UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

س- ما هو التوحيد

ج – هو إفراد الله بكل ما يختص به.

.2 س - من الذي خلقك؟

ج - الله - والدليل قوله تعالى :] الله خالق كل شئ [.

.3 س - من الذي يرزقك؟

ج - الله والدليل قوله تعالى :]وما من دابة في األرض إال على الله

رزقها[

.4 س - لما ذا خلقك الله ؟

ج - خلقني لعبادته . والدليل قوله تعالى: ]وما خلقت الجن واإلنس

إال ليعبدون[

.5 س - ما هي العبادة ؟

ج – العبادة: اسم كل ما يحبه الله ويرضاه.

.6 كم شروط قبول العمل؟

ج- اثنان هما اإلخالص واإلتباع.

.7 ما هو الشرك ؟

ج – هو صرف ما يختص بالله لغير الله .

.8 س – هل دعاء المالئكة واألنبياء واألولياء واإلستغاثة بهم والذبح

والنذر لهم والتوكل عليهم وخوفهم من الشرك ؟

ج – نعم كل ذالك من الشرك األكبر.

.9 س – هل نحلف بغير الله ؟

.11 ج –ال ألن الحلف بغير الله شرك.

.11 هل الشرك يحبط العمل ؟

ج – نعم الشرك محبط للعمل . والدليل قوله تالى : ]لئن أشركت

ليحبطن عملك[

.12 س – ما هو اإليمان؟

ج – اإليمان قول باللسان واعتقاد بالقلب وعمل بالجوارح يزيد

بالطاعة وينقص بالمعاصي.

.13 س - أين الله ؟

ج – الله فوق العرش . والدليل قوله تعالى : ]الرحمن على العرش

استوى[

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

“የተከበሩ ዶክተር ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) ፍልስጤማውያንን በተመለከተ የመከሩት አስደናቂ ምክር...”

✭✭✭✭✭✭✭✭✭✭

ለተከበሩት ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) የሚከተሉት ጥያቄዎች ቀረበላቸው፡

“በአሁኑ ሰዓት በፍልስጥኤማውያን ወንድሞቻችን ላይ እየተደረገ ያለው መከራና ሰቆቃ...ለነሱ (ለፍልስጤማውያን) ዱዓ ማድረግ፣የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣ከነሱ ጋር መታገል ይቻላልን?!”

ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ አሉ፦

“በሙስሊሞች ላይ ለሚደርሰው ችግር ዱዓ ማድረግ ግዴታ ነው። በንብረትም ሆነ ቁሳዊ ድጋፍ ማድረግ ግዴታ ነው። ለነሱ የሚጠቅመው ይህ ነው።” ይህንኑ ተከትሎ ለሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፡

“አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁና ይህ ጠያቂ እንዲህ ይላል፡ “የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግና እንዲሁም ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ጂሃድ ከማድረግ ይቆጠራልን?!፤ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በአላህ መንገድ ላይ እንደመታገል ይቆጠራልን?!” ከዚያም ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ፦

“በሰለማዊ ሰልፍ ምንም አይነት የሚገኝ ጥቅም የለውም፤ይልቅስ ከሰላማዊ ሰልፍ የሚገኘው ትርምስ፣ግርግር፣ረብሻ...ነው። ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ጠላቶችን ምን የሚጎዱት ነገር አለ?! ምንም አይጎዱም። በጎዳናዎች ላይ ሰልፎችን ማድረግ ጣላቶችን የሚያስከፋ ሳይሆን የሚያስደስት ተግባር ነው። ኢስላም የተቀደሰ ንፁህ የሆነ ሐይማኖት ነው፤ እንዲሁም ኢስላም በዘፈቀደና በስሜት የሚያስኬድ ሐይማኖት አይደለም። ኢስላም በሸራዓዊ እውቀት ተመርኩዞ የተገነባ እምነት ነው። ኢስላም የትርምስና የውዝግብ ሐይማኖት አይደለም፤ይልቁንም ለተጎዱ ሙስሊሞች ለነሱ የሚያስፈለገው: ዱዓ ማድረግ፣ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ማድረግ፣ ወታደራዊ...ድጋፎችን ማድረግ ነው። ስለዚህ በእነዚህም ሆኑ በሌሎች ጉዳዮች ሙስሊሞች የሰለፎችን መንሐጅ ነው መከተል ያለባቸው። ኢስላም በሰላማዊ ሰልፍ ጋጋታና ረብሻ አይደለም እዚህ ደረጃ የደረሠው፤ እንዲሁም ድምፆችን ከፍ በማድረግ፣ ንብረቶችን በማውደም አይደለም ኢስላም የተገነባው። እነኝህ ተግዳሮቶች ለኢስላም ጉዳት እንጂ ምንም አይነት ጠቃሜታ የላቸውም። እነኝህና የመሳሰሉት ተግዳሮቶች ለሙስሊሞች ውጤቱ የከፋ ነው። በል እንዳውም ካህዲያኖች ይደሰታሉ፤ ሙስሊሞችን ጎዳናቸው፣ አሰቃየናቸው...እያሉ ደስታቸውን ይገልፃሉ...”

