UMMA TOKEN INVESTOR

mez mame shared a
Translation is not possible.
ለመጅሊስ መሪነት ማንን እንምረጥ?
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
በአሕመዲን ጀበል
💢💢💢💢💢💢
ሕዝበ ሙስሊሙ የመሪ ተቋሙ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ምርጫ ላይ ይሆነኛል የሚለውን አካል በነጻነት መምረጥ ለድርድር የማይቀርብ መብቱ መሆኑ እሙን ነው። በዚህ ረገድ የሚመርጣቸው አካላት ምን እንዲያደርጉለት ይፈልጋል? የሚመርጣቸውስ ለምን ዓላማ ነው?
ሊመርጣቸው ያሰባቸው አካላትስ ያንን የሚያልመውን ዓላማውን እውን ማሳካት ይችላሉ ወይ? የሚለውን በአግባቢ ማየትና መለየት እጅግ ወሳኝ ይሆናል። ምክንያቱን መጅሊስንም ሆነ መሪዎቹ የሚፈለጉት የሕዝቡ ወኪል አገልጋይ ሆነውለት ከተቋሙ ሕዝበ ሙስሊሙ የሚፈልጋቸውን አገልግሎቶቹ በተገቢው መልኩ እንዲሰጡ ነውና። በመሆኑም መራጮች ይሆኑኛል የሚሉትን አካላት ሲመርጡ አልያም ለመመረጥ ያሰቡ ተመራጮችም ራሳቸውን ለቦታው ሲያጩ ስለተቋሙ ምንነት፥ የሕዝበ ሙስሊሙን ፍላጎት፥ስለሚጠበቅባቸው ሚና እንዲሁም የራሳቸውን አቅምና ብቃት ከግምት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
በዚህ ጽሑፍ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤትን ምንነትና ሚናን ስለመጅሊስ በቂ ግንዛቤ ለሌላቸው ለማስገንዘብ ፥ግንዛቤው ላላቸው ደግሞ ለማስታወስ እሞክራለሁ።ይህም የመጅሊስን ራዕይ፥ ተልዕኮ፥ ግቦች፥ ዓላማዎችና ተግባራትን በማብራራት ይሆናል። መልካም ንባብ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች(መጅሊስ) ራዕይ
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥
በሀገሪቱ ውስጥ በእስልምና መርሆች ላይ የተመሰረተ እና ለፍትህ፣ ለልማት እና ለአንድነት ቁርጠኛ የሆነ ሰላማዊ፣ ሁሉን ዓቀፍ እና በሃይማኖቱ የበለጸገ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ።
የመጅሊስ ተልዕኮ
🏀🏀🏀🏀🏀
በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኘውን ሙስሊም ማህበረሰብ ኢስላማዊ አስተምህሮዎችን በማስፋፋት ፣የሃይማኖት መብቶችን በማስጠበቅ፣የማህበረሰብን ተጠቃሚነት በማጎልበት ለሀገሪቱ ሃይማኖታዊ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት የመሪነት ሚናውን መወጣት።
የመጅሊስ ግቦች
🔮🔮🔮🔮🔮
1. የሃይማኖት ነፃነት እና እኩልነት በማስጠበቅ ከትንኮሳና ከአድሎ የራቀ ሰላማዊና የተረጋጋ ሕይወት ለሕዝበ ሙስሊሙ እውን እንዲሆን ማድረግ።
2. በመላው ኢትዮጵያ ኢስላማዊ ትምህርቶችን እና እሴቶችን ማሳደግ።
3. በሙስሊሞች መካከል አንድነት እና ትብብርን ማጠናከር።
4. የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ።
5. የሕዝበ ሙስሊሙን ፍላጎት በብቃት ለመፍታት እንዲያስችል ተቋማዊ አቅምን ቀጣይነት ባለው መልኩ መገንባት።
የመጅሊስ ዓላማዎች
🌺🌺🌺🌺🌺🌺
1. ለሙስሊሞች መብቶች መከበር መቆም
🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅🍅
የህብረተሰቡን ሃይማኖታዊ እና ህዝባዊ ጥያቄዎችን ለመፍታት ከመንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ መስራት።
