Translation is not possible.

የእስራ*ል ሀይሎች በምድር ውግያ ሀማስን በአመታት እንኳ ማጥፋት አይችሉም ተባለ።

ጋ-ዛ የቆዳ ስፋቷ የአዲስ አበባን ግማሽ አያክልም። ተራራ የለ ሸለቆ አባጣ ጎርባጣ ድንጋይ ቋጥኝ የለ መሬቱ አሸዋማና ለም መሬት ነው። በዛ ላይ በዛች ትንሽ መሬት 2.3 ሚሊዮን ህዝብ ተጨናንቆ ይኖራል። ያ ደግሞ ሁሉም አይነት የጦር መሣርያ ቴክኖሎጂ በጁ ለያዘው የእስራ*ል አየር ሀያል ጋ-ዛን በአየር ለማረስ ውሀ በብርጭቆ እንደመጠጣት ቀላል ሆኖላታል። ስለዚህ የእስራ*ል አየር ሀይል የጋ-ዛ ሰማይ ላይ እንደፈለገ መዋኘት ችሎዋል።

የምድሩ ግን እንደዛ አደለም። የተለየ ጉዳይ ነው። የጋ-ዛ መሬት ለስላሳ ስለሆነ ሀማስ ለአመታት የውስጥ ለውስጥ ጉድጓድ እንደ ፍልፈል ሲቆፍር ነው የሰነበተው።

አሁን ሰሜን ጋ-ዛ የገባው የእስራ*ል እግረኛም የገጠመው ይህንኑ ነው።

ሰሜን ጋ-ዛ ሲገባ ያን ያህል በጣም ከባድ መከላከል ያልገጠመው የእስራ*ል ሰራዊት እንደ ሸረሪት ድር ወደ ተቆፈሩት ጉድጓዶቹ በገባ ቁጥር የገጠመው ፈተና ግን ከባድ ነው።

የእስራ*ል ሰራዊት ጉድጓዶቹን ለመቆፈር ወራት ይፈጅበታል ያንን ሲያደርግ ግን ሀማ-ስ እንደገና ሌላ ጉድጓድ እየቆፈረ መዋጋቱን ይቀጥላል ስለዚህ ነገሩ ፈተና ነው ይላሉ የእስራ*ል ተንታኞች።

የጉድጓዶቹ ጥልቀት ከ 20-80 ሜትር ጥልቅ ነው እንደ ጉድጓዱ ሁኔታና ቦታ ቢለያይም። ጋ-ዛ ውስጥ የተቆፈሩ ጠመዝማዛ ጉድጓዶች ጠቅላላ ርዝመት እስከ 400 ኪ.ሜ ይሆናል። የአዲስ አበባ ግማሽ በማያክል ቦታ ያ ሁሉ ርዝመት ያለው ጉድጓድ መቆፈር ምን ያህል ጉድጓዱ ጠመዝማዛ ውስብስብና ጥልፍልፍ መሆኑን ያሳያል።

አንዳንዶቹ ጉድጓዶች oxygen የውሀ ማጠራቀሚያ አላቸው መብራት ያላቸውም ብዙ ናቸው። የመሣርያ ምግብ መጋዘን እና የስልክ ኔትወርክ ጭምር ያላቸው ጉድጓዶች ብዛት ቀላል አደለም። የሀማ-ስ ተዋጊዎች ድንገት ከጉድጓድ ወጥተው ጥቃት ሰንዝረው ወደ ጉድጓድ ስለሚመለሱ ወዴት እንደገቡ መፈለግም ከባድ ነው በተለይ በማታ። ታጋቾቹ የሚገኙትም እዛ ነው ተብሎ ይታሰባል።

የእስራ*ል ሠራዊት ጋር በቴክኖሎጂ ስለማይመጣጠኑ ሀማ-ሶች ካሏቸው አማራጮች አንዱ እንደዚ አይነት ዘዴዎችን መቀየስ ነው።

ሀማ-ሶች እንደዚ አይነት ጉድጓድ የመቆፈር ልምድ ካዳበሩ ቆይተዋል። የጋ-ዛ ገበሬዎች ከጥንት ጀምሮ ውሀ ለማውጣት በእጅ ጥልቅ ቁፋሮ የመስራት ጥበብ አላቸው።

ከባህርም አየርም ምድርም ታፍና ባለችው ጋ-ዛ ለአመታት የሀማ-ስ ታጣቂዎች ብዙ የሠው ጉልበትና ጊዜ ሚጠይቀውን እና እጅግ አደገኛ የሆነውን "ከተማ ስር ሌላ ከተማ" የተባለውን የጉድጓድ ኔትወርክ ለመገንባት የተገደዱት ምግብ መድሀኒት ሸቀጣሸቀጥ ነዳጅና መሣርያን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮችን ለማስገባትና ወደ ፊት ጦርነት ቢጀመር ጠላት ጋር ለረጅም ጊዜ የሽምቅ ውግያ ለመዋጋት ውስጥ ለውስጥ በሰው ሀይል ከተቆፈሩ ጉድጓዶች ውጭ ሌላ ምርጫ ስላልነበራቸው ነበር።

እነዚህ ጉድጓዶች ለጋ-ዛ ነዋሪዎች የደም ስር ነበሩ ማለት ይቻላል። ከታች እንደምታዩት የተለያዩ አስፈላጊ ሸቀጦች በጎች ፍየል ከብት ግመል ጭምር በነዚ ጉድጓዶች ነበር ሚገቡት። የሆነ ጊዜ አምበሳ ሁላ ለፓርኪንግ ተብሎ መግባቱ ይነገራል።

እስራ*ል ከአየር ላይ የምትጥለው ቦምብ ወደ መሬት ውስጥ በጣም ጠልቆ ሰርስሮ መግባት ስለማይችል ያላት ብቸኛ አማራጭ የእግረኛ ሰራዊት መጠቀም ኢንጅነሮችና የፈንጂ ባለሙያዎችን ይዛ የጉድጓዱ መጀመሪያና መጨረሻ ድረስ እዛው ቦታው ድረስ ሄዶ በሀይለኛ ፈንጂዎችና ማሽነሪዎች እየደረመሱ ማፈራረስ ነው ይላሉ ተንታኞች።

ያንን ስታደርግ ደግሞ የጉድጓዶቹን መውጫ መግቢያ የሚያውቁት የሀማ-ስ ተዋጊዎች አንዴ ከፊት ከኋሃ ከቀኝ ከላይ ከሰር እያሉ በተለያዩ ስልቶች የእስራ*ልን ሰራዊት ፈተና ያከብዱበታል ስለዚህ ነገሩ አደገኛና ከባድ ነው ይላሉ ተንታኞች።

አሜሪካ ኢራቅና አፍጋኒስታን ስትደበድብ ለሷ በጣም ቀላል ነበር። ሆኖም በምድር ገብታ የተዋጋች ጊዜ ነው እግረኛ ሰራዊቷ የተሸነፈው። እስራ*ልም ተመሣሣይ ነገር ይገጥማት ይሆን?

ምንጭ- ሙሉ ዘገባው የ Al jazeera ነው

(ውድ አንባቢያን ፔጃችን ተደራሽነት በከፍተኛ ደረጃ restricted ስለሆነ ላይክና ሼር በማድረግ ተደራሽ እንድታረጉ እናሳስባለን)

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group