Translation is not possible.

ነቢዩን ﷺ በህልማችን ካየናቸው እነሱ መሆናቸውን በምን ማረጋገጥ እንችላለን?

ነቢዩ ﷺ «በህልሙ ያየኝ የእውነት አይቶኛል። ሸይጧን በእኔ መመሰል አይችልምና።» ብለዋል።

(ቡኻሪይ 6994 / ሙስሊም 2268)

በዚህም ዑለማዎች ሸይጧን በሶሂህ ሐዲሶች በተገለፀው የነቢዩ ﷺ ትክክለኛ መልክ ተመስሎ በህልም መምጣት እንደማይችል ተስማምተውበታል። ይህም ሸይጧን በነቢዩ ﷺ ተመስሎ እየመጣ ሰዎችን እንዳያሳስት አላህ የዋለልን ፀጋ ነው።

ነገርግን አንዳንዴ ሸይጧን ሽማግሌ፣ ሽበታቸው የበዛና መልከመልካም አይነት ሰው ተመስሎ በመምጣት ነቢዩ ﷺ ነኝ በማለት ለማታለል ሊሞክር ይችላል።

♦️ ይህ ሲሆን ሰውየው ህልሙ ከአላህ ይሁን ከሸይጧን ማረጋገጫ የሚችለው በህልሙ ያያቸውን ሰው በሶሂህ ሐዲሶች ከተገለፀው ከነቢዩ ﷺ ትክክለኛ መልክ ጋር በማመሳከር ነው።

ኢብን ሲሪን ስለዚሁ ሲናገሩ «በህልሙ ያየኝ የእውነት አይቶኛል ማለት በእውነተኛ መልካቸው አይቷቸው ከሆነ ማለት ነው።» ብለዋል።

(ቡኻሪይ 6993)

ኢብን ሐጀር እንደዘገቡት ሰዎች ወደ ኢብን ዐባስ በመሄድ ነቢዩን ﷺ በህልማቸው እንዳዩ ሲነግሯቸው «መልካቸው ምን ይመስላል?» በማለት ይጠይቃቸው ነበር። ለአብነት ዐሲም ኢብን ኩላቢ ሲናገሩ «አባቴ ወደ ዐብዱላህ ኢብን ዐባስ ሄደና በህልሙ ነቢዩን እንዳያቸው ነገረው። ኢብን ዐባስም «መልካቸው ምን ይመስላል?» በማለት ጠየቀው። አባቴም «ሐሰን ኢብን ዐሊይን ይመስላሉ» አለው። ኢብን ዐባስም «በትክክል አይተሃቸዋል።» አለው።» ብለዋል።

(ፈትህ አል-ባሪ 12/383)

በተመሳሳይ የዚድ ኢብን አል-ፋሪሲ ሲናገር እንዲህ አለ «ነቢዩን በህልሜ አየኋቸውና ለኢብን ዐባስ ነገርኩት። እሱም «ያየኸው ሰው ምን እንደሚመስል ልትነግረኝ ትችላለህ?» አለኝ። እኔም ያየሁትን ገለፅኩለት። እሱም «ነቢዩን መንገድ ላይ ብታያቸው እንኳን ከዚህ በላይ ልትገልፃቸው አትችልም።» በማለት እነሱ መሆናቸውን አረጋገጠልኝ።»

(አሽ-ሸማኢል 412)

እንዲሁ ኢብን ሲሪንም አንድ ሰው ነቢዩን ﷺ በህልሙ እንዳያቸው ከነገራቸው «መልካቸው ምን ይመስላል?» በማለት ይጠይቁታል። ሰውየውም የነቢዩ ﷺ ያልሆነ ሌላ መልክ ከነገራቸው «አላየሃቸውም» ይሉት ነበር።

(ፈትህ አል-ባሪ 12/384)

♦️ ነቢዩን ﷺ በትክክለኛ መልካቸው ማየት አለበት ሲባል ታዲያ በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ሆነው ሊሆን ይችላል። ኢብን ሐጀር ስለዚሁ ሲናገሩ፡-

«በወጣትነት ወይም በትልቅነት ዘመናቸው በነበራቸው መልክ ሊያያቸው ይችላል። ነገርግን በትክክል እነሱ በወቅቱ ከነበራቸው መልክ ጋር አንድ መሆን አለበት። ምሳሌ ሊሞቱ አቅራቢያ በነበራቸው መልክ ካያቸው የሽበት ፀጉራቸው ብዛት ከ20 እንደማይበልጥ ማረጋገጥ አለበት።» ብለዋል።

(ፈትህ አል-ባሪ 12/386)

(ነቢዩ ﷺ መልካቸው ምን ይመስላል? የሚል ጥያቄ ያለው ካለ ይሄንን አለማወቅ ተገቢ ስላልሆነ ዛሬውኑ ዑለማዎችን መጠየቅ አለበት)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group