UMMA TOKEN INVESTOR

Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

👉 ተሸበረ ልቤ‼️

ተሸበረ ልቤ ሞትን አሰበና

ሩህ ስትወጣ ያለው ጭንቅ ፈተና

መለከል መውት መጥቶ ሲጨምቃት በጠና

እንዴት ልቋቋመው ስራየ አነሰና

ተጨነቀ ልቤ ያን አስታወሰና

ጭንቀቴ በረታ ስለይ ከወገኔ

እስከመጨረሻው ላላያቸው ባይኔ

ጭራሽ በረታብኝ ጠናብኝ ሀዘኔ

ስራየን ስፈትሽ ባዶ በመሆኔ

ተሸበረ ልቤ ተናጠ እንደ ወተት

በከንቱ ጫወታ ባባከንኩት ሰዓት

በማይጠቅም ወሬ ሰዎችን በማማት

ሞትን ረሰቼ ጌታን መገናኘት

አሁን ገና ከባኝ የቁርዓኑ አያት

وقيل من راق

وظن أنه الفيراق

አልቋል ሰዓት የለም በል ቀጥል ወደፊት

ጊዜው አልፎብሀል ንሰሀ ለመግባት

ተስፋ ቁረጥ ሲለኝ ወኪሉ መለአክት

ተሸበረ ልቤ ሲያስብ ይችን ሰዓት

እናት፣ አባት፣ወገን ቢሰበሰብ ሀብቴ

ሊያድኑኝ አይችሉም ካለቀ ሰዓቴ

ተሳፈር ከተባልኩ ተቆርጦ ትኬቴ

ያን ጊዜ አሳዘነኝ በከንቱ ጩኸቴ

መልሱኝ እያልኩኝ ማልቀስ መቆጨቴ

መልካም ስራ ሳጣ የሚቆም ከፊቴ

አብሮኝ የሚሳፈር ለዘላለም ቤቴ

ይህ ድቅን ሲልብኝ አልቻለም አንጀቴ

ከፈን ሲስተካል ሊያለብሱኝ ነጭ ጨርቅ

አካሌ ሲከዳኝ ሰውነቴ ሲደርቅ

አጥበው ሲከፍኑኝ ዘመድ ሲደባለቅ

ቃሬዛው ሲመጣ ከሰፈሩ ልለቅ

ማን ያቃል ያን ጊዜ የነፍሴን መጨነቅ

መግቢያ ቤቷን ስታይ ዘመድ ስትናፍቅ

ወይ ሞት❗️

መሪቱን ቆፍረው ሲያስገቡኝ መቃብር

በጭቃ መራርገው ሲጭኑብ አፈር

ቁጭ አርገው ሲይዙኝ ነኪር ና ሙንከር

መልስ ተዛብቶብኝ በሀይል ስወገር

ያኔ ስትል ነፍሴ ኢላ አይነል መፈር

ተሸበረ ልቤ ይህንን ሲፈክር!!!

ዋ ሞት መካሪነትህ በቃ‼️

አላህ ከዱንያም ከአኼራም ፈተና ይጠብቀን!!!!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

የምትጣራበት ነገር ቅናቻ ወይ ጥመት!!!

🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂

✍عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:- {مَن دَعا إلى هُدًى، كانَ له مِنَ الأجْرِ مِثْلُ أُجُورِ مَن تَبِعَهُ، لا يَنْقُصُ ذلكَ مِن أُجُورِهِمْ شيئًا، ومَن دَعا إلى ضَلالَةٍ، كانَ عليه مِنَ الإثْمِ مِثْلُ آثامِ مَن تَبِعَهُ، لا يَنْقُصُ ذلكَ مِن آثامِهِمْ شيئًا.}

 📚رواه مسلم الرقم: 2674 | 

🔹ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ 

“ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተለው ሰው አምሳያ ምንዳዎች ይኖሩታል። ይሄ ከምንዳዎቻቸው ምንም አይቀንስም። ወደ ጥመት የተጣራ የተከተለው ሰው አምሳያ ወንጀሎች ይኖሩበታል። ይሄ ከወንጀሎቻቸው ምንም አይቀንስም።”

📚( ሙስሊም ዘግበውታል: 2674)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

🅾አጫጭር መረጃዎች🅾

⭕️ከየመን ጦር የተሰጠ መግለጫ

ጦራችን ባለፉት ሰአታት ውስጥ በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በጽዮናዊያኑ ግዛት በሚገኙ የተመረጡ ቦታዎች ላይ ያስወነጨፍን ሲሆን ለአላህ ምስጋና ይግባውና ኢላማቸውን ጠብቀው አርፈዋል።

የየመን ጦር በፍልስጤም ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከልና ለመላው የየመን ህዝብ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም የወራሪዋ ጦር በጋዛ ወንድሞቻችን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት እስክታቆም ድረስ ወታደራዊ ዘመቻችን የሚቀጥል ይሆናል።

ድል የሚገኘው ከአላህ ብቻ ነው።

ረቢዑል አኺር 17   1445 ሂጅራ

ኖቬምበር 1 ቀን 2023

⭕️አሜሪካ ለእስራኤል የ14 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ልታደርግ ነው

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ ወደ ቴል አቪቭ ያቀናሉ።

❌⭕️እስራኤል ሁለት የሃማስ አዛዦችን መግደሏን አስታወቀች

ቴል አቪቭ በጅባሊያ የስደተኞች ጣቢያ ላይ በፈጸመችው የአየር ድብደባ በጥቂቱ 195 ፍልስጤማውያን ህይወት ማለፉን ሃማስ ገልጿል።

በዱዓ ሁላችሁም በሰገዳችሁበት ወንድሞቻችንን አትርሷቸው 🤲🤲🤲🤲

የማታው ፕሮግራማችን በአሏህ ፈቃድ እንደተጠበቀ ይሆናል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

የሰሜን ኮሪያው መሪ ለፍልስጤም ድጋፍ እንዲደረግ ማዘዛቸው ተነገረ

ድጋፉ ለሃማስ የጦር መሳሪያ በማቅረብ ሊታይ እንደሚችልም ነው የደቡብ ኮሪያ የስለላ ተቋም ያስታወቀው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

Let us make follow together ፎሎው እንዴራረግ

Send as a message
Share on my page
Share in the group