UMMA TOKEN INVESTOR

fatuma Nuri قام بمشاركة
لا يمكن الترجمة

«የሰው ልጅ ወደዚህ ዓለም ባዶውን ይመጣል!

ከዚያ ሁሉንም ነገር ለማግኘት ይሯሯጣል!

ከዚያም ሁሉን ነገር ይተዋል።

ከዚያ ሁሉንም ነገር ጥሎ ይሄዳል!

ከዛም ስለ ሁሉም ነገር ይጠየቃል።»

أرسل كرسالة
شارك على صفحتي
شارك في المجموعة
لا يمكن الترجمة

አልሀምዱሊላሂ

አላሁመ እርሀምና ቢራመትክ

أرسل كرسالة
شارك على صفحتي
شارك في المجموعة
fatuma Nuri قام بمشاركة
لا يمكن الترجمة

እህቴ 🌷 9

ዛሬ የእዝነትና የፍቅር የአታክልት ስፍራ በሆነዉ (በአቡ ደህዳህ) የአታክልት ስፍራ ዉስጥ ቆይታ እናረጋለን። ያቺ የአታክልት ስፍራ ልብን በሀሴት ምትሞላ፣ ደስታ የምትሰጥ፣ ሰላማዊ አየር ያላት ዉብ የአታክልት ስፍራ ናት። ያየዉን ሰዉ ድንገት ሳያስተዉል ‛ሱብሀነላህ!’ እንዲል ታስገድዳለች። የመዲና ሰዎች አዉርተዉላት የማያበቁ እጅግ ዉብና ምርጥ የአታክልት ስፍራ ነበር።

ከዕለታት በአንዱ ቀን የምድር ሰዎችን እንዳስገረመዉ ሁሉ የሰማይ መልዕክተኞችን አጀብ ማሰኘት የሚችል የሚገርም ክስተት ተከሰተ። ንፁህ ዐይኖችን በእንባ ያጠበ፣ እዚያ የነበሩትን ብቻ ሳይሆን ታሪካቸዉን የሰማዉን ሰዉ በእንባ ያራጨ ገራሚ ክስተት ተከሰተ።

ክስትቱ ወዲህ ነዉ..

አንድ ቀን (አቡ ደህዳህ) በነቢያችን አጠገብ ሲያልፍ የአንድን ታዳጊ ልጅ ለቅሶ ይሰማል። ልጁ የቲም መሆኑን ሲያዉቅ አዘነለትና ቆሞ የልጁን ጉዳይ መስማት ፈለገ። ልጁም ሀዘን በጎዳዉ አንደበት እንባዉ እየቀደመዉ ረሱሉን እንዲህ አላቸዉ..

«አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! በአታክልት ስፍራዬ ዙሪያ ግንብ እየሰራሁ እያለ (ግንዱ) የጎረቤቴን አንዲት የተምር ዛፍን ቆረጠበት። እንዲተዉልኝ ወይም እንዲሸጥልኝ ጠየኩት። እሱ ግን እምቢ አለ።»

ረሱሉም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሰሀቦችን ያን ጎረቤቱን እንዲጠሩት አዘዙትና መጣ። ረሱሉም ልጁ የቲም ስለሆነ እንዲሰጠዉ ሌላዉ ቢቀር እንዲሸጥለት ጠየቁት። እሱ ግን እንደማያረገዉ ተናገረ።

ረሱሉም በጣም የሚገርምን ንግድ አመላከቱት.. «ሽጥለት! ለአንተ ደግሞ በምትኩ መቶ የተምር ግንዶች ጀነት ዉስጥ አሉልህ!» አሉት። (ዐዉ ከማ ቃለ)

ሁሉም ሰሀባ በድንጋጤ ክዉ አሉ። ይሄን የመሰለ ግብይት ወደ ቀረበለት ሰዉ ጆሮዎች ዞሩ። እንደሚቀበል ማንም ሸክ አልነበረዉም።

እሱ ግን እምቢ አለ።

የቲሙም ልጅ እንባ በእንባ ሆነ። የሰሀቦች ዐይንም ወደ ሰዉዬዉ በግርምት ማየት ጀመሩ። እሱ ግን ምንም አቋሙን አልቀየረም ነበር።

ይሄኔ ነዉ (የአቡ ደህዳህ) ታሪክ ሚጀምረዉ። አቡ ደህዳህ ይሄንን ምልልስ ከሰማ ብኃላ ነፍሱ ወደ ጀነት ናፈቀች። ረሱልንም እንዲህ ሲል ጠየቀ..

«አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! የአታክልት ስፍራዬ ሽጬ ለልጁ የተምር ግንዱን ባስመልስለት በጀነት ዉስጥ የተምር ዛፍ አገኛለሁ?»

ረሱሉም ደስታ ፊታቸዉን አፈካዉ። «አዎ!» አሉት። አቡ ደህዳህም ወደ ሰዉዬዉ ዞረና «የአታክልት ስፍራዬን ታዉቀዋለህ?!» አለዉ። ሰዉዬዉም «አዎ!» አለ።

አቡ ደህዳህም «የተምር ግንድህን በአታክልት ስፍራዬ ሽጥልኝ!» አለዉ። ተስማማ ንግዱ ተፈፀመ። (ሱብሀነላህ!)

የልቡ ምት የእግሩን ፍጥነቶች እየቀደመ ወደ አታክልት ስፍራዉ ሮጠ። የመዲና ቤቶች በመላለሱት በተቆራረጠ ድምፅ..

«ኡመ ደህዳህ!..» ብሎ ሚስቱን ተጣራ።

«..ከአታክልት ስፍራዉ ዉጪ! እሱ ለአላህ!» አላት። የደህዳህ እናትም ወዲያዉ ከግዛቷ ተነሳች። እጆቿን ከፍራፍሬዎቹ ላይ አነሳች። በልጆቿ እጅ ላይ የቀሩትን ፍራፍሬ ሳይቀር ቀማቻቸዉና አማና ነዉና አስቀመጠችዉ። የባሏን ትዕዛዝ ከመፈፀሟ በፊት የአላህን ትዕዛዝ «ለበይክ!» አለች። ምንም ሳትጠይቅ፣ ምንም ሳታጣራ በንፁህ ልብ ዉሳኔዉን ተቀበለች። አንድ ነገር ብቻ ነዉ ምታቀዉ። «ለአላህ!» መሆኑን።

ከዚያም ወደ ባሏ ዞረችና..

«ትርፋማ ንግድ ነዉ አቡ ደህዳህ! ትርፋማ ንግድ ነዉ።» አለች።

እቺ እህትሽም የጀነትን ፀጋ በማሠብ ከዱንያዊዉ የአታክልት ስፍራ ወጣች።

ምን አይነት ሚገራርሙ ባልና ሚስት ናቸዉ?!

ልቧ በአታክልት ስፍራዉ ላይ የተንጠለጠለ ቢሆንም ያለ አንዳች ኪላፍና ሙሉ በሆነ ዉዴታ የባሏን ትዕዛዝ አከበረች። ወደደች።

ዛሬ እኔ ምንም አላወራም። ታሪኩ ብቻዉን ለሚገሰፁት በቂ ትምህርት ነዉ።

[[እህቴ! የፈለገዉን ያህል ፈታኝ ቢሆንም ከዱንያ የአታክልት ስፍራሽ ዉጪና ለአላህ መንገድ ደስ ከሚልሽ ነገር ላይ ለግሺ! ከንብረትሽ፣ ከወቅትሽ፣ ከእድሜሽ ለዚህ ዲን መፅዉቺ!! የአላህን ዉዴታና የጀነቱን የአታክልት ስፍራ በማሰብ በደስታ ካለሽ ላይ ስጪ!!]]

أرسل كرسالة
شارك على صفحتي
شارك في المجموعة
fatuma Nuri غيرت صورتها الشخصية
7 شهر
لا يمكن الترجمة

image
أرسل كرسالة
شارك على صفحتي
شارك في المجموعة