UMMA TOKEN INVESTOR

About me

https://t.me/collectionhamza

Наган дахаан йохтахам.

የለቱ ወጋገን ካድማሱ ቢታይም

ፀሀይ ልኳን አውቃ ፈንጥቃ ብትወጣም

ውዷ ተረበሸው ውስጣቸው ሲተክዝ ማየት አልቻለችም።

የኡማቸው ጉዳይ እንቅልፍ ነስቷቸው

ለይሉን አገላብጦ ቢያንዘፈዝፋቸው።

ከ ሉል አይኖቻቸው እንባ እያጎረፉ

ሽቅብ ወደ'ሰሚዕ ኡመቴን ኡመቴን እያሉ ለፈፉ።

በዐለመ ፍጥረት ከዘረጋው ሁላ

የሳቸው ውድያ ቢበልጥበት መውላ።

ያን ታላቅ መልዐክ ከሰባት ሰማያት አስጨብጦ ላከ

በዑመትህ ጉዳይ አላሳዝንህም እያለ ሰበከ።

.... ፊዳከ አቢ ወኡሚ ወነፍሲ ያ ረሱለላህ......

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

ልቦች ተላተሙ ቃላት ተሸነፉ

ሀሳቦች ነጎዱ ብዕሮች ነጠፉ።

ጉልበት ቢያንሳቸው ቢጎላቸው አቅሙ

በእፍኝ ቃላት የፍቅርን ትርጉም በፍቅር መሰየሙ

"አንቱ የፍቅር ትርጉም ፣ የፍቅር ህላዌ ... አሰላሙ ዐለይክ"

ٱللَّٰهُمَّ صَلِّ عَلَىٰ مُحَمَّدٍ وَعَلَىٰ آلِ مُحَمَّد

.............. ሶሉ ዓለ ነቢ ..............

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

እኔ የምልህ ...... እስከመቼ "ነገ" እያልክ ትኖራለህ .... እስከመቼስ ለዛሬ ጀርባህን ሰተህ ትችለዋለህ .... ነገ የዛሬ ና የትላንት ድምር ነችና ዛሬህን በመልካም ትላንት ፤ ነገህን ደግሞ በበጎ ዛሬ አበርታ... ነገ እገልጣቸዋለዉ ያልካቸውን የህይወትህ ገፆች ዛሬውኑ ዳስሳቸው .. በፅኑ ቃኛቸው.... ምክንያቱም አንድ ነገር ግልፅ ነው ...ነገ የሌለው ዛሬ ወደሁላችንም በር እየገሰገሰ ነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

sources of POWER

በምድር ላይ ሁለት አይነት የ ሀይል (power) ምንጮች አሉ። የመጀመርያው ጥልቅና ስምጥ የሀብትና resource ክባቴ (ማካበት) ሲሆን

ሁለተኛው ደግሞ ለሀብትና resource ድልብ ጀርባ መስጠት ፣ፊት መንሳት ነው።

የመጀመርያው:-

. አጎንባሽ ካድሬ ይሰጥሀል ... ደጀን ወዳጅ ይነፍግሀል (

. የትኩረት ማዕከል ያደርግሀል ... የትኩረት ዒላማህን ያስ'ትሀል

.የግዜን በር ያስቃኝሀል ... መዝለቅያ ቁልፉን ይነጥቅሀል

. የገዢነትን ሞፈር ያስጨብጥሀል....ለራሱ ቀንበር ያመቻችሀል

ሁለተኛው :-

.የብዙሀንን ጎሪጥ ያስኮመኩምሀል .... በጥቂት ደጀኖች ያካብብሀል

. የመታየት ከፍታን ይነሳሀል .... የእይታ ጥግህን ይጠርግልሀል

. በቁሳዊ ባርነት ያስጨንቅሀል ..... የነፃነትህን ቁልፍ ያመላክትሀል

ግና .... ፈልጎ ተንሰፍስፎ ማጣትንና "አለፈልግም"ን ለዩልኝ ...i mean... look back to the "ኸይሩ ቀርኒ" ትውልድ...🤔🤔

https://t.me/collectionhamza

Telegram: Contact @collectionhamza

Telegram: Contact @collectionhamza

ይህ የ ሀምዛ ነስረዲን የፅሁፍ ስራዎች የሚቀርቡበት channel ነው።ግጥሞች መነባንቦችና ወግ-ጣጥፎችን ተደራሽ ለማድረግ ይሞከርበታል።ሰናይ ግዜ...?
Send as a message
Share on my page
Share in the group
HAMZA NESREDIN Сhanged his profile picture
7 month
Наган дахаан йохтахам.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group