2. ትምህርት እና ግንዛቤ
📀📀📀📀📀📀📀📀
የኢስላማዊ ትምህርት ተደራሽነትን ለማሻሻል ኢስላማዊ ትምህርት ቤቶችን እና ማዕከላትን ማቋቋም፥ያሉትን ማጠናከር እና መደገፍ።
3. አንድነት እና ትብብርን ማጠንከር
🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁
በሙስሊሞች መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር በማህበረሰቡ መካከል ውይይቶችን እና ዝግጅቶችን ማድረግ።
4. የበጎ አድራጎት ድርጊቶችንና ተቋማትን ማስተባበር
📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶
የተቸገሩና ተጋላጭ የሆኑ ሙስሊሞችን ለመርዳት ተነሳሽነቶችን ማዘጋጀት።
5. ተቋማዊ ልማት
🆙🆙🆙🆙🆙
የአቅም ግንባታና የቴክኖሎጂ ትግበራ በማድረግ የምክር ቤቱን የአሰራር ቅልጥፍና ማሻሻል።
የመጅሊስ ስትራቴጂዎች
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
1. በሃይማኖታዊ፥ ማህበራዊ፥ኢኮኖሚያዊና ሀገራዊ ጉዳዮች የሕዝበ ሙስሊሙን ተሳትፎ የሚያጎለብቱ ዉጥኖችን ቀርጾ ንቅናቄን ማድረግ።
2. በሃይማኖታዊና ዓለማዊ የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ ሙስሊሞች በስፋት እንዲሳተፉ በማድረግ።
3. የመጅሊስ መዋቅርንና ሌሎች ኢስላማዊ ተቋማትን በሁለንተናዊ መልኩ የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄዎች መመለስ እንዲችሉና ፍላጎት ማሟላት በሚችሉበት ቁመና ላይ እንዲገኙ ማጠናከር።
4. ሕዝበ ሙስሊሙ ከድህነት፥ ችግርና ችጋር፥ ኋላ ቀርነትና መሃይምነት የተላቀቀ የተሻለ ሕይወት መኖር እንዲያስችለው የሙስሊሞችን ኢኮኖሚያዊ አቅምና ደረጃን ማጎልበት።
5. በሀገሪቱ ሙስሊሞች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ ያሉ አደናቃፊና ችግር ፈጣሪ የሆኑ ፖሊሲዎች፥ሕጎችና አሰራሮች እንዲለወጡ መስራት።
የመጅሊስ ተግባራት
🍀🍀🍀🍀🍀🍀
1. በኢትዮጵያ ዉስጥ የሃይማኖት ጉዳዮችን በየእርከኑ በተገቢው መልኩ መምራት።
2. የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ፍላጎትና መብት ማስጠበቅን ዓላማ ባደረገ መልኩ በሀገር ዉስጥም ሆነ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሙስሊሞችን መወከል።
3. በዘወትር የሚደረጉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በተገበው መልኩ ማስተዳደር።
4. የሙስሊሞችን መብቶችና ጥቅሞችን ማስጠበቅ።
5. የሕዝበ ሙስሊሙ ማህበራዊ ችግሮች እንዲቀረፉ የበጎ አድራጎት እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ማስተባበርና በተገቢው መልኩ መተግበር።
6. በኢትዮጵያ ያሉ ኢስላማዊ ቅርሶችና ታሪኮች እንዲጠበቁና እንዲታወቁ ማድረግ።
7. በሁለንተናዊ መልኩ ለሙስሊሙ ማህበረሰብና ተቋማት የአቅም ግንባታ ተግባራት መከወን።
8. የሕዝበ ሙስሊሙን አንድነት፥ ትብብርና ትስስር ማጎልበት የሚችሉ ተግባራትን መከወን።
9. በመላ ሀገሪቱ የሙስሊሞችን ማህበረሰባዊ ልማትን በተቀናጀ መልኩ መተግበር።
10. የሕዝበ ሙስሊሙን መብቶችንና ጥቅሞችን አሳልፎ በማይሰጥ መልኩ በሀገራዊና ሕዝባዊ ጉዳዮች ከመንግስት ጋር ተባብሮ መስራት።
በመጨረሻም!
