medina helil Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

medina helil shared a
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
medina helil shared a
Translation is not possible.

ጓደኛህ ማንነው?

—————

ለዲንህ ዋጋ በመስጠት መልካም ጓደኛ ምረጥ‼

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ጓደኝነትን በተመለከተ እንዲህ ብለዋል:-

“በአንድ የአዕምሮ ባለቤት በሆነ ሰው ላይ ባልደረቦቹ ላይ ባለው ነገር ማስተንተን ግድ ይለዋል!:

ጓደኞቹ መጥፎ ጓደኞች ናቸውን?

ከነሱ ይራቅ እነሱ ከጊንጥ የበለጠ ጠላቶቹ ናቸው።

ወይስ ጓደኞቹ የመልካም ባለቤት ናቸው?:

በመልካም የሚያዙትና ከመጥፎ ነገር የሚከለክሉት፣ እንዲሁም ለሱ የመልካም ነገርን በር የሚከፍቱለት ከሆኑ፣ እነሱን በመወዳጀት ላይ ይበርታ።” [አል-ቀውሉ'ል ሙፊድ 1/363]

ወገኖቼ ሆይ! ብዙ እህትና ወንድሞቻችን ለመበላሸት ዋንኛው ምክንያት በተለይ በዚህ ጊዜ መጥፎ ጓደኛ መያዝ ነው። እንዲሁም ለጓደኛ መጥፎ ይሁን ጥሩ አገናዝቦ ግምት አለመስጠት ነው።

ለመጥፎ ጓደኛ ለመጥፎነቱ ምንም ግምት ሳይሰጡት ይቀራረቡታል ሸሪዓ ወደማይፈቅዳቸው ነገሮች ይዟቸው ይሄዳል፣ ባህሪያቸው እንዳለ ይበላሻል።

ለጥሩ ጓደኛ ምንም ግምት ሳይሰጡት በትንሽ በትልቁ ይጋጩና ይርቁታል በዚያው ክፉ ጓደኞች ይጣበቁበታል፣ ከዚያ ከጥሩ ጓደኛ ወደ መጥፎ ጓደኛ ይዘዋወራል፣ እነዚያ መጥፎ ጓደኞች ወደ ዝሙት፣ አስካሪ መጠጥ፣ ቁማር ወደ መጫወትና ወደ ክህደት ይወስዱታል፣ ለዚህም ነው ታላቁ ነቢይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) “አንድ ሰው በጓደኛው እምነት ላይ ነው፣ አንዳችሁ ይመልከት የትኛው እምነት አሸንፎ እንደሚወርሰው” ያሉት። [አቢ ዳውድና ትርሚዚይ በሶሂህ ሰነድ ዘግበውታል]

በዚህ መልኩ ነው ሙስሊም እህቶችና ወንድሞች በአሁን ጊዜ ለምናየው ውድቀትና የስነ-ምግባር መበላሸት የተዳረጉት። በተለይ እህቶች በት/ት በምናምን ሰበብ ከከሀዲ ሴት ጋር ጓደኛ ትሆናለች፣ በዚያች ከሀዲ ሴት ምክንያት የሚመጣው ከሀዲ ወንድ አስተዋውቂኝ ይላታል በዚህ መልኩ እንዲህ እያለ ሙስሊሟን ሴት ወደ ዝሙት ይጠራታል። ከዚህ በኋላ ማንም ምንም ቢያናግራት የማትሰማ ልበ ደረቅ ሆና የዚህ ወንድ ጭራ ተከታይ ትሆናለች፣ በዚያው ወደ ክህደቱ ይጠራታል (አላህ ይጠብቀንና) ይህን ክህደት እንደ ተራ ነገር ትቀላቀለዋለች።

በመንሀጅም ጉዳይ እንዲሁ ነው። ብዙ ሰዎች ከመንሀጀ ሰለፍ የመውጣትና ዋልለው የመቅረታቸው አንዱ ምክንያት የጓደኛቸውን መንሀጅና ከማን ጋር ትስስር እንዳለው አለማወቃቸው ነው። ደብቆ የያዘውንና ማንነቱን የደበቀበትን የዝንባሌ አመለካከቱን ቀስ በቀስ በልባቸው ብዥታውን እየጣለባቸው አቅጣጫ ያስታቸውና የሆነ ፊትና በሚፈጠርበት ወቅት ይዟቸው ዳር ይወጣል። ጓደኛችሁ ምን አይነት አመለካከት እንዳለው፣ ከማን ጋር ትስስር እንዳለውና ትላንት ምን አይነት ሰው እንደነበረም በጥንቃቄ ማየት ግድ ይላል።

የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህን ፍሩ!!! አላህን ፍሩ!!! አላህን ፍሩ!!!

ለጓደኝነት ግምት ሰጥታችሁ ሸሪዓ እንድትርቁት ያዘዛችሁን ጓደኝነት ራቁት ተጠንቀቁት‼ እንድትቀጥሉት ያዘዛችሁን ጓደኝነት አጥብቃችሁ በመልካም ነገርና በትእግስት ላይ እየተመካከራችሁ አላህን እስክትገናኙ ቀጥሉ።

ወላሂ! ከላይ በጠቀስኩላችሁ መልኩ ክህደትን የታቀፉ በርካታ ወንድና ሴቶች ገጥመውኛል!! በተለይ ሴቶች፣ ከሀዲ ወንዶች በዝሙት ካስረገዟቸው በኋላ ኩፍሩንም ተቀብለው መኖር የጀመሩ በርካቶች ናቸው።

ይህ ሁሉ ዋንኛ መነሻው ጓደኛን አለመምረጥና ክፉ ጓደኞችን አለመራቅ ነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
medina helil shared a
Translation is not possible.

8 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group