UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

👉በሳምንቱ የሰማነው ምርጥ ነገር!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በትግራይ በነበረው ጦርነት ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት በእርቅ ከፈቱ በኋላ የመጅሊሱ ልዑካን ቡድን አባላት በክልሉ ዚያራ አድርገው ነበር በቆይታቸውም ከክልሉ መጅሊስ ጋራ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰበትን ታሪካዊውን የ " አል ነጃሺ መስጂድ "ን ጎብኝተዋል።

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ አደም በወቅቱ እንዳሉት " ነጃሺ ያለ ኢትዮጵያ ሙስሊም ምንም ነው፤ የሚለማው ታሪኩም የኢትዮጵያ ሙስሊም ነው " ብለዋል።

የፌዴራል መጅሊሱ ፕሬዝዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም በበኩላቸው " ነጃሺ ታሪካችን ብቻ ሳይሆን ምልክታችን ነው እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደቀደመ ቁመናው እንመልሰዋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በመካከል የነበራቸውን ችግር በይቅርታ ከፈቱ በኃላ ግንኙነታቸውን ሉ በሙሉ ወደነበረበት መልሰዋል።

በጉብኝታቸው ከክልሉ መጅሊስ አመራሮች በተጨማሪ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር መወያየታቸው የተነገረ ሲሆን በጦርነት ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ላሉ እና በድርቅ ለተጎዳው ህዝብ ድጋፍ ሰጥተው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

የተደረገው ድጋፍ የጥሬ ገንዘብ፣ የመድሃኒትና የእህል ሲሆን የርክክብ ስነ-ሰርዓቱ ትላንት በመቐለ ከተማ ተከናውኗል።

ድጋፉ በዝርዝር ምን ይመስላል ?

1ኛ. እህል ➡ 5,700 ኩንታል በቆሎ/እህል ብር 24 ሚልዮን የሚያወጣ።

2ኛ. መድሐኒት ➡ 1 ኮንተይነር 40 ፊት መድሐኒት ብር 40,200,000 ብር የሚያወጣ።

3ኛ. ለአልነጃሺ ትራንስፎርመር ➡ 3 ሚልዮን ብር

4ኛ. ለሌሎች ➡ 1.2 ሚልዮን ብር

ጠቅላላ ብር 67 ነጥብ 2 ሚልዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ለትግራይ ህዝብ መደረጉ ተነግሯል።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🚨 ኢትዮጵያ ከባድ አደጋ ተጋርጦባታል!

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች መግለጫ አውጥተዋል።

መግለጫቸው ፤ በአውሮፓ ኅብረት እና በአፍሪካ፣ በካሪቢያንና በፓስፊክ ሀገራት መካከል የተፈረመውንና የሳሞአ ስምምነት በመባል የሚታወቀውን የንግድና የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነት የተመለከተ ነው።

ጉባኤው ስምምነቱ ተካተውበታል ያላቸውን ጎጂ ሀሳቦች በዝርዝር አስፍሯል።

ከነዚህም መካከል ፦

- በስምምነቱ አንቀፅ 36.2 ላይ የተጠቀሰው የወሲብና የተዋልዶ ጤናና መብቶች" ("Sexual and Reproductive Health and Rights") የሚለው ሐረግ በቀጥታ ፦

* #ከግብረሰዶም መብቶች፤

* ከፆታ መቀየር፤

* ከውርጃ፤

* ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትና ግልሙትናን ሕጋዊ ከማድረግ በቀጥታ የተያያዘ መሆኑ በአውሮፓ ፓርላማና በዓለም የጤና ድርጅት የመረጃ ምንጮች ላይ በግልፅ መቀመጡ፤

- በስምምነቱ የአፍሪካ ፕሮቶኮል አንቀፅ 40.6 ላይ በአህጉሪቱ ለሚገኙ ልጆችና ታዳጊዎች ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (Comprehensive Sexuality Education) የተባለ እጅግ አደገኛ ኢግብረገባዊና ልቅ የወሲብ ትምህርት እንዲማሩ አስገዳጅ መሆኑ ለዚህም በዩኔስኮ የተዘጋጀውና እጅግ አደገኛ ይዘት እንዳለው የተረጋገጠው መተግበርያ "International Technical Guidance on Sexuality Education” በስም ተጠቅሶ መቀመጡ፤