ምንጭ፦ [From his lesson on the night of the 2nd/Safar/1423H (15 April 2002), in his open meeting after Maghrib prayer, and also broadcast on Paltalk. This was translated from the live lecture at the time.]

የሸይኽ አቡ ዒያድ (ሀፊዘሁሏህ) እንግሊዝኛ ፅሁፍ በዚህ ሊንክ ያገኙታል።⤵️

https://abuiyaad.com/a/fawzan-....advice-palestinians-

📝 ዶክተር ሸይኽ አቡ ዒያድ (ሀፊዘሁሏህ)

📝 አማርኛ ትርጉም፡ አቡ ሀፍሳህ (ዐፈላሁ ዐንሁ)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አሏህ ከዐርሽ በላይ ለመሆኑ ከሐዲስ ብቻ ማስረጃ

=~~~~~~~~=

የአላህ መልእክተኛ አላህ ከሰማያት ከዐርሽ በላይ መሆኑን በማያሻማ መልኩ ገልፀዋል፤ አላህ ከዐርሽ በላይ መሆኑን ከሚያረጋግጡ የሀዲስ ማስረጃዎች በጥቂቱ እንመልከት፡

قَال النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «أَلاَ تَأْمَنُونِي وَأَنَا أَمِينُ مَنْ فِي السَّمَاءِ›› صحيح البخاري4351

ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፡

‹‹ በሰማይ ያለው(አላህ) አምኖኝ ሳለ አታምኑኝምን››ቡኻሪ 4351

ሙዓውያ ኢብኑ ሀከም ፍየሎችን የምትጠብቅለት አገልጋይ ነበረችው እና ተኩላ በላባት ተበሳጭቶ መታት፤ ይህም ለነብዩ صلى الله عليه وسلم ነገራቸው በዚህም ነብዩ صلى الله عليه وسلم አከበዱበት…

قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللهِ أَفَلَا أُعْتِقُهَا؟ قَالَ: «ائْتِنِي بِهَا» فَأَتَيْتُهُ بِهَا، فَقَالَ لَهَا: «أَيْنَ اللهُ؟» قَالَتْ: فِي السَّمَاءِ، قَالَ: «مَنْ أَنَا؟» قَالَتْ: أَنْتَ رَسُولُ اللهِ، قَالَ: «أَعْتِقْهَا، فَإِنَّهَا مُؤْمِنَةٌ» مسلم 1/381

‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ ነፃ ላውጣትን›› አልኳቸው እሳቸውም‹‹ ወደኔ አምጣት አሉኝ›› ወደ እሳቸው አመጠኋት እና እንዲህ አሏት ‹‹አላህ የት ነው›› እሷም ‹‹በስማይ›› አለች እሳቸዉም ‹‹እኔ ማነኝ አሏት›› እሷም ‹‹ አንቱ የአላህ መልእክተኛ ናቹህ›› አሳቸው እንዲህ አሉ‹‹ ነፃ አውጣት እሷ ሙእሚን ነች››ሙስሊም ዘግበዉታል 1/381

–_

ከሀዲሱ እንደምንረዳው የአላህ መልእክተኛ እምነቷን ካረጋገጡበት አንዱ አላህ ከሰማያት በላይ መሆኑን መመስከሯ ነው፤በዚህ ዘመን አላህ የት ነው አይባልም በሚል ለሚሞግት ሰው በቂ ማስተማሪያ ነው! ልብ ካላቸው!!