🌹🌹🌹🌹🌹
ከላይ የተጠቀሱት የሕዝበ ሙስሊሙ መሪ ድርጅት የሆነው መጅሊስ በአስተዳደር ረገድ የሚጠበቅበትን ሚናን ለማብራራት የተሞከረበት ነው።እያንዳንዱ አንባቢ መጅሊስም ሆነ መጅሊሱን የሚመሩ አካላት ምን ዓይነት አገልግሎቶች እንዲሰጡት እንደሚፈልግ የየራሱን ሀሳብ እንደሚኖረው እገምታለሁ።በዚህ ላይ ይህንን ጽሑፍ መነሻ በማድረግ በጉዳዩ ላይ ዉይይት እያደረጉ ሀሳቡን ማዳብር እንዲሁም ከዚህ አንጻር ምን ዓይነት አመራሮችን ለመጀሊስ እንምረጥ? በሚል እየተወያዩ መዘጋጀት ተገቢ ይሆናል። በተይም የመጅሊስ ጉዳይ የሚያሳስባችና በመጅሊስ ጉዳይ ዋጋ የከፈላችሁ ከታች እሰከ ላይ ባሉት ሁሉም የመጅሊስ እርከኖች ተገቢው ሰው እንዲመረጥ ትጉ።
እንዲሁም በመጅሊስ ስልጣን ላይ ያላችሁም ሆነ ወደ መጅሊስ መሪነት ለመምጣት ፍላጎቱ ያላችሁ ከዚህ አንጻር ራሳችሁን በመገምገም ጉዳዩ አማናና በአላህ ዘንድ ተጠያቂነት ያለበት መሆኑን በመረዳት የተሻለ ተቋም ለመገንባት የየበኩላችሁን ታሪካዊ ሚና እንድትወጡ እጠይቃለሁ።
በዚህ ረገድ ከፌደራል መጅሊስ የአሁኑ ፕሬዝዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱህፋ አንስቶ እስከ የወረዳ መጅሊስ እርከን ያላችሁ ሁሉም የመጅሊስ አባላትና አመራሮች፥ የመጅሊስ ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት፥ እንዲሁም ለመመረጥ የመጅሊስን ደጅ እየጠናችሁና ቤት ለቤት ጥረት እያደረጋችሁ ያላችሁ አካላት፥ እንዲሁም የምርጫ ካርድ ያልወሳዳችሁም ሆነ የወሰዳችሁ እያንዳንዱ ሙስሊም መራጮች የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መሪ ድርጅት ከላይ የተጠቀሱትንና እናንተ የምታስቧቸውን ሚናዎች መወጣት የሚችል፥ የሕዝበ ሙስሊሙን ፍላጎት ያማከለና ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችል፥ የሀገርና የህዝብ ኩራት የሚሆን ጠንካራ ተቋም እዉን ለማድረግ የሚያግዙ
መሪዎችን ለመምረጥ ታሪካዊ ኃላፊነት በጫንቃችሁ ላይ ወድቋል።ስለሆነም ኃላፊነታችሁን ተወጡ!
ስለመጅሊስ ጽሑፌ ቀጥላል። አላህ ካለ በቀጣይ በተመሳሳይ የዑለማ ምክር ቤት ሚናና ተግበራት ጋር በተያያዘ ጽሑፍ እስክንገናኝ እሰከዚያው ቸር እንሰንብት!
https://t.me/Seyfel_Islam
Send as a message
Share on my page
Share in the group
mez mame shared a
Translation is not possible.
ሙዓዊያ እና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁማ በተጋጩ ግዜ ሁለት
ኢስላማዊ ስረወ መንግስት ተመሰረተ የሮሙ ንጉስ ይህን ሰምቶ
እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈ።
<<ከሮም ንጉሰ ነገስት ለ ሙስሊሞች መሪ ሙዐዊያ አቡ ሱፍያን!!
