Translation is not possible.

ኢትዮጵያ #ድምፀ_ተአቅቦ ያደረገችበት የተመድ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባኤ ተካሄደ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዓርብ ምሽት በእስራኤል እና ሃማስ የጋዛ ጦርነት ጉዳይ  አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ አካሂዷል።

በዚህም ጉባኤ በ " ዮርዳኖስ " አቅርቢነት በጋዛ " አስቸኳይ የሰብአዊ ተኩስ አቁም " እንዲደረግ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ ነበር።

የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ጥሪ የቀረበበት የውሳኔ ሀሳቡ ፦

- በ120 ድጋፍ፣

- በ14 ተቃውሞ

- በ45 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።

በዚህም መሰረት ተመድ በጋዛ አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

የውሳኔ ሃሳቡን ከተቃወሙት ውስጥ አሜሪካ ፣ እራሷ እስራኤል ፣ ሃንጋሪ ፣ ኦስትሪያ ይገኙበታል።

ድምፅ ተአቅቦ ካደረጉት መካከል ደግሞ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ፣ ጀርመን ፣ ካናዳ፣ ግሪክ፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ስውዲን፣ ኢራቅ፣ ጃፓን፣ ጣልያን፣ ሕንድ ፣ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩክሬን፣ ቱኒዝያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዛምቢያ ይገኙበታል።

የተመድ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ የተካሄደው በእስራኤል እና ሃማስ መካከል ጦርነቱ ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ነው

መልእክቱ እዲዳረስ ላይክ & ሼር አድርጉት

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group