muhaba sherif Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

muhaba sherif shared a
Translation is not possible.

👉👉👉👉:-የወጣቶችን ጤና እያመሳቀለ ያለው መድሐኒት : *ትራማዶል*

*ትራማዶል የሚባለው የህመም ማጥፊያ መድሐኒት ያለ አግባብ በወጣቶች ኪስ ተዘውትሯል። ከስምንተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በዚህ መድሐኒት ሱስ ተለክፈዋል። መድሐኒቱ ያለ በቂ ምክንያት እና ተዘውትሮ ሲወሰድ ወደ ሱስነት ይሸጋገራል።

*አንድ የገጠመኝ ተማሪ በቀን 26 ትራማዶል ክኒን መውሰድ ደረጃ የደረሰ ነበር። በቀን 26 ማለት ለመውሰድ ቀርቶ ለመቁጠር የሚታክት ነው። ሱስ የማያደርገው የለምና እያደረገ ቆይቷል። ከዚህ ደረጃ የደረሰው በአንድ ቀን አልነበረም። በቀን አንድ ተጀምሮ ቀስ በቀስ መላመድ ስላለው የሚፈለገው የሱስ ቃና ስለማያስገኝ መጠኑን እንዲጨምር በሱስ ትዕዛዝ ሁለት፣ አራት፣ ስድስት፣.....እያለ ሀያ ስድስት ክኒን ላይ ደርሷል።

*የትራማዶል ሱስ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ የሚገኝ አደገኛ የስነ አእምሮ ችግር ነው። ከመድሐኒት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የስነ አእምሮ ችግር የማይነካው ማዕዘን የለም። የግለሰብ ፣የቤተሰብና የማህበረሰብ ጤና፤ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መስተጋብሮችን አደጋ ላይ ይጥላል።

*ትራማዶል ከድንገተኛ  መሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና እክሎች ያስከትላል። በአንድ ግዜ በብዛት ከተወሰደ ለሞት ይዳርጋል። የአንጎል ንዝረት፣የኩላሊት መድከም/መባባስ፣ ለጡንቻ መቅለጥ እና ለከፋ የስነ ልቦና ችግር የሚዳርግ  ነው።

*ችግሩ ትኩረት የተሰጠው አይደለም። ምንም እንኳ በጤና ጥበቃ በኩል መድሐኒቱን ያለ ልዩ ማዘዧ እንዳይታዘዝ የሚል መመሪያ ቢነገርም ተፈፃሚነቱ ላይ ግን አጠያያቂ ነው። ከዚያ ባሻገር ሰፊ የግንዛቤ መድረክ ፈጥሮ የችግሩን አሳሳቢነትና አስከፊነት ማሳወቅ ተገቢ ነው። ትኩረት ይሰጠው።

*ኪኒኑን በመውሰድ ሱሳቸውን ማብረድ ሲሳናቸው በመርፌ መውሰድ ይጀምራሉ። ከዚህ ደረጃ ተደረሰ ማለት በችግር ላይ ሰፊ ችግር ተባዝቶ ለልብና አንጎል የጤና እክል ለሚዳርግ መጥፎ ሁኔታ ይዳርጋል። የልብ በር ኢንፌክሺን በመፍጠር ለእስትሮክ ይዳርጋል።

*እስትሮክ ወጣቶች ላይ ከሚከሰትባቸው መንስኤዎች አንዱ በደም ስር የሱስ መድሐኒት መውሰድ ጋር የተያያዘ ነው። ትራማዶልና መሰል የሱስ አምጪ መድሐኒቶችን በመርፌ መውሰድ ለእስትሮክ ያጋልጣሉ።

*ሱስ ሁሉን አቀፍ የጋራ ትብብርና ቅንጅት የሚፈልግ የአእምሮ ጤና እክል ነው።

👉:-ዶር መስፍን በኃይሉ

@HakimEthio

https://ummalife.com/Meryemhassen

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
muhaba sherif shared a
Translation is not possible.

እኛ ሙስሊሞች ለምንድነው ለመስጂድ አል-አቅሷ ወይም ለሀገር

ፈለስጢን የምንጨነቀው?