አላህ በስማይ ነው ስንል በሰማይ ዉስጥ ሳይሆን ከሰማያት በላይ መሆኑን እና ‹ፊ› የሚትለዋ ፊደል በላይ የሚል ትርጉም እንዳላት ከላይ ስለተመለከትን የሚያወዛግበን አይመስለኝም፡፡

قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَمَّا قَضَى اللَّهُ الخَلْقَ كَتَبَ فِي كِتَابِهِ فَهُوَ عِنْدَهُ فَوْقَ العَرْشِ إِنَّ رَحْمَتِي غَلَبَتْ غَضَبِي»صحيح البخاري 3194

የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፡

‹‹ አላህ ፍጥረታትን(ፈጥሮ) እንደጨረሰ እሱ ዘንድ ከዓርሽ በላይ ካለው መፅሓፉ እዝነቴ ቁጣዬን ቀድማለች ብሎ ፃፈ፡፡›› ሶሂህ አል-ቡኻሪ 3194

ከዚህ ሀዲስ በማያሻማ መልኩ የምንረዳው አላህ ከዐርሽ በላይ መሆኑን ነው፡፡

عَنْ أَنَسٍ قَالَ: فَكَانَتْ زَيْنَبُ تَفْخَرُ عَلَى أَزْوَاجِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ تَقُولُ: زَوَّجَكُنَّ أَهَالِيكُنَّ، وَزَوَّجَنِي اللَّهُ تَعَالَى مِنْ فَوْقِ سَبْعِ سَمَوَاتٍ.‹‹صحيح البخاري 7420

አነስ (ረድየሏሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት፡ ዘይነብ በነብዩ ሚስቶች ላይ ስትፈክር ነበር እንዲህም ትላለች‹‹ እናንተን የዳሯቹህ ቤተሰቦቻቹህ ናቸው እኔን ግን ከሰባት ሰማያት በላይ(ያለው) አላህ ነው የዳረኝ፡፡›› ሶሂህ አል-ቡኻሪ 7420 በሌላ የቲርሚዚ ዘገባ ደግሞ፡

لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الْآيَةُ فِي زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ {فَلَمَّا قَضَى زَيْدٌ مِنْهَا وَطَرًا زَوَّجْنَاكَهَا} [الأحزاب: 37]

አነስ(ረድየሏሁ አንሁ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ እርሷን አጋባንህ፡፡›› ይህ የቁርአን አንቀፅ በዘይነብ ቢንት ጀሕሽ በወረደ ግዜ ዘይነብ በነብዩ ሚስቶች ላይ ስትፈክር ነበር እንዲህም ትላለች‹‹ እናንተን የዳሯቹህ ቤተሰቦቻቹህ ናቸው እኔን ግን ከሰባት ሰማያት በላይ(ያለው) አላህ ነው የዳረኝ፡፡›› ቲርሚዚ 3213

عَنْ أَبِي حَازِمٍ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، مَا مِنْ رَجُلٍ يَدْعُو امْرَأَتَهُ إِلَى فِرَاشِهَا، فَتَأْبَى عَلَيْهِ، إِلَّا كَانَ الَّذِي فِي السَّمَاءِ سَاخِطًا عَلَيْهَا حَتَّى يَرْضَى عَنْهَا» مسلم 1436

አቡ ሁረይራ(ረድየሏሁ አንሁ) እንደዘገቡት የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ ነብሴ በእጁ በሆነው እምላለው አንድ ወንድ ሚስቱን ለምኝታ ጋብዟት እምቢ አትለውም ፤ ያበሰማይ ያለው በሷ ላይ የተቆጣባት ቢሆን እንጂ እሱ(ባሏ) ከእርሷ እስኪወድ ድረስ፡፡››

عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «الرَّاحِمُونَ يَرْحَمُهُمُ الرَّحْمَنُ، ارْحَمُوا مَنْ فِي الأَرْضِ يَرْحَمْكُمْ مَنْ فِي السَّمَاءِ، …»:الترمذي 1924 حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ

አብደላህ ኢብኑ ኡመር(ረድየሏሁ አንሁማ) እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፡

‹‹ አዛኞችን አር-ራህማን(አዛኙ አላህ) ያዝንላቸዋል፤ በመሬት ላሉት እዘኑ በሰማይ ያለው(አላህ) ያዝንላችኋል››ቲርሚ ዘግበዉታል 1924 ሀዲሱ ሶሂህ ነው

ብዙ ሀዲሶችን መጥቀስ ቢቻልም ፅሁፉ እንዳይረዝም ከላይ የጠቀስናቸው ሶሂህ ሀዲሶች አላህ ከሰማያት በላይ ከዓርሽ በላይ መሆኑን ያረጋግጣሉ፤ አላህ ያጠመመው ቢሆን እንጂ ይህንንም የሚያስተባብል የለም፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Send as a message
Share on my page
Share in the group