UMMA TOKEN INVESTOR

About me

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?ፉሲለት 41፥33

shemsu shared a
Translation is not possible.
26 weeks' Translate

የጋዛ ሴቶች ጉዳይ ሒጃብ የማውለቅ ቢሆን ኖሮ አውሮፓዊያን የጦር መርከቦቻቸውን ይልኩላቸው ነበር። የጋዛ ወንዶች ጉዳይ የግብረሰዶማዊነት ጉዳይ ቢሆን ኖሮ አሜሪካ የአውሮፕላን ተሸካሚዎችን ትልክላቸው ነበር። የጋዛ ህጻናት ጉዳይ ጾታ የመቀየር ጉዳይ ቢሆን ኖሮ የተባበሩት መንግስታት በአንድ ድምፅ ያለቅስላቸው ነበር። ነገር ግን ጉዳዩ የእምነት እና የክህደት ሆነ። እምነት "የቲም" ሲሆን ክህደት ግን ብዙ ቤተሰቦች አሉት።

#mahi mahisho

ኡማ ላይፍ

👇👇👇

https://ummalife.com/mahimahisho

Mahi Mahisho | UmmaLife

Mahi Mahisho | UmmaLife

Mahi Mahisho: Mahi Mahisho. Nikname: @mahimahisho | One Ummah — One Network - was created as a response to the Internet technology needs of Muslims and all adherents of traditional value
Send as a message
Share on my page
Share in the group
shemsu shared a
Translation is not possible.

International Union of Muslim Scholars

አንድ ታዋቂ የሙስሊም ምሁራን ህብረት የሙስሊም ወታደሮች በጋዛ ውስጥ ያለውን "የዘር ማጥፋት" ለማስቆም "በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡ" የሚጠይቅ አዋጅ አውጥቷል.

ዓለም አቀፉ የሙስሊም ምሁራን ህብረት (IUMS) ማክሰኞ በሰጠው መግለጫ የሙስሊም ወታደሮች ፍልስጤማውያንን መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው ብሏል። ገዥ መንግስታት እና ባለስልጣናት ጦር ልከው ጋዛን ከእልቂት እና ጅምላ ጥፋት ለመታደግ በሸሪዓው መሠረት በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡ ይጠበቅባቸዋል" ሲል ገልጿል።

"ጋዛ እና ፍልስጤም እንዲጠፉ እና እንዲወድሙ መተው በአላህ እና በፍልስጤማውያን ላይ ክህደት ነው" ብሏል።

ህብረቱ አክሎም ፍልስጤምን የሚዋሰኑ ሀገራት ግብፅ፣ዮርዳኖስ፣ሶሪያ እና ሊባኖስ - ፍልስጤማውያንን እራሳቸውን እንዲችሉ መተው “በአላህ ፊት ከትልልቅ ወንጀል” አንዱ መሆኑን በመግለጽ እርምጃ የመውሰድ የበለጠ ግዴታ አለባቸው ብሏል።

@Meddle East Monitor

Send as a message
Share on my page
Share in the group
shemsu shared a
Translation is not possible.

የመን ይፋዊ በሆነ መልኩ እስራኤል ጋር

ጦርነት ያወጀች የመጀመሪያዋ ሀገር ሁናለች

...

ሀሩን ሚዲያ፥ ጥቅምት 20/2016

...

የየመን ታጣቂ ሃይሎች ሚሳኤሎችን እና ዩኤቪዎችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፋቸውን ተናግረዋል።

...

“የእኛ የታጠቁ ሃይሎች በእስራኤል የተለያዩ ኢላማዎች ላይ እጅግ ከባድ የሚባሉ የባለስቲክ እና የክሩዝ ሚሳኤሎችን እንዲሁም በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አስወነጭፈናል" ሲል ገልጿል። ከነዚህ ውስጥ ረጅም ርቀት የሚጓዙ ሚሳኤሎች የእስራኤል የኒውክለር ማብላያን ኢላማ ያደረጉ ጭምር ነበሩ ተብሏል።

...

የየመን ጦር ሃይሎች ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ያህያ ሳሪ የእስራኤል ጥቃት እስኪቆም ድረስ ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም የተሻሉ ጥቃቶችን ማድረሳችንን እንቀጥላለን ብለዋል

Send as a message
Share on my page
Share in the group
shemsu shared a
Translation is not possible.

