UMMA TOKEN INVESTOR

Ibrahim Kedir пайларӗ
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

image
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас
Ibrahim Kedir пайларӗ
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

#ሰበር

ሒዝቦላህ፡ ተቃውሟችን አል-መሊኪያህ የተባለውን ቦታ በተገቢው የጦር መሳሪያ ኢላማ ያደረገ ሲሆን ዛሬ ከሰአት በኋላ ቀጥተኛ ድብደባ ፈጽሟል።

image
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас
Ibrahim Kedir пайларӗ
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

ከዛሬው ጉባኤ የወጣ የጋራ ስምምነት መግለጫ!

🔴 በጋዛ ሰርጥ ላይ ያለውን የእብደት ጦርነት ለማስቆም ታሪካዊ፣ ልዩ እና ቆራጥ ውሳኔ ወስዷል።

🔴 በጋዛ ሰርጥ ላይ ለ17 አመታት የቆየውን ከበባ ለማንሳት ውሳኔ ሰጥቷል።

🔴 የራፋህ ድንበርን በቋሚነት በመክፈት፣ ለነዳጅ፣ ለእርዳታ እና ለህክምና ቁሳቁሶች ምቹ መተላለፊያ እንዲሆን ተወስኗል።

🔴 የጋዛ ሰርጥ መልሶ ግንባታን የሚያግዝ ፈንድ የጋራ ጥምረት በአስቸኳይ በማቋቋም ከ41 ሺህ በላይ ሙሉ በሙሉ የወደመ መኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም ከ222 ሺህ በላይ በከፊል የወደሙ መኖሪያ ቤቶችን የመንግስት መስሪያ ቤቶችን፣ መስጊዶችን፣ ቤተክርስትያኖችን፣ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመገንባት የወሰነ ሲሆን ይህን የፈፀሙ የጦር ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ እና ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች እና ለሚመለከታቸው ፍርድ ቤቶች ለማቅረብ የአረብ እስላማዊ የህግ አካል ለማቋቋም ተወስኗል።

🔴 የወራሪዋ አምባሳደሮች ከአረብ እና ሁሉም እስላማዊ ሀገራት ማባረር ፣የሀገራቸውን አምባሳደሮች በመጥራት እየተፈጸመ ላለው ወንጀል እና እልቂት ምላሽ እና ይህንን ወራሪ ሙሉ በሙሉ ቦይኮት ለማድረግ ተወስኗል።

🔴 ወራሪውን ከፍልስጤም ግዛት ማባረር፣ ወረራውን ማስቆም እና እየሩሳሌም ዋና ከተማዋ በማድረግ የፍልስጤም ሀገርን ለመመስረት ስምምነት ላር ተደርሷል።

የሙሐመድ ትውልድ From Ultra palestine

#palestine

image
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас
Ibrahim Kedir пайларӗ
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

እማ ቦምብ ሲመታኝ ወድያው ነው የሚ*ገለኝ ወይስ በጣም እያመመኝ ነው የምሞተው? ስሞትስ ብቻዬን ነው የምሞተው ? አይ ሁላችንም አንድ ላይ ነው የምንሞተው የኔ ልጅ።

...

ጁሪ ተጨዋች ሳቂታ፣ ሁሌም በጩኸቷ ቤት የምታደምቅ ልጅ ነበረች፣ ከወ*ረ*ራው በኃላ ግን ምግብ አትበላም እንደ ድሮ፣ ያ ሁላ ሳቅ ጨዋታ የለም፣ እናቷ የድሮ ትዝታዎችን እያነሳች ለማጫወት ብትሞክርም ጁሪ በትካዜ ከመዋጥ ውጪ ከእናቷ ጋር መቦረቅ መጫወት ካቆመች ሰነባበተች፣ ጦ*ርነቱ ካበቃ በኃላ መጀመርያ እንዳደርግልሽ የምትፈልጊው ነገር ምንድነው ? ተብላ በእናቷ ስትጠየቅ... ምንም ነገር አልፈልግም ፣ ይሄ ቦምብ ብቻ ይቁምልኝ፣ሌላ ምንም አልፈልግም። እሱን ብቻ ነው የምፈልገው ....

...