ባንተ እና በዐሊይ መካከል የተከሰተውን ግጭት
ሰምተናል።ስለዚህም ለሙስሊሞች መሪ አንተ መሆን
እንዳለብህም ስለምናምን አንተ ፍቃድህ ከሆነ የዐሊይን ጭንቅላት
ቀንጥሶ የሚያመጣልህን ወታደር ልላክልህ>>
ይህ ደብዳቤ ሙዐዊያ ጋር እንደደረሰም ሙዓዊያም
<<ከሙዓዊያ ለሮም መሪ!!! ሁለት ወንድማማቾች ስለተጣሉ
አንተ ምን አገባህ? አፍህን የማትዘጋ ከሆነ ጅማሬው እኔ ጋ የሆነ
እና ፍፃሜው አንተ ጋ የሆነ ሰራዊት ልኬ አንገትህን በማስቀንጠስ
ለዐሊይ በስጦታ መልኩ አበረክትለታለሁ>>
#ይህ_ትክክለኛ_ሙስሊሞች_ሳለን_ነው
_____
___
ካሊድ ኢብን ወሊድ ለፐርሺያው ንጉሰ ነገስት እንዲህ ሲል
ደብዳቤ ፃፈለት
<<ስለም ትድናለህ። እንቢ ያልክ እንደሆን ግን፤ እናንተ ህይወትን
የምትወዱትን ያህል ሞትን የሚወዱ ሰራዊቶችን ይዤልህ
እመጣለሁ።>>
ንጉሱ ይህን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የቻይናውን ንጉስ የጦር እርዳታ
ሊለምነው ደብዳቤ ፃፈለት።
የቻይናውም ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ መልሶ ላከለት።
<<ንጉስ ሆይ! ተራራን እንኳን ለመናድ ካሰቡ ምንም
ከማያግዳቸው ወታደሮች ጋር ለመጋፈጥ አቅሙ ስለሌለኝ
ጥያቄህን መፈፀም አልችልም።>>
# ምን_ያህል_ሀያላን_እንደነበርን_ተመልከቱ
_____
____
በደውለቱል ዑስማኒያ የአገዛዝ ዘመን የሙስሊም ወታደሮች የጦር
መርከቦቻቸውን ይዘው በአውሮፓ ደሴቶች ሲያልፉ በአከባቢው ያሉ
አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ሙስሊሞች መጥተው ፈትህ
እንዳያደርጉ በመፍራት ከበሮ ከመምታት እና ምንም አይነት ድምፅ
ከማሰማት ይቆጠቡ ነበር።
#ያኔ_ጀግና_ሳለን
_____
____
በደውለቱል ኡስማኒያ የአገዛዝ ዘመን በያንዳንዴ ቤት ደጅ ላይ
ሁለት የበር ማንኳኩያዎች ይኖራሉ። አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ትንሽ
ነው። በትልቀኛው ከተንኳኳ አንኳኪው ወንድ ነው'ና በሩን ሊከፍት
ሚመጣው ወንድ ይሆናል። ነገር ግን በትንሸኛዋ ከተንኳኳ
አንኳኪዋ ሴት መሆኗ ስለሚታወቅ ሴት ትከፍትላታለች።
በዚያ ምርጥ ዘመን አንድ ቤት ውስጥ ሰው ከታመመ ደጅ ላይ
ቀይ አበባ ይንጠለጠል ነበር። ያን አበባ የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ
እዝያ ቤት በሽተኛ መኖሩን ስለሚያውቁ በበሩ ሲያልፉ ድምፃቸውን
ዝቅ ያደርጉ ነበር።
#ሹፍ_ምን_እንመስል_እንደነበር !!!
_____
_
ግዜው ሰላሁዱን አል አዩቢ በይተል መቅዲስን ባስመለሰበት ግዜ
ነበር። እና ጦርነቱ ነገውን ሊጀመር ማታ ላይ የጦር መሪው
ሰላሁዲን የወታደሮቹን ድንኳን እየዞረ ሲያዳምጥ፤ ግማሹ ለይል
ይሰግዳል፣ ሌላው ቁርአን ይቀራል፣ የተቀሩት ደግሞ ይዘክራሉ።
ግን ድንገት በሆነ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ በድንኳኑ ውስጥ ያሉት
ሁሉም ተኝተው ነበር። ይህን ግዜ፦"በዚህች ድንኳን አዳሪዎች
ምክንያት ልንሸነፍ እንችላለን" ብሎ አለፈ።
#ማንተኛበት_ዘመን
_____
___
ቀደምት ዑለማኦች በሶስት ነገራት አደራ ይባባሉ ነበር።
1፦ሰውዬው በሱ እና በአላህ መካከል ያለውን ግንኙነት ካሳመረ፤
በሱ እና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ያምርለታል።
2፦ሰውዬው ሚስጥራዊ ተግባሩን ካሳመረ አላህ ይፋዊ ተግባሩን
ያሳምርለታል።
3፦ሰውዬው የአኪራው ጉዳይ ካስጨነቀው አላህ የዱንያውንም
የአኪራውንም ጉዳይ ያግራራለታል።
_____
_
#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው
ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ
ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።
በእለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ ቁርአንን መቅራት ካልተካተተ ትልቅ
ኪሳራ ነው።
ይህን ፅሁፍ በማሰራጨት ጓደኛህን እንድታነቃው ይከጀላል!
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
mez mame Changed her profile picture
2 years
Translation is not possible.
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group