1. ለእኛ ሙስሊሞች የመጀመሪያ ቂብላችን ስለሆነ፡፡ (በወንጌል

ዮሃንስ ወንጌል 4፥19 እና

¶በቅዱስ ቁርአን ¶ ደግሞ

ሱረቱል አል በቀራ (2:144) ፣ 3:96 ተጠቅሷል

2. ከካዕባ በስተቀር በቁርአን ውስጥ ስሙ የተጠቀሰው ብቸኛው መስጅድ

ስለሆነ፡፡ ( ሱረቱል አል ኢስራዕ 17:1)

3. በምድር ላይ የተገነባ ሁለተኛው የአላህ ቤት ስለሆነ።

4. የአላህ (ሱ.ወ) ተአምራት የሚታዩበት ቦታ ስለሆነ።

5. በመቶዎች የሚቆጠሩ መልእክተኞችና ነቢያት የተቀበሩበት ስፍራ ስለሆነ፡፡

6. ብዙ የአላህ መልእክተኛ ባልደረቦች (ሰሀቦች) የተቀበሩበት ቦታ ስለሆነ።

7. አላህ (ሱ.ወ) ራሱ የተባረከ ቦታ ብሎ ስለጠራው። (ቁርአን 17:1)

8. 70 ጊዜ በቁርአን ውስጥ ፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመጠቀሱ።

9. መላእክት ከአላህ መልእክት ጋር ይወርዱበት የነበረ ቦታ ስለሆነ፡፡

10. በምድር ላይ ሁሉም የአላህ መልእክተኞች በአንድ ጊዜ በነቢዩ ሙሐመድ

(ሰ.ዐ.ወ) መሪነት ለአላህ (ሱ.ወ) የሰገዱበት ብቸኛው ቦታ ስለሆነ፡፡

:– ሙስሊም እንደ አንድ አካል ነው አንዱ አካል ሲታመም ሌላው አካል

ይታመማል። አንድ ሙስሊም ሲጨቆን እኛም ይሰማናል ያመናል.... ለዛ ነው

በጥቂቱ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
muhaba sherif shared a
Translation is not possible.

ወንድሞች እና እህቶች ኢስላማዊ ማህበራዊ አውታረ መረብ UMMA LIFE ከጓደኞችዎ እና ከሚወዷቸው ጋር ያስተዋውቁ። ሁሉም ሙስሊም የአላህን ህግጋት የሚያከብር የጋራ እና ብቸኛ ማህበራዊ ድህረ ገፃችን መኖሩን ማወቅ አለበት። ይህ ገና ጅምር ነው በቅርቡ ኢንሻአላህ ሁሉም ስለኡማ ህይወት ያወራል። ዱዓ አድርጉ፣ ዜናውን በንቃት አካፍሉ። እናም በፍልስጤም ያሉ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን አትርሳ! አላህ የሙስሊሞችን ሁኔታ ያቅልልን።

https://linktr.ee/ummalife

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
muhaba sherif shared a
Translation is not possible.

መህዲ ማነው?

‹‹መህዲ›› በመጨረሻው ዘመን ከደጃልና ዒሳ መምጣት አስቀድሞ የሚነሳ ታላቅ ‹‹ኸሊፋ›› ነው። ‹‹መህዲ›› የማዕረግ ስሙ ሲሆን ‹‹ሁዳ›› ከሚለው ቃል የተገኘና ‹‹የተመራ ቅን ኸሊፋ›› ማለት ነው። መጠሪያ ሙሉ ስሙ ደግሞ ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ አል-መህዲ›› ነው።

ስለ መህዲ በቁርኣን የተነገረ ምንም ነገር አናገኝም። መረጃዎቹ በሙሉ ከሐዲስ የተገኙ ሲሆን ከሃያ በላይ የተረጋገጡ ዘገባዎች ይገኛሉ። ብዙ የሱንና ዑለማዎች ስለ መህዲ የፃፉ ሲሆን ቲርሚዚና አቡ-ዳውድ ራሱን የቻለ ምዕራፍ ሰጥተውታል።

ከሁሉም ታዋቂው ሐዲስ አቡ-ዳውድ የዘገቡት ሲሆን ነቢዩ (ዐሰወ) እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ትንሳኤ ሊቆም አንድ ቀን ቢቀረው እንኳን አላህ ከቤተሰቤ የሆነን፤ ስሙ ከእኔና ከአባቴ ጋር የሚመሳሰል መሪን ሳያስነሳና በበደል የተዋጠችውን ምድር በፍትህ ሳይሞላት አይተዋትም።››

(አቡ-ዳውድ 4282)

ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው መህዲ የነቢዩ (ዐሰወ) ቤተሰብ ነው። ስሙም የነቢዩን (ዐሰወ) እና አባታቸውን የያዘ ሲሆን ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ›› ወይም ‹‹አህመድ ኢብን አብዱላህ›› ነው። የሚመጣውም ዓለም በዙልም በተዋጠችበት በመጨረሻው ዘመን ሲሆን የአላህን ቃል ከፍ በማድረግ ፍትህን ያነግሳል።

ኡሙ ሰላማ (ረዐ) እንደተናገረችው ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ በፋጡማ በኩል የሚገኝ ቤተሰቤ ነው።›› ብለዋል። ኢብኑል ቀይም ይሄንን ሐዲስ ሲያብራሩ ‹‹መህዲ የሐሰን ዘር ሲሆን አል-ሐሰን ለሙስሊሙ አንድነት ሲሉ ኸሊፋነታቸውን አሳልፈው በመስጠታቸው ምክንያት አላህም በመጨረሻው ዘመን ከቤተሰባቸው ታላቅ ኸሊፋ በማስነሳት ክሷቸዋል።›› ሲሉ ፅፈዋል።

(አቡ-ዳወድ 11/373)

አቡ-ሰዓድ አልኩድሪ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ (ዐሰወ) ስለ መህዲ ገፅታ ሲናገሩ ‹‹ቁመቱ ረጂም፣ ትከሻው ሰፊ፣ አፍንጫው አጠፍ ያለ ነው።›› ብለዋል።

(አቡ-ዳውድ 4265)

መህዲ የሚነሳበትን ቦታ በተመለከተ የተለያዩ ዘገባዎች አሉ። ከፊሎቹ ከሻም ከፊሉ ከኹራሳን ሌላው ደግሞ ከመዲና እንደሆነ ይናገራሉ። ኢብን ከሲር የሁሉንም ሐዲሶች ጥቅል ሀሳብ ሲያስቀምጡ ‹‹የሚነሳው ከምስራቅ ነው። ከዚያም ወደ መካ ይሄዳል። ሰዎችም በከዓባ ዙሪያ ቃልኪዳን ይገቡለታል።›› ብለዋል። እንዲሁም በሌላ መጽሐፋቸው ‹‹በሐዲስ በተጠቀሰው መሰረት ባንዲራው ጥቁር ነው።›› በማለት አብራርተዋል።

(አልቢዳያህ ወልኒያህ 19/63፤ አልፊታን ወልመላሂም 1/49)

ኢማም አህመድ እንደዘገቡት መህዲ መሪነት ሲመረጥ ፍላጎቱም ክህሎቱም አልነበረውም። እናም ‹‹አላህ በአንድ ሌሊት ይመራዋል።›› ብለዋል (ዐሰወ)። ኢብን ከሲር ሐዲሱን ሲያብራሩ፡- ‹‹ይህ ማለት አላህ ይረዳዋል፣ ከዚህ በፊት ያልነበረውን ችሎታም ይሰጠዋል ማለት ነው።›› ብለዋል።

(አህመድ 2/58/ አልፊታን ወልመላሂም 1/29)

መህዲ ኸሊፋነትን ከተረከበ በኋላ ሙስሊም አገራትን በአንድ በማፅናት በቀደመው ኢስላማዊ አስተዳደር ስር ያስገባቸዋል። ከዚያም በቡኻሪ እና ሙስሊም (2897) እንደተዘገበው ከሮማውያን ጋር የመጨረሻው ታላቁ ጦርነት ‹‹አል-መልሃማ አል-ኩብራ›› ይካሄዳል። ሙስሊሞችም ዳቢቅ ላይ ድል ደርጋሉ። ከዚህ በፊት ያልተከፈቱ አገራትንም ይከፍታሉ። ከዚያ በኋላ ሙስሊሞች በየትኛውም ኃይል አይሸነፉም። አላህ አማኞችን ከፍተኛ የሀብት መትረፍረፍ ይባርካቸዋል።

ሸይህ ዑመር ሱለይማን አል-አሽቀር ሐዲሱን መሰረት በማድረግ እንደተናገሩት ‹‹ይህ ጦርነት ከባድ ውድመትን ስለሚያስከትል ዓለም አሁን ካለችው ስልጣኔ ወደኋላ በመመለስ እንደ ጥንቱ በጦር በጋሻ በፈረስ መጠቀም ይጀምራሉ።›› ብለዋል።

(አል-ቂያማህ አስ-ሱግራ 275)

