Husniya Sultan Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ስሙ ተቀይሯል‼

============

✍ በጠቅላይ ሚኒስተሩ ባለቤት በቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው አስተባባሪነት በሼይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ አማካኝነት በአዲስአበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የተገነባው ሼይኻ ፋጢማ ቢንቲ ሙባረክ የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ስሙ ወደ ብርሃን ዓይነ ስውራን የአዳሪ ትምህርት ቤት መቀየሩን ዛሬ በቦታው የተገኙ ወንድሞች ታዝበዋል።

ትምህርት ቤቱ ምንም እንኳን የፊት ለፊት በሩ ላይ \"ሼይኻ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት\" የሚል ቢሆንም ውስጥ ላይ ሲገባ ስሙ ተቀይሮ \"ብርሀን የዓይነ ስውራን 2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤት\" ወደሚል ስም መቀየሩ ታይቷል።

በትምህርት ቤቱ የነበረውን የሶላት ክልከላ አስመልክቶ የአቃቂ ቃሊቲ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት በስፍራው በመገኘት የሚመለከታቸው አካላትን ለማነጋገር ቢሞክረም ጉዳዩ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የመጣ በመሆኑ ምንም አይነት ምላሽ አንሰጥም ብለዋል። ዛሬ ርዕሰ መምህሩ ባይኖርም ምክትሉ ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ እንደሆነና ማናገር እንደማይፈልግ አሳውቋል።

ዕድሉን አግኝተው ትምህርታቸውን ለመከታተል በማዕከሉ የገቡ ሙስሊም ዓይነ-ስውራን ተማሪዎች ሰላት እንዳይሰግዱ እንዲሁም ምንም አይነት ኃይማኖታዊ እንቅሰቃሴ ማድረግ እንዳይችሉ መከልከላቸውን በመግለፅ የሚመለከተው አካል በተለይ የአዲስ አበባ መጅሊስ እና የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የሚመለከታችሁ ሁሉ ድምፅ እንሁናቸው። ይህ በኛው ሰው ገንዘብ የተገነባን ተቋም አለመጠቀም ነውር ነው። ንቀትም ነው። መጅሊስ ይህን ማስፈፀም አለመቻሉ ትልቅ ድክመት ነውና ያስብበት።

||

t.me/MuradTadesse

Send as a message
Share on my page
Share in the group
3 months Translate - Facebook
Translation is not possible.
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሌላ ነገር ላስተዋውቃችሁ‼

===================

✍ ያው የመጀመሪያ ድግሪዬን ያጠናቀቅኩት ከAAU በኤሌክትሪካልና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ (ኮምፒዩተር ስትሪም) ስለነበር፤ አሁን ላይ ከመደበኛ ሥራዬና ትምህርቴ ውጭ በማገኘው ትርፍ ጊዜዬ ከተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት ትዕዛዞችን እየተቀበልኩ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ድረ ገፆችንና ችግር ፈች ሲስተሞችን (አፖችን) እሠራለሁ።

አለፍ ሲልም በዘርፉ እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ባሉ ታላላቅ የሃገራችን ተቋማት ውስጥ በነርሱ ግብዣ መሠረት Restrict Competitive Bid (RCB) ላይ እሳተፋለሁ።

ከሠራኋቸው ድረ ገፆች መካከል ለዛሬ ለናሙና ያክል መቀመጫውን በመዲናችን አዲስ አበባ ላደረገው BetAddis Properties ለተሰኘ የሪል ስቴት ኤጀንት ያበረከትኩትን ይህን ድረ ገፅ ላጋራችሁ።

ድረ ገፁን በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ።

www.betaddisproperties.com

ገባ በሉና ጎብኙት፤ ትወዱታላችሁ ብዬ አስባለሁ።

ልክ እንደዚህ አይነት ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ድረ ገፆች (ዌብሳይቶች) ስትፈልጉ፤ በውስጥ መስመር ወይም በቴሌግራም t.me/Murad_Tadesse ላይ የምትፈልጉትን አይነት ዌብሳይት ወይም ሲስተም በመጥቀስ ልታናግሩኝ ትችላላችሁ። በድረ ገፁ ላይ የተካተቱ ኮንተንቶችን ጭምር (ኮንተንት ለሌላችሁ) በማካተት ልክ እንደ ቤት አዲስ ይሠራላችኋል።

በፈለጋችሁበት ጊዜ፣ በፈለጋችሁት መልኩ፣ የድርጅታችሁን ችግር በሚቀርፍና ሥራውን በሚያዘምን መልኩ፤ ስትፈልጉ በግለሰብ ደረጃ ስትፈልጉ በተቋም ደረጃ እሠራላችኋለሁ – ኢንሻ አላህ። ለትምህርት ተቋማት፣ ለጤና ተቋማት፣ ለኤጀንሲዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት… ወዘተ።