- የፆታ ትንኮሳን (gender based violence) ማስቀረት በሚል በጣም አሻሚ የሆነ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን ለማስረፅ እንዲረዳው በሰነዱ በበርካታ ክፍሎች ውስጥ " አካታች " (inclusive) በሚሉ ቃላት ተሸፍኖ እንዲገባ የተደረገ መሆኑ፤

- በበርካታ ሥፍራዎች የተጠቀሰው "Gender" የሚለው ቃል ወንድና ሴት ተብሎ እንደሚተረጎም በስምምነቱ በግልጽ ባለመቀመጡ ይልቁንም በርካታ ጾታዎች እንዳሉ በማስመሰል ሀገራትን የሚያደናግሩባቸው እንደ (sexual orientation እና gender identity)ን የመሳስሉ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን የያዙ ዶክመንቶች በስም ተጠቅሰው በስምምነቱ ውስጥ መካተታቸው፤

- ስምምነቱ የወላጆችን መብት የሚጥስና የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እሴቶችን አደጋ ላይ የሚጥሉ አንቀፆችን የያዘ ስለመሆኑ በሰነዱ ላይ ከተደረገ የኤክስፐርቶች ጥልቅ ጥናት ተረድተናል... የሚሉት ይገኙበታል።

ጉባኤው በነዚህ እና ሌሎች ጎጂ ምክንያቶች ፦

➡ መንግስት የሳሞአ የንግድና የኢኮኖሚ የአጋርነት ስምምነትን በርካታ ጎጂ ጎኖች እንዳሉት በማመን ከዚህ ስምምነት #ኢትዮጵያ ራሷን እንድታገልል በማድረግ መንግስታዊ ኃላፊነቱንና አደራውን በተግባር እንዲወጣ በአጽንኦት ጠይቋል።

➡ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በሥሩ ያሉ የሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የስምምነት ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የቀረቡትን በተለይም ፦

° ከሰብኣዊ መብቶች፣

° ከወሲባዊና የተዋልዶ ጤናና መብቶች፣

° ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት፤

° አካታችነት እና መሰል በሰነዱ የተካተቱ አንቀጾች ወይም ይዘቶች ከግብረሰዶማዊነትና ጾታን ከመቀየር እንዲሁም ከልቅ ወሲብና ከውርጃ ጋራ በቀጥታ ተያያዥነት ያላቸው ጽንስ ሃሳቦች መሆናቸውን በመረዳት ይህንን እጅግ አደገኛ ስምምነት ባለማጽደቅ ህዝባዊና ታሪካዊ አደራውን እንዲወጣ በአጽንኦት ጠይቋል።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🚨 ደቡብ አፍሪካ

የደቡብ አፍሪካ የአለም አቀፍ ግንኙነት ሚንስትር ናሌዲ ፓንዶር በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ ያወጣው ዓለም አቀፉ የጦር መንጀለኞች ፍርድ ቤት እስራኤል በጋዛ ላይ በፈፀመችው የጦር መንጀል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ላይ ለምን የእስር ትዕዛዝ አላወጣም የሚል ጥያቄ ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ቢያቀርቡም ከዋና አቃቤ ህግ ከሪም ኻን ምላሽ እንዳላገኙ ገለፁ።

የደቡብ አፍሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ከሳምንት በፊት በኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣ ለዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቧል።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

What is wrong with Germany?

First they did Holocaust on Jews.

Now they support Holocaust on Palestinians in stead of regreting on their previous Holocaust.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ጀርመን "ዘረኛው የእስራኤል መንግስት በጋዛ ንፁሀን ሲቪሎች ላይ የፈፀመውን የዘር ማጥፋት መደገፏን" ናሚቢያ ውድቅ አደረገች።

"ጀርመን በናሚቢያ ለተካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ መሆኗን ጨምሮ ለተባበሩት መንግስታት የዘር ማጥፋት ስምምነት ቁርጠኝነትን የመግለፅ ሞራል ሊኖራት አይችልም በጋዛ እየተካሄደ የሚገኘው አዲስ ሆሎካስት ነው ብላለች ናሚቢያ"

የናሚቢያ ፕረዚደንት ጂንጎብ የጀርመን መንግስት የእስራኤልን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመከላከል እና በአለም አቀፍ የፍትህ ፍ/ቤት ፊት ለእስራኤል ለመከራከር ያሳለፈውን ወቅታዊ ውሳኔ እንደገና እንዲያጤነው ጠይቀዋል።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group