ወደ ደቡባዊ ስፍራ እንድንሰደድ ትዕዛዝ ቢተላለፍም ወደ ደቡባዊ ጋዛ መሄጃ ጎዳናው ሁሉ አስክሬን ነው (ለስደት የሚወጡ ሰዎች መንገድ ላይ በቦምብ ዒላማ ተደርገው ተገለዋል)፣ አስክሬን ማንሳት ስለተከለከለ ጎዳናው ሁሉ በወዳደቁ አስክሬን የተሞላ ነው። መንገድ ላይ በቦምብ የመመታቱን ዕድል ተቋቁሜ እንኳን ጉዞ ብጀምር ልጄን በነዚህ አስክሬን መሃል ይዤ መራመድ እንዴት ይቻለኛል ? ...

...

ይህ የአልጀዚራ ጋዜጠኛዋ ዩምና አል ሰዒድ እና የልጇ ጁሪ አሁናዊ ተጨባጭ ነው ፣ በህይወት ተርፎ መቆየት ከቻሉ ደሞ ለነገ በራሷ ተሰንዶ ሊቀመጥ የሚችልና በሩዋንዳዋ ኢማኩሌ ኢሊባጊዛ 'ለወሬ ነጋሪ መትረፍ' መፃህፍት ተርታ የሚሰለፍ የዘ*ር ማ*ጥፋት ታሪክ ነው ። ከነ ልጇ አትርፎ ለዛ መብቃቱን ካደላቸው...

Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас
Ibrahim Kedir пайларӗ
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

የአሕዛብ ዘመቻ‼️

▬ ▬ ▬ ▬ ▬

ክፍል፦ 1

-------------

(ፁሁፌ ትንሽ ቢረዝምም፣ እናንተም የረጅም ፁሁፍ ፎቢያ ቢኖርባችሁም፤ ታሪኩን ከራሴ ሳልጨምር፣ ሳላጋንን ቁርኣንና ሐዲስ ላይ ብቻ ተርኪዝ በማድረግ አስቀምጣለሁ፤ ታሪኩ ታሪካችን ነውና ታሪኩን ሁላችንም ማወቅ ግዴታችን ስለሆነ ተረጋግታችሁ ሳትሰለቹ አንብቡት!)

||

✍ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በኩፋሩል ቁረይሽ አማካኝነት ወደ መዲና ከተሰዱዱ በኋላ ተውሒድን ለማስተማር ጥበብ የተሞላበት እርምጃዎችን በመውሰዳቸው ምክንያት ፀጥታ ነገሰ። ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እና ሙስሊሞች ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት፣ ተውሒድን ለማስተማር ሁኔታዎቻቸውን ለማበጃጀትና ለማስተካከል ጊዜ አገኙ።

:

ይህ በመሆኑም ከበኒ-ነዲር ዘመቻ በኋላ ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ምንም የተጋፈጣቸው ነገር አልነበረም።

'ይሁን እንጂ!'

ኢሳ (ዓለይሂ ሰላም) «እነዚህ እባቦች!» ያላቸው፣ አሁን ላይ የነብያቶች ምድር የሆነችዋን ሀገር አርዱ-ሻም ፍልስጥየሞችን እየጨፈጨፉ ያሉት አይሁዶች በሙስሊሞች እረፍት ማግኘት አልተደሰቱም።

በ 'ኸይበር' ተረጋግተው ከሰፈሩ በኋላ በስውር እየተንቀሳቀሱ ተንኮል መሸረብ ጀመሩ።

°

በመጨረሻም መዲናውያንን (ሙስሊሞችን) የሚዋጋ በጣም ታላቅ ሠራዊት ከተለያዩ የዓረብ ጎሣዎች ለማሰባሰብ ቻሉ።

:

እንደውም የሲራ ምሁራን እንደሚሉት 20 የአይሁድ ሹማምንትና መሪዎች ወደ ቁረይሾች በመሄድ መዲና ላይ እንዲዘምቱ አነሳሱዋቸው። እነርሱም እንደምረዱዋቸው ቃል ገቡላቸው። ቁረይሾች ተቀበሉዋቸው። ከዚያም ወደ 'ገጥፋን' ሄዱ። እነሱም እሺ በማለት ሀሳባቸውን ተስማሙበት፡፡