BTW, እኔ ጋ ድረ ገፅ ወይም ሲስተም ስታሠሩ እግረ መንገዱን ተቋማችሁ በገፆቼ ላይም ይተዋወቃልስ¡

ተመርቀን ሥራ አጣን ለምትሉ ወንድምና እህቶች ብዙ ጊዜ የቴክ ፊልዶች ላይ ብታተኩሩ ትጠቀማላችሁ የምለው ያለውን ነገር ስለማውቀው ነው። እጅግ በጣም በርካታ ሥራዎችን ከሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ ታገኛላችሁ። በተለይ ደግሞ ቋሚ ሥራችሁ አድርጋችሁ ከያዛችሁት ያዋጣችኋል። በርቱ! ተማሩ፣ አስተምሩ፣ ጠቃሚ ነገር ስታገኙ ለራሳችሁ ብቻ ጥቅሙን ከመደበቅ ሌሎችም እንዲጠቀሙ ሃሳብ ተቀያየሩ።

ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌሎች ለተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት የሠራኋቸውን ድረ ገፆችና ሲስተሞች አጋራችኋለሁ።

ከቴክኖሎጂ መስኮችና መሰል ጠቃሚ ዱንያዊ ሐላል የቢዝነስ ነክ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሃሳቦችን ለማንሳት እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ሥራዎቼን ለማስተዋወቅ የከፈትኩትን አዲሱን የቴሌግራም ቻነል ብትቀላቀሉት ይመከራል።

Join:

√ የቻነል ሊንክ፦ https://t.me/STEMwithMurad

√ የግሩፕ ሊንክ፦ https://t.me/STEMwithMuradGroup

*

በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ነገሮች ቀላል ናቸው። አላህ ያግዘን እንጂ ምኞታችን ከፍ ያለ ነው፤ ታላላቅ ነገሮችን መሥራት። ኢንሻ አላህ አብረን ከፍ እንላለን።

||

t.me/MuradTadesse

image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አዲስ የፌስቡክ ገፅ‼

===============

✍ ላለፉት 8 አመታት ስጠቀምበት የነበረውን የፌስቡክ ፕሮፋይሌን ባለፈ እሁድ «UN - Useless Nations» በሚለው ልጥፌ የተነሳ የሜታ ኩባንያ ሙሉ በሙሉ ዘግቶታል። UN በፈለስጢን ጋዛና እስራኤል ጉዳይ በድጋሜ ባካሄደው ስብሰባ አሜሪካ እንደተለመደው ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ጦርነቱ እንዲቀጥል አድርጋለች። ተመድ አሁንም በርሷ መንገድ ስለሆነ UN - Useless Nations ብዬ ነበር።

አይሁዳዊው የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ከ12 ሚሊዮን በላይ ተከታታይ የነበረውን የጋዛን ገፅም በቋሚነት ዘግቶታል። እስራኤልን የሚነቅፉና ፈለስጢንን የሚደግፉ ልጥፎችን የሚለቁ ገፆችን ተከታትሎ በመዝጋት ላይ ይገኛል።

ያኛው አካውንት የመመለስ እድሉ 1% ገደማ ስለሆነ በነዚህ አዲስ ገፆቼ ፌስቡክ ላይ እገኛለሁ።

የ5000 ገደቡ እስኪሞላ ድረስ friend request እቀበላለሁ።

Profile: https://www.facebook.com/MuradTadesseOfficial

Page: https://www.facebook.com/MuradTadesseOfficialPage

በተጨማሪም በቴሌግራም ቻነሌ: t.me/MuradTadesse ላይ አለሁ።

የእስራኤል ወዳጆች (ምዕራባውያንና አውሮፓውያን) ፈለስጢንን የሚደግፍ ድረ ገፆችንና የቴሌቪዥን ሳተላይት ስርጭቶችን ጭምር እያሳደዱ በመዝጋት ላይ ስለሆኑ የኔን ገፅ በመዝጋታቸው አልገረምም።

ኢንሻ አላህ! እኛም አንፋታቸውም።

©: ፎቶ: ወንድም ዐብዱ-ር'ረሒም አሕመድ (ሃሩን ሚዲያ) የፌስቡክ ፕሮፋይሌን በሜታ ኩባንያ ሎጎ ቀይረው ሲዘጉት አጋጣሚ አይቶ በስክሪን ሹት ያስቀረው ምስል

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የፈለስጢንና እስራኤልን ጉዳይ በተመለከተ ስላለው እውነታና እኛ እንደ ሙስሊም ማድረግ ስላለብን ነገሮች ሸይኽ Ilyas Ahmed ትናንት እሁድ በኢማሙ አሕመድ መስጅድ በነበረው የፈታዋ ፕሮግራም ላይ ያስተላለፈው ሰፊ መልዕክት‼

ከግንዛቤ ፈጠራ ጀምሮ ብዙ ቁም ነገሮች ስላሉት ብታዳምጡትና ነገሩን ከስር መሠረቱ ለማያውቁ ይጠቅም ዘንድ ብታሰራጩት መልካም ነው።

©: Video Credit: Huda Multimedia

የቪድዮው ሳይዝ ለበዛባችሁ በድምፅ ብቻ ለማዳመጥ ከፈለጋችሁ!

https://t.me/MuradTadesse/32501

||

https://ummalife.com/MuradTadesse

t.me/MuradTadesse

59 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group