ኢየሩሳሌም ዳግም በሙስሊሞች እጅ መልሳ የማትገባ ይመስላችሗል ??? አል አቅሷ መልሶ ነፃ የማይወጣ ይመስላችሗል ??!! አትጠራጠሩ !!!!

         👉 t.me/Seidsocial

የቅርቡን የዚህችን እጅግ ጥንታዊት ከተማ ታሪክ እናንሳ እንኳ ቢባል

፨ ለ በርካታ መቶ አመታት በባይዛንታይን ሮሞች አረመኔያዊ አገዛዝ ስትማቅቅ የቆየችው ቁድስ በነ ኻሊድ ኢብን ወሊድ እና አቡኡበይዳ ኢብን አልጀራህ የሚመራው ጦር ባይዛንታይኖችን አንበርክኮ ቁድስ ዳግም በሙስሊሞች እጅ ለመግባት ችላ ነበር ። የቁድስን ቁልፍ ቦታው ድረስ ሂደው የተቀበሉት ኡመር ኢብኑል ኸጧብ የቁድስን ነዋሪዎች ነፃነት አውጀው ነበር የተመለሱት ። ቁድስ ከዚያ በሗላ አበበች አሸበረቀች በፍትህና በኢስላማዊው ስልጣን ተንቆጠቆጠች ።

፨ በኡመር ጊዜ ሙስሊሞች ከተቆጣጠሯት በሗላ ቁድስ እስከ መጨረሻው በሙስሊሞች እጅ አልቆየችም ። የሙስሊሞችን መከፋፈልና እርስበርስ መባላት ተጠቅመው ባይዛንታይኖች ዳግም ቁድስን ተቆጣጠሩ ። ቁድስ ( ኢየሩሳሌም ) ዳግም የጨለማ ዘመን ውስጥ ገባች ። ከተማዋን በደል ግፍና ጭካኔ ሞላት !! በከተማዋ የሚስኪኖች ዋይታና የገዥዎች ከልክ ያለፈ አረመኔነት እንጅ አይሰማም አይታይም ነበር ! ቁድስ በባይዛንታይኖች እንደዚህ በበደል ተውጣ ቆዝማ አዝና ብዙ አመታትን አሳለፈች !!

፨ አሏህ #ሰልጁቅ የተሰኙ ቱርኮችን ከወደ ምስራቅ ኤዥያ አስነሳ ። የሰልጁቅ የልጅ ልጅ የሆኑት እነ ቱግሪል ፣ ቻግሪ ፣ አልፕ አርስላን ፣ መሊክ ሻህ የመሳሰሉ ተወዳዳሪ አልባ ጀግና የጦር መሪዎች የአለም ልእለሀያል የነበረውን የባይዛንታይን ሮም ስርወመንግስት ስብርብር አድርገው የቱርኮች የኢስላም ገባሪ አደረጉት ። ከሰልጁቆች ጎሳ #ከኪኒክ የሚመዘዘው የሰልጁቆቹ ጦር መሪ #አቲሲዝ_ቤይ ባይዛንታይኖችን አንኮታኩቶ ዳግም ቁድስ ነፃ አወጣት ። አላህ ዲኑን በማን እንደሚረዳው ይአጅባል ። ገና ከሰለሙ ጥቂት አመታትን ያስቆጠሩት ሰልጁቅ ቱርኮች የኢስላም ቅዱስ ከተሞችን በሙሉ አስመልሰው ከቻይና እስከ ሮም ያሉ የኢስላም ጠላቶችን በጉልበቶቻቸው አንበረከኳቸው ።

፨ በሀያሎቹ ወራሪዎች ሞንጎሎች የሰልጁቆች የአባሲድና የኸዋርዚም ሙስሊም መንግስታቶች  ሲደመሰሱ አሁንም ዳግም አውሮፓዊያን ተባብረው " የመስቀል ጦርነት " በሙስሊሞች ላይ አወጁ ። ሁሉንም የአውሮፓ መንግስታት ባካተተውና በጳጳስ ክሊመንት በተባረከው በዚህ ጦርነት ሙስሊሞች እንደ ቅጠል ረገፉ !! ኢየሩሳሌምን ( ቁድስ ) የሰው ደም ሀይቅ ሆኖ ተንጣለለባት ። ህፃናት አዛውንት ሳይሉ ፣ ሴት ደካማ ሳይሉ መስቀላዊያኑ ሁሉንም በሰይፋቸው አረዷቸው ። ቁድስም ዳግም በጭራቆች እጅ ገባች ።

