UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ሥነ ፈለክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

21፥33 እርሱም ሌሊትን እና ቀንን፣ ፀሐይን እና ጨረቃን የፈጠረ ነው፡፡ ሁሉም በምህዋራቸው ውስጥ ይዋኛሉ፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ كُلٌّ فِي فَلَكٍ يَسْبَحُونَ

"ፈለክ" فَلَك የሚለው ቃል "ፈለከ" فَلَك ማለትም "ሖረ" "ሔደ" አለፈ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ምሕዋር"orbit" ማለት ነው፥ የፈለክ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አፍላክ" أَفْلَاك ሲሆን "ምሕዋራት" ማለት ነው፦

21፥33 እርሱም ሌሊትንና ቀንን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ ነው፡፡ ሁሉም በምህዋራቸው ውስጥ ይዋኛሉ፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ كُلٌّ فِي فَلَكٍ يَسْبَحُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ምሕዋር" ለሚለው የገባው ቃል "ፈለክ" فَلَك ሲሆን በዐማርኛ ላይ "ፈለክ" የሚለው ቃል የተወሰደው ከዐረቢኛው እንደሆነ እሙን እና ቅቡል ነው፥ ስለ ከዋክብት፣ ፀሐይ፣ ጨረቃ የሚያጠና የዕውቀት ዘርፍ "ፈለኪያህ" فَلَكِيَّة ማለትም "ሥነ ፈለክ"Astronomy" ይባላል። "አስትሮኖሚ"Astronomy" የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል "አስትሮኖሚያ" ἀστρονομία ከሚል የግሪክ ቃል የተወሰደ ነው። "አስትሮን" ἄστρον ማለት "ኮከብ" ማለት ሲሆን "ኖሞስ" νόμος ማለት "ሕግ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "አስትሮኖሚያ" ἀστρονομία ማለት "የከዋክብት ሕግ" ማለት ነው።

“መሽሪቅ” مَشْرِق የሚለው ቃል "ሸረቀ" شَرَقَ ማለትም "ወጣ" "ታየ" "ተገለጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መውጪያ” “መታያ” “መገለጪያ” "ምሥራቅ" ማለት ነው፥ “መግሪብ” مَغْرِب የሚለው ቃል “ገረበ” غَرَبَ ማለትም “ገባ” “ጠለቀ” “ተሰወረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መግቢያ” “መጥለቂያ” “መሰወሪያ” "ምዕራብ" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ የምሥራቅ እና የምዕራብ ጌታ ነው፥ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፦

73፥9 እርሱም የምሥራቅ እና የምዕራብ ጌታ ነው፥ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው፡፡ رَّبُّ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ فَاتَّخِذْهُ وَكِيلًا

ከመነሻው ፀሐይ በፍጹማዊ እውነታ መውጫ እና መግቢያ የላትም፥ መውጣት እና መግባት አንጻራዊ እውነታ ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ የመሽሪቅ ሙሰና "መሽሪቀይኒ" مَشْرِقَيْنِ ሲሆን "ሁለቱ ምሥራቆች" ማለት ነው። ፀሐይ በበጋ ጊዜ በሰሜን ንፍቀ-ክበብ”north pole” ስትወጣ አንደኛው መውጫ ይህ ሲሆን በክረምት ጊዜ ደግሞ በደቡብ ንፍቀ-ክበብ”south pole” መውጣቷ ሁለተኛው መውጫ ይህ ነው፥ ሁለቱ ምሥራቆች የሚለው ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።

የመግሪብ ሙሰና “መግሪበይኒ” مَغْرِبَيْنِ ሲሆን "ሁለቱ ምዕራቦች" ማለት ነው። ፀሐይ በበጋ ጊዜ በሰሜን ንፍቀ-ክበብ”north pole” ስትገባ አንደኛው መግቢያ ይህ ሲሆን በክረምት ጊዜ ደግሞ በደቡብ ንፍቀ-ክበብ”south pole” መግባቷ ሁለተኛው መግቢያ ይህ ነው፥ ሁለቱ ምዕራቦች የሚለው ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፦

55፥17 "የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ እና የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው"፡፡ رَبُّ الْمَشْرِقَيْنِ وَرَبُّ الْمَغْرِبَيْنِ

ታላቁ ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር ይህንን አንቀጽ የፈሠረው በዚህ መልኩ እና ልክ ነው፦

ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 55፥17

*"የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ እና የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው" ማለት "የበጋ እና የክረምት የፀሐይ መውጫዎች እና የበጋ እና የክረምት የፀሐይ መጥለቂያዎች" ማለት ነው። አላህ በሌላ አንቀጽ፦ "በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ" አል-መዓሪጅ 40 ፥ ይህ የሚያመላክተው በእያንዳንዱ ቀን ለሰዎች የተለያዩ የፀሐይ መውጫዎች እና የፀሐይ መጥለቂያዎች ቦታዎች እንዳሉ ነው። አላህ በሌላ አንቀጽ፦ "እርሱም የምሥራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው" አል-ሙዘሚል 9 ፥ ይህ የሚያመላክተው የተለያዩ የፀሐይ መውጫዎች እና የፀሐይ መጥለቂያዎች ቦታዎች እንዳሉ እና ይህ ልዩነት ለተፈጠሩት ለጂኒዎችም ሰዎችም ጥቅም ያመጣል"*።

( رب المشرقين ورب المغربين ) يعني مشرقي الصيف والشتاء ، ومغربي الصيف والشتاء . وقال في الآية الأخرى : ( فلا أقسم برب المشارق والمغارب ) [ المعارج : 40 ] ، وذلك باختلاف مطالع الشمس وتنقلها في كل يوم ، وبروزها منه إلى الناس . وقال في الآية الأخرى : ( رب المشرق والمغرب لا إله إلا هو فاتخذه وكيلا ) [ المزمل : 9 ] . وهذا المراد منه جنس المشارق والمغارب ، ولما كان في اختلاف هذه المشارق والمغارب مصالح للخلق من الجن والإنس

Send as a message
Share on my page
Share in the group

🤲  አል አቅሷ

👌 ወራሪዎችን ማባረር ብዙ ዋጋና ደም እንደሚያስከፍል በቅኝ የተገዙ ህዝቦች ያውቁታል

ድል በማለዳና በምሽት መሀል አይመጣም

ያለ አቅማቸው አትበል ❗️

ያቅማቸውን አዘጋጅተው ገብተውበታል አላህ ይርዳቸው እኛም አል መውት في سبيل الله ይወፍቀን

{ وَأَعِدُّوا۟ لَهُم مَّا ٱسۡتَطَعۡتُم مِّن قُوَّةࣲ ...

[سُورَةُ الأَنفَالِ: ٦٠]

የቻላቹትን ሀይል አዘጋጁ ነው የተባልነው

እንጂ አቅማችን ከካፊሮቹ እኩል መሆኑ መስፈርት አይደለም ለጂሀድ

فَإِن یَكُن مِّنكُم مِّا۟ئَةࣱ صَابِرَةࣱ یَغۡلِبُوا۟ مِا۟ئَتَیۡنِۚ  (٦٦) }

[سُورَةُ الأَنفَالِ: ٦٥-٦٦]

ከእናንተ መቶ ታጋሽ ሙጃሂዶች  ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ

የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እናሸንፋለን በጌታችን ፍቃድ

የነስር የድል ለሊት ያርግልን

ደህና እደሩልኝ

https://t.me/+6pYJEqYj0aU1M2Jk

https://t.me/+Q-mP9wcqnysk-Ep2

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
MIFTA STUDENT OF WEHID Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group