👉በሳምንቱ የሰማነው ምርጥ ነገር!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በትግራይ በነበረው ጦርነት ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት በእርቅ ከፈቱ በኋላ የመጅሊሱ ልዑካን ቡድን አባላት በክልሉ ዚያራ አድርገው ነበር በቆይታቸውም ከክልሉ መጅሊስ ጋራ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰበትን ታሪካዊውን የ " አል ነጃሺ መስጂድ "ን ጎብኝተዋል።

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ አደም በወቅቱ እንዳሉት " ነጃሺ ያለ ኢትዮጵያ ሙስሊም ምንም ነው፤ የሚለማው ታሪኩም የኢትዮጵያ ሙስሊም ነው " ብለዋል።

የፌዴራል መጅሊሱ ፕሬዝዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም በበኩላቸው " ነጃሺ ታሪካችን ብቻ ሳይሆን ምልክታችን ነው እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደቀደመ ቁመናው እንመልሰዋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በመካከል የነበራቸውን ችግር በይቅርታ ከፈቱ በኃላ ግንኙነታቸውን ሉ በሙሉ ወደነበረበት መልሰዋል።

በጉብኝታቸው ከክልሉ መጅሊስ አመራሮች በተጨማሪ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር መወያየታቸው የተነገረ ሲሆን በጦርነት ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ላሉ እና በድርቅ ለተጎዳው ህዝብ ድጋፍ ሰጥተው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

የተደረገው ድጋፍ የጥሬ ገንዘብ፣ የመድሃኒትና የእህል ሲሆን የርክክብ ስነ-ሰርዓቱ ትላንት በመቐለ ከተማ ተከናውኗል።

ድጋፉ በዝርዝር ምን ይመስላል ?

1ኛ. እህል ➡ 5,700 ኩንታል በቆሎ/እህል ብር 24 ሚልዮን የሚያወጣ።

2ኛ. መድሐኒት ➡ 1 ኮንተይነር 40 ፊት መድሐኒት ብር 40,200,000 ብር የሚያወጣ።

3ኛ. ለአልነጃሺ ትራንስፎርመር ➡ 3 ሚልዮን ብር

4ኛ. ለሌሎች ➡ 1.2 ሚልዮን ብር

ጠቅላላ ብር 67 ነጥብ 2 ሚልዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ለትግራይ ህዝብ መደረጉ ተነግሯል።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group