Translation is not possible.

ሌላ ነገር ላስተዋውቃችሁ‼

===================

✍ ያው የመጀመሪያ ድግሪዬን ያጠናቀቅኩት ከAAU በኤሌክትሪካልና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ (ኮምፒዩተር ስትሪም) ስለነበር፤ አሁን ላይ ከመደበኛ ሥራዬና ትምህርቴ ውጭ በማገኘው ትርፍ ጊዜዬ ከተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት ትዕዛዞችን እየተቀበልኩ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ድረ ገፆችንና ችግር ፈች ሲስተሞችን (አፖችን) እሠራለሁ።

አለፍ ሲልም በዘርፉ እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ባሉ ታላላቅ የሃገራችን ተቋማት ውስጥ በነርሱ ግብዣ መሠረት Restrict Competitive Bid (RCB) ላይ እሳተፋለሁ።

ከሠራኋቸው ድረ ገፆች መካከል ለዛሬ ለናሙና ያክል መቀመጫውን በመዲናችን አዲስ አበባ ላደረገው BetAddis Properties ለተሰኘ የሪል ስቴት ኤጀንት ያበረከትኩትን ይህን ድረ ገፅ ላጋራችሁ።

ድረ ገፁን በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ።

www.betaddisproperties.com

ገባ በሉና ጎብኙት፤ ትወዱታላችሁ ብዬ አስባለሁ።

ልክ እንደዚህ አይነት ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ድረ ገፆች (ዌብሳይቶች) ስትፈልጉ፤ በውስጥ መስመር ወይም በቴሌግራም t.me/Murad_Tadesse ላይ የምትፈልጉትን አይነት ዌብሳይት ወይም ሲስተም በመጥቀስ ልታናግሩኝ ትችላላችሁ። በድረ ገፁ ላይ የተካተቱ ኮንተንቶችን ጭምር (ኮንተንት ለሌላችሁ) በማካተት ልክ እንደ ቤት አዲስ ይሠራላችኋል።

በፈለጋችሁበት ጊዜ፣ በፈለጋችሁት መልኩ፣ የድርጅታችሁን ችግር በሚቀርፍና ሥራውን በሚያዘምን መልኩ፤ ስትፈልጉ በግለሰብ ደረጃ ስትፈልጉ በተቋም ደረጃ እሠራላችኋለሁ – ኢንሻ አላህ። ለትምህርት ተቋማት፣ ለጤና ተቋማት፣ ለኤጀንሲዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት… ወዘተ።

BTW, እኔ ጋ ድረ ገፅ ወይም ሲስተም ስታሠሩ እግረ መንገዱን ተቋማችሁ በገፆቼ ላይም ይተዋወቃልስ¡

ተመርቀን ሥራ አጣን ለምትሉ ወንድምና እህቶች ብዙ ጊዜ የቴክ ፊልዶች ላይ ብታተኩሩ ትጠቀማላችሁ የምለው ያለውን ነገር ስለማውቀው ነው። እጅግ በጣም በርካታ ሥራዎችን ከሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ ታገኛላችሁ። በተለይ ደግሞ ቋሚ ሥራችሁ አድርጋችሁ ከያዛችሁት ያዋጣችኋል። በርቱ! ተማሩ፣ አስተምሩ፣ ጠቃሚ ነገር ስታገኙ ለራሳችሁ ብቻ ጥቅሙን ከመደበቅ ሌሎችም እንዲጠቀሙ ሃሳብ ተቀያየሩ።

ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌሎች ለተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት የሠራኋቸውን ድረ ገፆችና ሲስተሞች አጋራችኋለሁ።

ከቴክኖሎጂ መስኮችና መሰል ጠቃሚ ዱንያዊ ሐላል የቢዝነስ ነክ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሃሳቦችን ለማንሳት እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ሥራዎቼን ለማስተዋወቅ የከፈትኩትን አዲሱን የቴሌግራም ቻነል ብትቀላቀሉት ይመከራል።

Join:

√ የቻነል ሊንክ፦ https://t.me/STEMwithMurad

√ የግሩፕ ሊንክ፦ https://t.me/STEMwithMuradGroup

*

በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ነገሮች ቀላል ናቸው። አላህ ያግዘን እንጂ ምኞታችን ከፍ ያለ ነው፤ ታላላቅ ነገሮችን መሥራት። ኢንሻ አላህ አብረን ከፍ እንላለን።

||

t.me/MuradTadesse

image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group