ፀጋችንና መከራችን ቢወዳደሩ
አላህ በቁርኣኑ «ፀጋዬን ብትቆጥሩ አትዘልቋትም።» ብሎናል።
እኛ ሰዎች ደግሞ ደካሞች ነንና አላህ ከዋለልን ፀጋ ይልቅ መከራችን የበዛ ይመስለናል። ነገርግን በተጨባጭ የአላህ ፀጋ ከሚገጥመን መከራ በላጭ ብቻ ሳይሆን ሊወዳደርም አይችልም። ለምሳሌ፦
♦️ የታመማችሁበትንና በጤና የኖራችሁበትንም ቀናት ቁጠሩ። የታመምንባቸው ቀናት ቢቆጠሩ አንድ ዓመት ቢሞሉ ነው። ብዙ ዓመታትን ግን አላህ በጤና አኑሮናል።
♦️ የተራባችሁበትንና የበላችሁበትንም ቀናት ቁጠሩ። የተራብንባቸው ቀናት ቢደመሩ አንድ ዓመት ቢሞሉ ነው። ብዙ ዓመታትን ግን አላህ መግቦናል።
♦️ የታረዛችሁበትንና የለበሳችሁበትን ቀናት ቁጠሩ። ልብስ ያጣንባቸው ቀናት ቢደመሩ አንድ ዓመትም አይሞሉም። ብዙ ዓመታትን ግን አላህ አልብሶናል።
♦️ የተጨነቃችሁበትንና ሰላም የሆናችሁበትን ቀናት ቁጠሩ። የተጨነቅንባቸው ቀናት ቢደመሩ አንድ ዓመት ቢሆኑ ነው። ብዙ ዓመታትን ግን አላህ በሰላም አኑሮናል።
🔷 የትኛውም መከራ ቁጠሩ። አላህ ከሰጣችሁ ፀጋ ጋር በፍፁም ሊወዳደር አይችልም። የአላህን ፀጋ እኛ ጨርሰን ባናውቀውም ነገርግን ቆጥረን የምንጨርሰው አይደለም። የገጠመው መከራ ግን ተቆጥሮ ያልቃል። እናም መከራችን እንደበዛ አድርገን አናስብ።