ከዚያም በተለያዩ ጎሣዎች ውስጥ ተዘዋውረው የብዙዎቹን ድጋፍ አገኙ።

ከዚያም እነዚህን ሕዝቦች በተቀናጀ መልኩ አንቀሳቅሰው ሁሉም በአንድ ጊዜ መዲና ዳርቻ እንዲደርሱ አደረጉ።

*

የአሕዛቦችን መሰባሰብና ወደ መዲና መንቀሳቀስ መጀመራቸውን ወሬ ሲሰሙ ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሰሓቦቻቸውን አማከሩ።

:

ሰልማን አል-ፋሪሲ (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ) የጠላት ጦር ወደ መዲና ማለፍ እንዳይችል ፈረስ የማያስዘልል ትልቅ ቦይ (ኸንደቅ) እንዲቆፈር ሀሳብ ሰጠ።

ሀሳቡን ወደዱት ተስማሙበት፡፡

:

መዲና በምሥራቅ፣ በምዕራብና በደቡብ አቅጣጫዎች የተቃጠሉ የሚመስሉ ጥቋቁር ድንጋዮች ባሏቸው ኮረብታዎች የተከበበች አገር በመሆኗ በሰሜን አቅጣጫ ብቻ እንጂ የጠላት ሠራዊት ሊገባባት አይችልም።

ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በምሥራቅና በምዕራብ በኩል በሚገኙ ሁለቱ ኮረብታዎች መሃል ጠበብ ያለውን ቦታ (በግምት 1 ማይል ይላሉ ይህን ርዝመት ያለውን ቦታ) መርጠው ቦይ በማስቆፈር ሁለቱን ኮራብታዎች በቦዩ አገናኙ።                

*

ግዜው በጣም ከባድ ነበር‼️

ለየ 10 ሰው 40 ክንድ ርዝመት ያለውን ቦይ እንዲቆፍሩ ተመደበ።

ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በቦዩ ቁፋሮም ሆነ አፈር በማጋዝ ተሳትፏል። ርሃብ፣ ጥም ተፈራርቆባቸውም ነበር።

አነቃቂ ግጥሞችን ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሲገጥሙ ሰሓቦቹ ይቀበሏቸዋል እንደነበር ዘገባዎች ያመላክታሉ።

*

የአሕዛብ ዘመቻ የማይረሳ ልብ ነኪው ትውስታ‼️

------------------------------------------------------------

በቁፋሮው ወቅት ብዙ መከራ አጋጠማቸው ነበር። በተለይም ደግሞ ብርዱና ረሃቡ ጠንቶባቸው ነበር።

አንድ እፍኝ ገብስ ሲመጣላቸው ከሻገተ ሞራ ጋር እየደባለቁ ከጎሮሮ አላልፍ እያላቸው በግድ ይበሉት ነበር።

ሰሓቦች ረሃብ እንደጠናባቸው በማመልከት በረሃብ ምክንያት በሆዳቸው ላይ ያሰሩትን አንዳንድ ድንጋይ ለነቢዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እስከማሳየት ደርሰው ነበር።

ስለ ዘመቻው ርሃብ ሲያወራ አቢ ጦልሃ (ረድየ-ል-ሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ይላል፦

«በጣም ርቦኝ ሆዴ ላይ ያሰርኩትን ድንጋይ አሳየኋቸው፣ እሳቸውም ሆዳቸውን ፈቱ በጣም እርቧቸው ሁለት ድንጋይ አስረው ነበር።»

*

በቁፋሮው ግዜ የታዩ ተዓምራቶች‼️

--------------------------------------------

በቁፋሮው ጊዜ አንዳንድ ተአምራት ታይተው ነበር።

➊ኛ. የምግብ በረከት‼️

በሶሒህ ሐዲስ እንደተወራው፦

ጃቢር (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ) ነብዩን (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ረሃብ እንደጠናባቸው አይቶ መታገስ ስላልቻለ ወደ ቤቱ በመሄድ አንዲት ትንሽ ፍየል አርዶ ባለቤቱ ደግሞ አንድ ቁና ገብስ ፈጭታ አዘጋጁና ጃቢር ነቢዩን (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከተወሰኑ ሶሓቦቻቸው ጋር በድብቅ ጠራቸው።

:

ነብዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ቦዩን በመቆፈር ላይ የነበሩትን አንድ ሺህ ሰሓቦች አስከትለው ወደ ጃቢር ቤት ሄዱ።

የተዘጋጀውን ነገር ሁሉም ሰሓቦቻቸው በልተው ሲጠግቡ የተረፈው ወጥ ከእሳት ላይ መንተክተኩንና ሊጡም መጋገሩን አላቋረጠም ነበር።  

°

በሌላም ዘገባ ላይ፦

የኑዕማን-ቢን-በሺር እህት ለኑዕማን አባትና አጎት አንድ እፍኝ ተምር አመጣች፡፡

ነብዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ተምሩን ወስደው በጨርቅ ላይ ከፋፍለው በማስቀመጥ የኸንደቁን ሰዎች በሙሉ ጠሩዋቸው። ሁሉም በልተው ተመለሱ። የተረፈው ተምር ግን ጨርቁን ሞልቶ ከዳርዳሩ ይወድቅ እንደነበር ተዘግቧል።

*

➋ኛ. የቋጥኙ መሰበር‼️

√ በቁፋሮው ላይ እያሉ ጃቢርንና ከርሱ ጋር የተመደቡትን ሰሓቦች በጣም ጠንካራ ድንጋይ አጋጠማቸው። ነብዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሄደው በመዶሻ ሲመቱት ደቃቅ አሸዋ ሆኖም ነበር።

°

√ በራእንና ጓደኞቹንም እንደዚሁ ትልቅ ድንጋይ ሲያጋጥማቸው ነብዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወርደው «ቢስሚላህ!» በማለት አንድ ጊዜ በዶማ ሲመቱት ብልጭታ በማሳየት 'ገሚሱ' ተሰብሮ ወጣ።

የዛን ግዜም፦

ነብዩ  «አላሁ አክበር የሻምን ቁልፎች ተሰጠሁ፤ ባሁኑ ሰዓት ቀያይ ሕንፃዎቿን እየተመከትኩ ነው።» አሉ።

ሁለተኛ ጊዜ ሲመቱት 'የፋርስን' መከፈት አበሰሩ።

ሦስተኛ ጊዜ ሲመቱ የ'የመንን' መከፈት አበሰሩ። ድንጋዩ ተሰብሮ አለቀ።

*

በሁለቱ ጎራዎች መካከል የነበረው‼️

-----------------------------------------------

✍ቁረይሾች ከተከታታዮቻቸው ጋር 4ሺ ሰዎች ሆነው 3መቶ ፈረሶችንና 1ሺ ግመሎችን በመያዝ ባንድራቸውን ዑስማን-ቢን-ጠልሃ-ቢን-አቢ-ጠልሃ አል-ዐብደሪይ'ን በማስያዝ በአቡ ሱፍያን መሪነት መጥተው 'በጃሩፍና በዘጋባ' መካከል የሩማ ጉርፎች በሚገናኙበት ቦታ ላይ ሰፈሩ።

'ገጥፋኖች' ከነጅ'ድ ተከታዮቻቸው ጋር 6ሺ ሰዎች ሆነው በመምጣት 'በኡሑድ' ተራራ ጎን ቦታው 'ዘነብ ነቅማ' በሚባል ስፍራ ላይ ሰፈሩ።

:

በደንብ እየገባችሁ ከሆነ በአጠቃላይ 10ሺህ ሠራዊት መሆኑ ነው። የዚህ ታላቅ ሠራዊት ወደ መዲና ክልል መግባት ታላቅ ፈተናና አስፈሪ ሆነ፣ ነበርም።

*

✔️ ታሪኩን በሱረቱል አሕዛብ ላይ አላህ አስቀምጦታል።

እንዲህም በማለት ታሪኩ መረሳት እንደሌለበት ገልፆታል፦

إِذْ جَآءُوكُم مِّن فَوْقِكُمْ وَمِنْ أَسْفَلَ مِنكُمْ وَإِذْزَاغَتِ ٱلْأَبْصَـٰرُ وَبَلَغَتِ ٱلْقُلُوبُ ٱلْحَنَاجِرَ وَتَظُنُّونَ بِٱللَّهِ ٱلظُّنُونَا۠۝

image
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас