UMMA TOKEN INVESTOR

About me

ربي هو الله . ديني الإسلام، وأنا أمة النبي محمد صلى الله عليه وسلم.

Translation is not possible.

የተከተልከው መንገድ ቀጥተኛ መሆኑን ካረጋገጥክ:-

የመንገዱ ርዝመት፣የተጓዦቹ አናሳነት፣የመሰናክሎቹ ብዛት፣የተቃዋሚዎቹ ዉዥንብር አያሸማቅህ። ዋናው የሚፈለገው ነገር ከመስመሩ ሳትወጣ በጎዳናው ላይ ጸንተህ ወደ ቀጣዩ ዐለም ሂወት መሸጋገርህ ነው።

If you confirm that the path you followed is straight:

Don't let the length of the road, the fewness of the travelers, the number of obstacles, the chaos of the opposition scare you. The main thing that is required is that you stay on the streets without going out of line and move on to the life of the next world.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

👉 ራስህን ለማስደሰት ሌሎችን አትጫን።

ስህተትህን  ትክክል ለማስመሰል ግለሰቦችን አትበድል።

ሁሌም ቢሆን ደስታህን ከሰዎች ህመም አርቀህ ለመገንባት ሞክር ።

#በዩሱፍ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አዳማ ነገ ትደምቃለች‼️

=====================

በነገው ዕለት አዳማ ላይ ልዩ የኪታብ ኮርስ አለ።

በውቢቷ የአዳማ ከተማና ዙሪያዋ የምትገኙ ሙስሊሞች ይህ እድል እንዳያመልጣችሁ ተጠቀሙበት።

ለሌሎችም መንገርን አትርሱ።

አቅራቢ፦ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

ቦታ፦ አዳማ 05 ኢብኑ ዐባስ መስጂድ

ቀንና ሰዓት፦ ነገ ማክሰኞ ሕዳር 11, 2016 E.C  ከዐስር በኋላ

=====================

የኪታብ ስም፦ ላሚይ'የቱ ኢብኒል ወርዲይ ፊል-ሒከሚ ወል-ዓዳቢ

ኪታብ ስለተዘጋጀ እዛው ማግኘት ትችላላችሁ።

||

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

~መብራት አጥፍተው፣ በብርድልብሳቸው ተሸፍነው፣በጨለማ ለሚያነቡ አይኖች አሏህ ፈረጃቸውን ያቅርብላቸው!

~አዛኝ መሆናቸው ልባቸውን ያቆሰላቸው ደጎች እፎይ የሚሉበት እቅፍ አይራቃቸው!

~ናፍቆት ከጥም በላይ ለከበዳቸው ናፍቆታቸው አደብ የሚይዝበት ሐላል ብስራት አይራቃቸው!

•አብሽሩ!

ከሁሴን አራጋው

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እንዳትሰላቹ እስከ መጨረሻው ይነበብ!!!

እ.ኤ.አ. በ 1258 የሞንጎላውያን ጦር ለማውራት የሚዘገንን እልቂት የበግዳድ ሙስሊሞች ላይ ከፈፀመ፣ የዐባሳውያን ኺላፋንም እስከ ወዲያኛው ካፈራረሰ በኋላ እርጥብ ደረቅ ሳይለይ ያገኘውን እየበላ ወደ ደማስቆ ሲገሰግስ የሆነውን አልኢማም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይተርኩታል።

“ከኢስላማዊ ሸሪዐህ ውጭ ያለው የተታር ጦር ደማስቆን ሲያጠቃ ጊዜ ላኢላሀ ኢለላህ” የሚሉት ሙስሊሞች ወደ ሁሉን ቻዩ አላህ ከመሸሽ ይልቅ ‘አደጋን ያስወግዳሉ፣ ጉዳትን ያነሳሉ’ ብለው ወደሚያምኑባቸው ሰዎች መቃብር ነበር የወጡት። ከነዚህም ሰዎች ገጣሚያቸው እንዲህ ሲል ገጥሟል፡-

‘እናንት ተታርን የምትፈሩ

በአቡ ዑመር ቀብር ተጠለሉ።’

ወይም ደግሞ እንዲህ ይል ነበር፡-

‘በአቡ ዑመር ቀብር ተጠበቁ

ያተርፋችኋል ከጭንቁ።’

