UMMA TOKEN INVESTOR

bint abesha Changed her profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
bint abesha shared a
1 year Translate
Translation is not possible.

🚩የእስራኤል ጋዛ ጦርነት የአለምን አሰላለፍ ይቀይር ይሆን?

👉የካይሮው ጉባዬ ተጠናቀቀ

~~~RN05~~~

.

ከተመሰረተችበት 1948 ጀምሮ እስራኤል ከአረብ ጎረቤቶቿ ጋር የነበራት ግንኙነት በግጭት የተሞላ ነው። በተለይ ማክሰኞ በጋዛ ከተማ የሚገኘዉን አል-አህሊል ሆስፒታል መታ የበርካታ ሰዎች ህይወት እንዲቀጠፍ አድርጋለች ከተባለ በኋላ በክልሉ የሚገኙ አብዛኛዎቹ የአረብ መንግስታት እስራኤልን ተጠያቂ ነች ሲሉ ከሰዋል። በሌላ በኩል እስራኤል ሆስፒታሉ የተመታው በኔ ሳይሆን አንዴ ከሀማዝ አንዴ ደግሞ ከታጣቂው የፍልስጤም ድርጅት ኢስላሚክ ጂሃድ የተተኮሰ ሮኬት ያስከተለው ውጤት ነው ስትል ትናገራለች።

.

እ.ኤ.አ ኦክቶበር 7 ሃማስ እስራኤል ላይ ያደረሰዉን ያልተጠበቀና አስደንጋጭ ጥቃት ተከትሎ እስራኤል እየወሰደችው ባለው የጅምላ ጭፍጨፋ እርምጃ አብዛኞቹ የአረብ ሀገራት (ከእስራኤል መንግስት ጋር ለአስርት አመታት ውይይት እና ትብብር ሲያደርጉ የቆዩትን ጨምሮ) - ለጥቃቱና ለሰቆቃው መባባስ "እስራኤል በአካባቢው ለዘመናት የምታራምደው የአፓርታይድ አገዛዝ ዉጤት ነው!" በማለት ተጠያቂ አድርገዋታል። በተለይም እስራኤል በያዘችው ዌስት ባንክ እያካሄደች ያለውን የሰፈራ ግንባታ እና ከጋዛ ሰርጥ ጋር በተያያዘ የምታደርገውን እንቅስቃሴ በዋቢነት ይጠቅሳሉ።

.

በአሁኑ ሰአት የአረብና የሙስሊም በዝ ሃገራት ከወትሮው በተለየ በጋራ መቆም የአካባቢውን የዘመናት ችግር በግል ሳይሆን በጋራ መፍትሄ መፈለግ አስፈላጊ ነው ብለው ያመኑ ይመስላሉ፡፡ ለዚህም ማሳያው በፍልስጤሙ የተመድ ተወካይ መሪነት ሰሞኑን የአረብ ሃገራት በጋራ በመሆን እስራኤልን በመክሰስ ለፍልስጤማዊያን የጋራ ድምጽ ሲያሰሙ መቆየታቸዉ፣ ብሎም እጅግ ባለተለመደና በማይጠበቅ መልኩ የመሳርያ እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ሙሉ ለሙሉ ከእስራኤልን ጎን የቆሙቱን የአለማችንን አዲስ አሰላለፍ (new world order) መሪን ጆ ባይደንን የጆርዳን፣ የግብጽና የፍልስጤም መሪዎች አናናግርም ማለታቸው የሚጠቀስ ሲሆን በተጨማሪም ዛሬ የተጠናቀቀዉን የአረብ እና የሙስሊም ሃገራት ከወትሮው በተለየ ብዛት የተሳተፉበትን የካይሮ የሰላም አስቸኳይ ጉባዬ በግብጽ ማካሄዳቸው ነው፡፡

.

በዚህ ጉባዬ ላይ የተለያዩ የአፍሪካ፣ የአዉሮፓ፣ የእስያ ሀገራት መሪዎችና የዉጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የተሳተፉ ሲሆን አሜሪካ እንደ ከዚህ በፊቱ አልሳተፍም ብላ ንቃ ሳትተው ራስዋን በአምባሳደሯ በኩል መወከሏ የካይሮው ጉባዬ ከወትሮው የተለየ እንደሆነ ማሳያ ተደርጎ መውሰድ የሚቻል ይመስለናል፡፡

.

የካይሮው የጋዛ የሰላም ጉባዬ ተሳታፊዎች በስተመጨረሻም እስራኤል ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጋዛ ላይ የምታደርገውን የቦምብ ጥቃት ያወገዙ ሲሆን በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል ለዘመናት ሲካሄድ የነበረዉን ግጭት ለማስቆም አዲስ ጥረቶች እንዲጀመሩ ጠይቀዋል።

.

የዮርዳኖሱ ንጉስ አብዱላህ የእስራኤልን እርምጃ "አለም አቀፋዊ አፈና!" ሲሉ ያወገዙት ሲሆን የእስራኤል እና የፍልስጤም ችግር መፈታት ያለበት በፍትሃዊነት ብቻ ነው ሲሉ አሳስበዋል።

.

በዛሬው እለት ከፍተኛ ትኩረት የሳበዉና ሚድያዎችም በሰፊው ሽፋን የሰጡት የፍልስጤሙ ፕሬዝደንት ማህሙድ አባስን "ፍልስጤማውያን አይፈናቀሉም፤ መሬታቸውንም ለቀው ወደ የትም አይወጡም!" የሚለዉን ንግግራቸዉን ነበር፡፡

.

ይህም የማህሙድ ሃሳብ የብዙዎችን ትኩረት የሳበው በተለይ እስራኤል "ሰላማዊ ፍልስጤማዊያንን ላለመጉዳት" በሚል የጋዛ ነዋሪዎች ወደ ደቡብ ጋዛ እንዲሄዱ ብቻ ሳይሆን ወደ ግብጽም እንዲፈልሱ ግፊት ማድረጓ ይታወሳል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ፍልስጤማዊያን አንዴ መሬታቸዉን ለቀው ከወጡ ተመልሰው የመግባት መብትን እስራኤል መንፈጓን ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡

.

በመሆኑም ይህ የማህሙድ አባስ ንግግር ሲተረጎም "አሁንም አስወጥታ ሃገር አልባ ልታደርገን ማሰቧን እናውቃለን፣ ይህንን እቅዷን ደግሞ አንፈጽምላትም!" ማለታቸው እንደሆነና ይህም በመሆኑ እስራኤል ያላት እድል ወይ ወረራዉን ማቆም አልያም በጅምላ ህዝቡን መፍጀት ስለሆነ፣ ይህ ደግሞ ያለዉን ፍጥጫ የሚያጠናክረው በመሆኑ እንደሆነ ይገመታል፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

2 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

6 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group