Translation is not possible.

አዲስ የፌስቡክ ገፅ‼

===============

✍ ላለፉት 8 አመታት ስጠቀምበት የነበረውን የፌስቡክ ፕሮፋይሌን ባለፈ እሁድ «UN - Useless Nations» በሚለው ልጥፌ የተነሳ የሜታ ኩባንያ ሙሉ በሙሉ ዘግቶታል። UN በፈለስጢን ጋዛና እስራኤል ጉዳይ በድጋሜ ባካሄደው ስብሰባ አሜሪካ እንደተለመደው ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ጦርነቱ እንዲቀጥል አድርጋለች። ተመድ አሁንም በርሷ መንገድ ስለሆነ UN - Useless Nations ብዬ ነበር።

አይሁዳዊው የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ከ12 ሚሊዮን በላይ ተከታታይ የነበረውን የጋዛን ገፅም በቋሚነት ዘግቶታል። እስራኤልን የሚነቅፉና ፈለስጢንን የሚደግፉ ልጥፎችን የሚለቁ ገፆችን ተከታትሎ በመዝጋት ላይ ይገኛል።

ያኛው አካውንት የመመለስ እድሉ 1% ገደማ ስለሆነ በነዚህ አዲስ ገፆቼ ፌስቡክ ላይ እገኛለሁ።

የ5000 ገደቡ እስኪሞላ ድረስ friend request እቀበላለሁ።

Profile: https://www.facebook.com/MuradTadesseOfficial

Page: https://www.facebook.com/MuradTadesseOfficialPage

በተጨማሪም በቴሌግራም ቻነሌ: t.me/MuradTadesse ላይ አለሁ።

የእስራኤል ወዳጆች (ምዕራባውያንና አውሮፓውያን) ፈለስጢንን የሚደግፍ ድረ ገፆችንና የቴሌቪዥን ሳተላይት ስርጭቶችን ጭምር እያሳደዱ በመዝጋት ላይ ስለሆኑ የኔን ገፅ በመዝጋታቸው አልገረምም።

ኢንሻ አላህ! እኛም አንፋታቸውም።

©: ፎቶ: ወንድም ዐብዱ-ር'ረሒም አሕመድ (ሃሩን ሚዲያ) የፌስቡክ ፕሮፋይሌን በሜታ ኩባንያ ሎጎ ቀይረው ሲዘጉት አጋጣሚ አይቶ በስክሪን ሹት ያስቀረው ምስል

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group