ይህኔ እንዲህ አልኳቸው፡ ‘እነዚህ እርዳታን የምትጠይቋቸው ሰዎች ከናንተው ጋር ጦርነቱ ውስጥ ቢገቡ ልክ የኡሑድ ጦርነት ላይ ሙስሊሞች እንደተሸነፉት ይሸነፋሉ።’ … በዚህም ሳቢያ የዲኑ ምሁራን እና አስተዋዮች በዚህ ጦርነት ጊዜ አልተዋጉም። ምክንያቱም አላህና መልእክተኛው ያዘዙበት የሆነው ሸሪዐዊ ጦርነት ስላልነበር፣ ክፋትና ጥፋት የሚከተለው በመሆኑ፣ በጦርነቱም የሚፈለገው ድል ባለመኖሩ ነው። እናም የዱንያም ይሁን የአኺራ ሽልማት አይገኝበትም።… ከዚህ በኋላ ሰዎችን ሃይማኖታቸውን አሸናፊና የላቀ ለሆነው አላህ እንዲያጠሩ፣ ከሱም ብቻ እንጂ እርዳታን እንዳይጠይቁ፣ ከዚህ ውጭ ቅርብ በሆነ መልአክም፣ በተላከ ነብይም እርዳታን እንዳይጠይቁ ማዘዝ ያዝን። ልክ የላቀው አላህ የበድር ጦርነት ጊዜ ከጌታችሁ እርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ መለሰላችሁ እንዳለው ማለት ነው። … ከዚያ በኋላ ሰዎች ሁኔታዎቻቸውን ሲያስተካክሉና በጌታቸው እርዳታ እውነት ብለው ሲያምኑ በጠላታቸው ላይ ረዳቸው። ተታሮች የዚህን ጊዜ የተሸነፉትን ያክል ቀድመው አልተሸነፉም። ምክንያቱም ቀድሞ ከነበረው በተለየ የላቀው አላህ ተውሒድ እና ለመልእክተኛው ታዛዥ መሆን በሚገባ ስለተረጋገጠ ነበር። የላቀው አላህ መልእክተኛውንና እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቷም ህይወት እንዲሁም ምስክሮች በሚቆምበት ቀን በርግጥም ይረዳል።” [አረድ ዐለል በክሪ፡ 2/732-738]

ዛሬም ችግሩ ከፍቶ ሙስሊሙ በዐቂዳህ ብክለት ከጫፍ እስከ ጫፍ ይናጣል። ፍትህን በነፈጉት አንባገነኖች ይረገጣል። በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ይታመሳል። ታዲያ ችግሩን የሚመለከቱ የተለያዩ አካላት እንደየአስተሳሰባቸው የተለያዩ የመፍተሔ አቅጣጫዎችን መርጠዋል። ከፊሉ ሙስሊሙን ካለበት ውርደት ለማውጣት ሁነኛው መፍተሄ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን ማፈርጠም ነው በሚል ጧት ማታ ለዚያ ይጥራል፣ ስለለዚያም ይደሰኩራል። ከፊሉ ሌሎች አጀንዳዎችን ከቁብም ሳይቆጥር ማህበራዊ ህይወትን ያቃና ዘንድ ሰርክ ደፋ ቀና ይላል። ሌላው የችግሩን ቀዳሚ ሰበብ ፖለቲካ አድርጎት ኖሮ የስልጣን ማማዎችን ለመቆናጠጥ ሳይቦዝን ይጭራል። ሌላው ደግሞ የችግሩ ምንጭ ከዘመናዊ ትምህርት መራቃችን ነው በሚል ያለ የሌለ ሃይሉን አስኮላ ላይ አድርጓል። እነዚህ “የመፍተሄ አቅጣጫዎች” ከፊሎቹ ቢሳኩም የሙስሊሙን ክብር የማያስመልሱ፣ ካለበት ምስቅልቅል ህይወት የማያወጡት ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ከፊል እውነታ ቢይዙም ነገር ግን ባፈፃፀማቸው ግድፈት ምክንያት ይበልጥ የሙስሊሙን ስቃይ ጨምረውታል። “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ።

በኢኮኖሚ መፈርጠም ከገባንበት ውጥንቅጥ ለመውጣት ዋስትና አይሆነንም። እንዳውም ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም {ድህነትን አይደለም የምፈራላችሁ! ይልቁንም ሀብትን ለማግበስበስ የምታደርጉትን መሽቀዳደም ነው የምፈራላችሁ!} ይላሉ። [አስሶሒሐህ፡ 2216] ዛሬ ዱንያ ፊቷን ስታዞርላቸው ከዲን ፊታቸውን የሚያዞሩት ስንቶች ናቸው? ዘመናዊ ትምህርትም ብቻውን ከችግራችን አይታደገንም። እንዳውም በቅጡ ካልተያዘ፣ በከሃዲዎች ታሪክና ስልጣኔ ተማርከን የአስተሳሰብ ቅኝ ግዛት ስር ከወደቅን መማራችን ይበልጥ ለውድቀታችን ሰበብ ሊሆን ይችላል። ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንደሚሉት “የፋርስና የሮማ ፈላስፎች ጥበብ ላይ የሚያተኩር ለኢስላማዊ ጥበብና ስርኣት ልቡ ውስጥ ቦታ አይኖርም።” [አልኢቅቲዳእ፡ 217] ዛሬ ሃያ ሰላሳ አመት እድሜያቸውን ትምህርት ላይ ፈጅተው ይሄ ነው የሚባል ትኩረት ባልሰጡት እምነት ላይ በተበከለ ህሊናቸው ሊፈርዱ የሚዳዳቸው ስንቶች ናቸው? የስልጣን ማማዎችን መቆናጠጥም በራሱ ሸሪዐዊ ፍትሕ በህዝብ ዘንድ እንዲሰፍን አያደርግም። ለምን ቢባል“ከተውሒድ በላይ ፍትህ፣ ከሺርክ በላይ በደል የለምና!!" [መዳሪጁስሳሊኪን፡ 3/336] ይልቅ ቀዳሚው የመፍተሄ አቅጣጫ የዐቂዳን ብክለት ማስወገድ ነው። እምነት ሲስተካከል ሌሎቹ ጉዳዮች መስመር ይይዛሉ። ተውሒድ በሌለበት የሙስሊሙ ልማትም፣ ብቃትም፣ ንቃትም ፍትሕም አይታሰብም።

ከ"ተውሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ" መጽሐፍ የተወሰደ

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group