፨ አሁን ደግሞ ቁድስን ዳግም ማስመለስ የአንድ በአሁኗ የኢራቋ ቲክሪት ከተማ የተወለደ ኩርዳዊ ሙጃሂድ ተራ ሆነ ። ያ ሙጃሂድ የሙጃሂድ ልጅ ሰላሁዲን አልአዩቢ ይባላል ።

ሰላሁዲን በሰልጁቅ የጦር መሪ በነበረው በኢማዱዲን ዘንኪ ልጅ በኑረዲን ዘንኪ አመራር ስር ሆኖ በወታደራዊ ክህሎት ተኮትኩቶ በኡለሞች ተርቢ ታንፆ አደገ ። አባቱ ሰላሁዲንን ከልጆች ጋር ሲጫወት ባገኘው ጊዜ ብድግ አደረገና ፍርጥ አደረገው ። እና ተቆጣው ሰደበው ። " እኔ አድገህ ቁድስን ታስመልሳለህ እያልኩ አንተ እዚህ አቧራ ታቦላለህ ?" አለው ። ሰላሁዲን አላለቀሰም ። ለምን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃልና ።

ሰላሁዲን ቁድስን ነፃ ሳያወጣ በፊት ስቆ አያውቅም ተደስቶ አያውቅም ። ያ የአሏህ ወልይ በቱርኮች ጥምረት መላው የአውሮፓ መስቀላዊ ጦርን ደምስሶ ኢየሩሳሌም ( ቁድስን ) ዳግም ነፃ አወጣ ።

፨ ከዚያ በሗላ በግብፅ የነገሱት ቱርኮቹ ማምሉኮች ተረክበው ኢየሩሳሌምን ጠብቀው አቆዩ ።

፨ ከነርሱ በሗላ የአለማችን የምንጊዜውም ሀያሉ ኢምፓየር የሚሰኘው የኦቶማን ኺላፋ ( ደውለቱል ኡስማኒያ ) ቦታውን ተክቶ በየትኛውም የአለም ጫፍ ያለን የኢስላም ሉአላዊነት ሳያስደፍር ለ 500 አመታት ቀጥ አድርጎ ገዛ ። ያኔ እንኳንስ ቁድስንና ትሪፖሊን እንኳ ማጥቃት የኦቶማኖችን ጀሃነም ያስከትላል ። አውሮፓን በእንብርክኳ ያስኬዳት ፣ ሩሲያን ወገቧን የሰበራት ያ የኦቶማን ኺላፋ እሶከ ውድቀቱ መጨረሻ ድረስ ቁድስን መካንና መድናን ለጠላት አሳልፎ አልሰጠም ነበር !

፨ አሁን ቁድስ ከአንደኛው የአለም ጦርነት በሗላ በክርስቲያን_አይሁዳዊያን ጥምረት ስር ነች ። እነሆ ቁድስ ማንባት ከጀመረች ድፍን አንድ ክፍለዘመን ሊሞላት ነው ።

እና ከዚያ ሁሉ ጨለማ የወጣች ቁድስ አላህ አሁን ሌላ ሰላሁዲን ፣ ሌላ አቲሲዝ ቤይ ፣ ሌላ አልፕ አርስላንን አይልክላትም ብላችሁ ታስባላችሁ ??? በፍፁም አታስቡ !

ወድቆ መነሳት ፤ ጨለሞ መብራት የቁድስ ተፈጥሮዎች ናቸው !

ቁድስን አንድ ጊዜ አረቦች ፣ 3 ጊዜ ቱርኮች አንድ ጊዜ ኩርዶች ነፃ አውጥተዋታል ! አሁንስ እነማን የነፃነት ሰንደቁን ይዘው ቁድስን ነፃ ያወጡ ይሆን ??? ሁሉንም ጊዜ ያሳየናል !

ግና አትጠራጠሩ ቁድስ ነፃ ትወጣለች !!

#seid_mohammed_alhabeshiy

👉 t.me/Seidsocial

Send as a message
Share on my page
Share in the group
shemsu Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group