UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

☑️ የጁሙአ ቀን ከሚሰሩ መልካም ስራዎች ውስጥ አንዱ በውዱ ነብያችን ላይ ሰለዋት ማውረድ ነው። በስራም ሆነ በማንኛውም ሁኔታ ውዱእ ቢኖረንም ባይኖረንም ሰለዋት ማውረድ ትልቅ ምንዳ ያስገኛል።

የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል።

♦️ በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ ሰው፦

🔹በአስር እጥፍ አላህ በሱ ላይ ያወርድበታል

🔹አስር መጥፎ ሰራዎች ይሰረዝለታል

🔹አስር ደረጃዎች ከፍ ይደረጋል

📚الباني (صحيح النسائي) جـ1 ص415

አል-ጁሙዓ‼️

▬ ▬ ▬ ▬ ▬

✍አሏሁ'መ ሶሊ ወሲሊም ወባሪክ ዓላ ነቢይና ሙሀመድ‼️

«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،

كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،

اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،

كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሞት የህይወት መጨረሻ ሳይሆን የፀጋ ጅምርት ነው፣ አሊያም የስቃይና የዘላለማዊ ቅጣት ጅምርት ነው ጉዞህን ወዴት ማድረግ እንዳለብህ በማትፀፀትበት መልኩ አሁኑኑ ወስንና ተዘጋጅተህ ጠብቀው ‥

(كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَنْ زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ)

" ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው. ከእሳትም የተራቀና ገነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ

ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጂ ሌላ አይደለችም ፡፡"

[ዒምራን 185]

ዱንያ በፀጋዎቿ አታላህ ዛሬ ነገ እያለችህ እያዘናጋችህ ዘላለምህን ልትወጣበት በማትችለው ወጥመድ ውስጥ እንዳትከትህ ተጠንቀቅ !!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

“የተከበሩ ዶክተር ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) ፍልስጤማውያንን በተመለከተ የመከሩት አስደናቂ ምክር...”

✭✭✭✭✭✭✭✭✭✭

ለተከበሩት ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) የሚከተሉት ጥያቄዎች ቀረበላቸው፡

“በአሁኑ ሰዓት በፍልስጥኤማውያን ወንድሞቻችን ላይ እየተደረገ ያለው መከራና ሰቆቃ...ለነሱ (ለፍልስጤማውያን) ዱዓ ማድረግ፣የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣ከነሱ ጋር መታገል ይቻላልን?!”

ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ አሉ፦

“በሙስሊሞች ላይ ለሚደርሰው ችግር ዱዓ ማድረግ ግዴታ ነው። በንብረትም ሆነ ቁሳዊ ድጋፍ ማድረግ ግዴታ ነው። ለነሱ የሚጠቅመው ይህ ነው።” ይህንኑ ተከትሎ ለሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፡

“አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁና ይህ ጠያቂ እንዲህ ይላል፡ “የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግና እንዲሁም ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ጂሃድ ከማድረግ ይቆጠራልን?!፤ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በአላህ መንገድ ላይ እንደመታገል ይቆጠራልን?!” ከዚያም ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ፦

“በሰለማዊ ሰልፍ ምንም አይነት የሚገኝ ጥቅም የለውም፤ይልቅስ ከሰላማዊ ሰልፍ የሚገኘው ትርምስ፣ግርግር፣ረብሻ...ነው። ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ጠላቶችን ምን የሚጎዱት ነገር አለ?! ምንም አይጎዱም። በጎዳናዎች ላይ ሰልፎችን ማድረግ ጣላቶችን የሚያስከፋ ሳይሆን የሚያስደስት ተግባር ነው። ኢስላም የተቀደሰ ንፁህ የሆነ ሐይማኖት ነው፤ እንዲሁም ኢስላም በዘፈቀደና በስሜት የሚያስኬድ ሐይማኖት አይደለም። ኢስላም በሸራዓዊ እውቀት ተመርኩዞ የተገነባ እምነት ነው። ኢስላም የትርምስና የውዝግብ ሐይማኖት አይደለም፤ይልቁንም ለተጎዱ ሙስሊሞች ለነሱ የሚያስፈለገው: ዱዓ ማድረግ፣ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ማድረግ፣ ወታደራዊ...ድጋፎችን ማድረግ ነው። ስለዚህ በእነዚህም ሆኑ በሌሎች ጉዳዮች ሙስሊሞች የሰለፎችን መንሐጅ ነው መከተል ያለባቸው። ኢስላም በሰላማዊ ሰልፍ ጋጋታና ረብሻ አይደለም እዚህ ደረጃ የደረሠው፤ እንዲሁም ድምፆችን ከፍ በማድረግ፣ ንብረቶችን በማውደም አይደለም ኢስላም የተገነባው። እነኝህ ተግዳሮቶች ለኢስላም ጉዳት እንጂ ምንም አይነት ጠቃሜታ የላቸውም። እነኝህና የመሳሰሉት ተግዳሮቶች ለሙስሊሞች ውጤቱ የከፋ ነው። በል እንዳውም ካህዲያኖች ይደሰታሉ፤ ሙስሊሞችን ጎዳናቸው፣ አሰቃየናቸው...እያሉ ደስታቸውን ይገልፃሉ...”

ምንጭ፦ [From his lesson on the night of the 2nd/Safar/1423H (15 April 2002), in his open meeting after Maghrib prayer, and also broadcast on Paltalk. This was translated from the live lecture at the time.]

የሸይኽ አቡ ዒያድ (ሀፊዘሁሏህ) እንግሊዝኛ ፅሁፍ በዚህ ሊንክ ያገኙታል።⤵️

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

*ፊቅህን ለማወቅ*

በየ ሆስፒታሉ ያንተን አይነት ኑሮ መኖርን ሚመኝ ሞልቷል፡፡

በየእስርቤቱ ያንተን ነፃነት የሚናፍቅ ሞልቷል፡፡

በየ ማስጠለያው ያንተን አይነት ማረፊያ ፈላጊ ሞልቷል፡፡

በቀብር ላይ ያሉ ሁሉ ደግሞ ያንተን ክፍት ሰዓት ናፋቂዎች ናቸው ...

ስለዚህ ያንተ ህይወት(ኑሮ) ምንም እንኳን እንደ አንተ እይታ የተበላሸ ቢሆንም ብዙዎች ግን ያንተን አይነት ህይወት የሚመኙ ሞልተዋል፡፡!!

.

منقول

Send as a message
Share on my page
Share in the group
abduljelil ahmedin abu henif Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group