጦ ወደ እስራኤል የሚገባዉን የነዳጅ መስመር ለማስቆም ቀርቶ ስሙንም እንደማስፈራራያ እንኳ ስታነሳ አይሰማም፡፡

.

በአሁኑ ሰአት ከሌሎች አረብ ሃገራት የተሻለች ነች የምትባለው የአረብ ኢሜሬትስም ጉዳይ ቢሆን በተለይ የእስራኤል ታጋቾችን የማስለቀቅ ሚና እየተጫወተች ሲሆን በምትኩ ደግሞ ጦርነቱ እንዲቆም ሳይሆን እስራኤል በፈቀደችው ልክ ፍልስጤማዊያን ከመገደላቸው በፊት ዉሃ እንዲጎነጩ የማድረጉን ስራ የአለማችን ትልቁ የዲፕሎማሲ ስራ አድርጋው ከዛ ያለፈ ነገር ካልተደረገ ሽምግልናዉን አላካሂድም የሚል ማሳሰብያ እንኳን ስትሰጥ አይሰማም፡፡

.

ከዚህ ሁሉ በተለየ መልኩ ድሃይቱና በማእቀብ የምትንገላታው ከሳዉዲ ጋር ከተደረገው ጦርነት ገና ያላገገመችው የመን እስራኤል ጦርነቱን ታቆም ዘንድ በእጅዋ ያለዉንና ልታደርግ የምትችለዉን ነገር በመገምገም በአለማቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የንግድ መሥመር የሆነዉን የቀይ ባህርን መስመር በመዝጋት “ጋዛዊያን ላይ የሚደረገው የቦምብ ናዳ ካልቆመ በቀር አንድም መርከብ እኔን አቋርጦ ወደ እስራኤል አያልፍም” በማለት የወሰደችው ተግባራዊ እርምጃ ያልተጠበቀና እጅግ ያነጋገረ ሆኗል፡፡

.

ይህ የፍልስጤም ህዝብን በመደገፍ እየተወሰደ ያለው የየመን ሁቲዎች ድርጊት በእስራኤል እና በአለም አቀፍ ንግድ ላይ ትልቅ ተጽእኖ እያሳደረ ነው። በቀይ ባህር ውስጥ ቢያንስ 12 የንግድ መርከቦች ኢላማ ተደርገዋል ፣በዚህም ቢያንስ 44 ሀገራት ተነክተዋል። የዓለማችን ቀዳሚዎቹ አምስት ዋና ዋና የመርከብ ኩባንያዎች በየመን ሁቲዎች ጥቃቶች ምክንያት በቀይ ባህር በኩል የመርከብ ጉዞን ላለማድረግ እንደተገደዱ ያሳወቁ ሲሆን የብሪታንያ የነዳጅ ዘይት ኩባንያዎች BP በከፍተኛ ሁኔታ የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ እንደሚጨምር አሳውቋል፣ይህም እንደተሰማ ሰሞኑን የእንግሊዙ ጠ/ሚር ከመስመራቸው ወጥተው የጋዛው ጦርነት መቆም ያለበት ስለመሆኑ ሳይወዱ በግድ እንዲተነፍሱ ተገደዋል።

.

እስካሁን በየመን ሁቲዎች የመርከቦች ጥቃት ሰበብ የተጎዳ ሰው የለም ያም ሆኖ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በቀይ ባህር በኩል ወደ እስራኤል ወደብ የሚደረጉ የንግድ መርከቦችን ጉዞ ዘግተዋል። በአሁኑ ሰአት ከእስያ ወደ እስራኤል የሚመጡ የንግድ መርከቦች እጅግ ረዥምና ዉድ የሆነን መስመር በመከተል አፍሪካን ለመዞር ተገደዋል፣ ይህም ጉዟቸዉን በሶስት ሳምንታት አራዝሞታል፣ ወጪዎቻቸዉንም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። በቀይ ባህር በኩል አቋርጠው ይጓዙ ለነበሩ የእስራኤል የንግድ መርከቦች አሁን አፍሪካን መዞር ግድ ስለሚላቸው የኢንሹራንስ ወጪያቸው ብቻ እስከ 250 በመቶ ጨምሯል።

.

ለዚህም ምላሽ ዩኤስ አሜሪካ አዲስ የባህር ጥበቃ ጥምረት ሃይል ማቋቋሟን አስታውቃለች። ጥምረቱ በአሜሪካ የሚመራ ሲሆን ሌሎች ዘጠኝ ሀገራትን ያቀፈ ነው ። ያም ሆኖ እንደ ስፔን ጣልያንና ፈረንሳይ ያሉ የህብረቱ አባላት “እኛ የምንጠብቀው የሃገራችንና የአዉሮፓ ንብረት የሆኑ መርከቦችን ብቻ ነው” ማለታቸው አሜሪካንንም ሆነ እስራኤልን ያላስደሰተ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ ተጨማሪ የጥበቃ መርከቦችን እንዲልኩ በአሜሪካ ከታዘዘት መሃል ኖርዎይና ሆላንድን የመሳሰሉ ሀገራት ያንን እንደማይፈጽሙ መግለጻቸው ሌላው ያልተጠበቀ ምላሽ ሆኗል፡፡

.