መህዲ ታላቅ ጦርነት አድርጎ ሙስሊሞችን የበላይ ቢያደርግም ጊዜው የቂያማህ ቀን መቃረቢያ በመሆኑ ከባባዶቹ ፊትናዎች ይከሰታሉ። ከእነዚህም መካከል ቀዳሚው የደጃል መነሳት ነው። እሱን ተከትለው የዕጁጅና መዕጁጆች ከጉድጓዳቸው ይወጣሉ። በዚህ ጊዜ አላህ ዒሳን (ዐሰ) ለእርዳታ ይልከዋል።

በሐዲስ እንደተጠቀሰው ዒሳ (ዐሰ) ወደ ምድር የሚወርደው በፈጅር ሰላት ወቅት ነው። ነቢዩ (ዐሰወ) ስናገሩ ‹‹መህዲ ዒሳን አሰግደን ይለዋል። ዒሳም እናንተ መሪዎች መሆናችሁ ከቂያማህ ምልክቱ ነውና አንተ አሰግደን ይለዋል። ዒሳም ከመህዲ ኋላ ተከትሎ ይሰግዳል።›› ብለዋል።

(ሙስሊም 225)

ከዚያ በኋላ ዒሳ ከሙስሊሞች ጋር በመሆን የዕጁጆችንና ደጃልን በመጋደል በአላህ ዕርዳታ ያጠፋቸዋል። ነቢዩ (ዐሰወ) እንደተናገሩት ‹‹ሙስሊሞች ለሰባት ዓመታት ያህል የየዕጁጆችን አጥንት ቀስትና ጋሻ ለማገዶነት ይጠቀሙበታል።

መህዲ በኸሊፋነት የሚቆይባቸው ዓመታት ‹‹ሰባት›› እንደሆኑ አብዛኛዎቹ የሐዲስ ምሁራን ይናገራሉ። ከእነሱ መካከል አንዱ የኢብኑ ማጃህ ሲሆኑ ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ ሰባት አጭር ጊዜያትን ይቆያል።›› ማለታቸውን ዘግበዋል።

(ኢብን ማጃህ 4039)

አል-መህዲ እስኪመጣ ሙስሊሙ ጂሐድን በመተው መጠበቅ ይኖርበታል? ለሚለው ጥያቄ ሸይህ ሙሐመድ ሷሊህ አል-ሙነጂድ በፈትዋ ገፃቸው እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ከጂሐድ መዘንጋት ከከባባድ ወንጀሎች አንዱ ነው። አላህ ያዘዘው ሁሉም የራሱን ግዴታ እንዲሞላ ነው። መህዲ የራሱ ጂሐድ አለው። ይሄም ህዝብ የራሱን ጂሐድ ማድረግ ግዴታው ነው።

#አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፡-

وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ كُلُّهُ لِلَّهِ ۚ فَإِنِ انتَهَوْا فَإِنَّ اللَّهَ بِمَا يَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሏቸው፡፡ ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡

[ ሱረቱ አል-አንፋል - 39 ]

®ምንጭ"face book.ድ/ገጽ"

©ኮፒ ራይት"

#ዘላለም_ኗሪ_አላህ_ነው

Send as a message
Share on my page
Share in the group
muhaba sherif shared a
Translation is not possible.

✨እንተዋወስ❗

🍃ኢባዳ_በስንት_ይከፈላል ?🍃

  🍃🍃ምን_ምን_ናቸው?🍃🍃

➻ኢባዳ  በሶስት ይከፈላል።

💐እነርሱም ፦💐

➻⇘ ኢባደቱል ቀልቢያ

➻⇘ ኢባደቱል ቀውሊያ

➻⇘ ኢባደቱል አመሊያ

✅የቀልብ አምልኮ:-

⇛ ኢልም

⇛ ኢማን

⇛ ኢኽላስ

⇛ ኢህሳን

⇛ ተውኩል

⇛ ተቀዋዕ

⇛ ሙአባህ

⇛ ሰብር ናቸው።

✅የምላስ አምልኮ:-

⇛ ተውበት

⇛ ሸሃዳ

⇛ ዱአ

⇛ ዳዋዕ

⇛ ዚክር

⇛ ቁርአት ናቸው።

✅ የድርጊት አምልኮ:-

⇛ ሰላት

⇛ ፆም

⇛ ዘካ

⇛ ሃጅ

⇛ ጅሃድ ፊ ሰብሊላህ ናቸው

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group