Translation is not possible.

ዕድሜ በዱዓዕ ሊጨምር ይችላል?

ዕድሜ አላህ ቀድሞ ከቀደራቸው ነገሮች አንዱ ሲሆን፦

«ዕድሜው ከሚረዘምም አንድም አይረዘምም ከዕድሜውም አይጎደልም በመጽሐፉ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጂ።» ብሏል።

(ፋጢር 11)

ሆኖም አንድ ሰው ዕድሜው እንዲረዝምለት ዱዓዕ ማድረግ ይችላል። ነቢዩ (ﷺ) ስለዚሁ ሲናገሩ፦

«ሪዝቁ እንዲጨምርና ዕድሜው እንዲረዝም የፈለገ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።» ብለዋል።

(ቡኻሪይ 2067/ ሙስሊም 2527)

♦️ አላህ ዕድሜውን ቀድሞ ከወሰነው በኋላ እንዴት ሊረዝምለት ይችላል? ለሚለው ጥያቄ፦

ኢብን ተይሚያህ ሲያብራሩ «አላህ መለዒካዎችን ዕድሜውን እንዲፅፉ ያዛቸዋል። ከዚያም “ዝምድናውን ከቀጠለ በዚህ ያህል ዕድሜ አረዝምለታለሁ” ይላቸዋል። መለዒካዎቹ ወደፊት ዕድሜው ይጨምር አይጨምር አያውቁም። አላህ ግን ያውቃል። ከዚያም አላህ በወሰነው ጊዜ ሞቱ ይመጣበታል። ብለዋል።

(መጅሙዕ አል-ፈታዋ 8/517)

♦️ ኢማም ነወዊይ ደግሞ ዕድሜ ስለሚጨምርበት መንገዶች ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፦

«ዕድሜ በሶስት መንገዶች ሊጨምር ይችላል።

❶ አላህ ዕድሜውን በረካ ወይም መልካም የሚሰራበት ሊያደርግለት ይችላል።

❷ አላህ በዕድሜው ላይ ተጨማሪ ዕድሜ ሊሰጠው ይችላል። ምሳሌ 60 የነበረውን 100 ሊያደርገው ይችላል።

➌ ሰውዬው ከሞተ በኋላ የሚቀጥል መልካም ስራ ሊሰጠው ይችላል።

አላህ የበለጠ ያውቃል!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group