Translation is not possible.

“የተከበሩ ዶክተር ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) ፍልስጤማውያንን በተመለከተ የመከሩት አስደናቂ ምክር...”

✭✭✭✭✭✭✭✭✭✭

ለተከበሩት ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) የሚከተሉት ጥያቄዎች ቀረበላቸው፡

“በአሁኑ ሰዓት በፍልስጥኤማውያን ወንድሞቻችን ላይ እየተደረገ ያለው መከራና ሰቆቃ...ለነሱ (ለፍልስጤማውያን) ዱዓ ማድረግ፣የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣ከነሱ ጋር መታገል ይቻላልን?!”

ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ አሉ፦

“በሙስሊሞች ላይ ለሚደርሰው ችግር ዱዓ ማድረግ ግዴታ ነው። በንብረትም ሆነ ቁሳዊ ድጋፍ ማድረግ ግዴታ ነው። ለነሱ የሚጠቅመው ይህ ነው።” ይህንኑ ተከትሎ ለሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፡

“አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁና ይህ ጠያቂ እንዲህ ይላል፡ “የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግና እንዲሁም ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ጂሃድ ከማድረግ ይቆጠራልን?!፤ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በአላህ መንገድ ላይ እንደመታገል ይቆጠራልን?!” ከዚያም ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ፦

“በሰለማዊ ሰልፍ ምንም አይነት የሚገኝ ጥቅም የለውም፤ይልቅስ ከሰላማዊ ሰልፍ የሚገኘው ትርምስ፣ግርግር፣ረብሻ...ነው። ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ጠላቶችን ምን የሚጎዱት ነገር አለ?! ምንም አይጎዱም። በጎዳናዎች ላይ ሰልፎችን ማድረግ ጣላቶችን የሚያስከፋ ሳይሆን የሚያስደስት ተግባር ነው። ኢስላም የተቀደሰ ንፁህ የሆነ ሐይማኖት ነው፤ እንዲሁም ኢስላም በዘፈቀደና በስሜት የሚያስኬድ ሐይማኖት አይደለም። ኢስላም በሸራዓዊ እውቀት ተመርኩዞ የተገነባ እምነት ነው። ኢስላም የትርምስና የውዝግብ ሐይማኖት አይደለም፤ይልቁንም ለተጎዱ ሙስሊሞች ለነሱ የሚያስፈለገው: ዱዓ ማድረግ፣ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ማድረግ፣ ወታደራዊ...ድጋፎችን ማድረግ ነው። ስለዚህ በእነዚህም ሆኑ በሌሎች ጉዳዮች ሙስሊሞች የሰለፎችን መንሐጅ ነው መከተል ያለባቸው። ኢስላም በሰላማዊ ሰልፍ ጋጋታና ረብሻ አይደለም እዚህ ደረጃ የደረሠው፤ እንዲሁም ድምፆችን ከፍ በማድረግ፣ ንብረቶችን በማውደም አይደለም ኢስላም የተገነባው። እነኝህ ተግዳሮቶች ለኢስላም ጉዳት እንጂ ምንም አይነት ጠቃሜታ የላቸውም። እነኝህና የመሳሰሉት ተግዳሮቶች ለሙስሊሞች ውጤቱ የከፋ ነው። በል እንዳውም ካህዲያኖች ይደሰታሉ፤ ሙስሊሞችን ጎዳናቸው፣ አሰቃየናቸው...እያሉ ደስታቸውን ይገልፃሉ...”

ምንጭ፦ [From his lesson on the night of the 2nd/Safar/1423H (15 April 2002), in his open meeting after Maghrib prayer, and also broadcast on Paltalk. This was translated from the live lecture at the time.]

የሸይኽ አቡ ዒያድ (ሀፊዘሁሏህ) እንግሊዝኛ ፅሁፍ በዚህ ሊንክ ያገኙታል።⤵️

https://abuiyaad.com/a/fawzan-....advice-palestinians-

📝 ዶክተር ሸይኽ አቡ ዒያድ (ሀፊዘሁሏህ)

📝 አማርኛ ትርጉም፡ አቡ ሀፍሳህ (ዐፈላሁ ዐንሁ)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group