ያም ሆነ ይህ ሁቲዎች ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ አሜሪካን በሰየመችው የጥበቃ ቡድን ሰበብ በምንም መልኩ ተስፋ እንዳልቆረጡ እና አሜሪካ መላዉን አለም ማስተባበር ብትችል እንኳ እስራኤልና አሜሪካ በጋዛ ላይ የጀመሩትን ጦርነት ሙሉ ለሙሉ እስካላቆሙና ጋዛዊያን እርዳታ ማግኘት እስካልጀመሩ ድረስ በቀይ ባህር መስመር በኩል ወደ እስራኤል የሚያመሩ ማንኛቸዉንም መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸማቸዉን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ።

.

ይህም በመሆኑ የነገን ባናውቅም ለዛሬው ማንኛዉም አካል የመን ሳትፈቅድለት ቀይ ባህር ዉስጥ መዋኘት አይችልም! ለጊዜው ቀይባህር ዉስጥ እንዳሻቸው መዋኘት የሚችሉት የመኒዎች ብቻ ናቸዉና!!

.

ሌላው ጥያቄ ከየመን በላይ አቅም ያላቸው ሃገራት ለመሆኑ እስራኤልን የሚያስፈራሩበት ምንም ነገር የላቸዉምን? የሚለው ነው!!

.

ይሄው ነው!

image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🇱🇧 ከሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ነስረላህ የተመረጡ ንግግሮቹ

ክፍል ሁለት

❝ለጠላት እንነግረዋለን የጦርነቱ መጨረሻ የጋዛ ድል ነው።❞

❝ምዕራባውያን ዲሞክራሲያዊ ሀገር እንደ ጎረቤት እንዳለን ሊነግሩን ይሞክሩ ነበር ግን እውነታው ታየ ውሸታቸውም ተጋለጠ።❞

❝የኛን አረብ እና ኢስላማዊ ህዝቦች ከነዚህ አረመኔ ፅዮናውያን መንግስቶች ጋር ኖርማላይዝ እንድናደርግ ሊያታልሉን ይፈልጋሉ ነገር ግን የኛ ህዝብ መቼም ቢሆን የሚታለል አይደለም።❞

❝እኛ ጦርነቱን ከኦክቶበር 8 ጀምሮ ተቀላቅለናል።❞

❝እኛ ለአሜሪካ መርከቦች ዝግጅታችንን አድርገናል። አሜሪካን 🇦🇫 የአፍጋኒስታን ፤ 🇮🇶 የኢራቅ ፤ 🇸🇾 የሶሪያ እና 🇱🇧 የሊባኖስ ሽንፈቶቿን እንድታስታውስ እንላለን።❞

❝አሜሪካዎች እኛ (በዚህ) ከቀጠልን ኢራንን እናፈነዳታለን የሚል መልዕክት ልከውልናል። እንዴት ብትደፍሩ ነው የኛን ትግል የምታስፈራሩት??? በሜዲትራንያን ያሉ መርከቦቻችሁ አያስፈሩንም እና እርግጠኛ ሁኑ ለነሱ ዝግጅታችንን አድርገናል።❞

❝ለአሜሪካኖች አረጋግጥላቸዋለው ምናልባት አካባቢያዊ ጦርነት ከተነሳ የነሱ መርከቦች እና የአየር ሀይላቸው ከባድ ክፍያ ነው የሚከፍሉት።❞

❝ጋዛ አሸናፊ እንድትሆን ልንሰራ ይገባል። በጋዛ ያሉ ታጋዮች አሸናፊ እንዲሆኑ ልንሰራ ይገባል።❞ 

❝በጋዛ ፤ በዌስት ባንክ እና በሁሉም ቦታ ጭቆና ውስጥ ላሉ ህዝቦቻችን ያ ትዕግስት ክፍያው ድል ነው እላቸዋለሁ።❞

❝እኛ ‟አላህ አማኞችን ባለድል እንደሚያደርጋቸው ቃል በገባው” ላይ እምነት አለን። አላህ ሁሌም ቃል የገባውን ፈፃሚ ነው።❞

https://www.youtube.com/@QisaTube1

Facebook - ቂሳ ትዩብ Qisa Tube

Telegram - t.me/QisaTube

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከኮሎምቢያ ቀጥላ ሌላዋ የላቲን አሜሪካ አገር ቦሊቪያ ከእስራኤል ጋር ያላትን የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ማቋረጧን አሳውቃለች

የቦሊቪያ ፕሬዚዳንት ሉዊስ አርሲ እንዳሉት በዘር ማጥፋት ወንጀል በደም ከተጨማለቀች ሀገር እስራኤል ጋር ያለን ግኑኝነት አብቅቷል ሌሎች ሀገራትም ተመሳሳይ እርምጃ ይወስዱ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል

አስቡት እንግዲ ግንኙነታቸውን እያቋረጡ የሉት የካፊር ሀገራት ናቸው. ይገርማል የኛዎቹስ የት ናቸው??? ለምን ከዝምታ የዘለለ ነገር አያደርጉም!!😏😏😏

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group