ምን ተፈጸመ? ዋና ዋና ጉዳዪች- የጋዛን ጦርነት በተመለከተ አጫጭር ማስታወሻዎች
__ RN05 __
👉የእስራኤል ተቃዋሚዎች ኔታንያሁ ስልጣን እንዲለቁ ጥሪ አቀረቡ
👉በጋዛ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ 51 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል
👉የዩኤስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የዮርዳኖስን ንጉስ አብዱላህ IIን ጨምሮ ቅዳሜ እለት ከአረብ ሀገራት መሪዎች እና ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው ነበር፣ነገር ግን የተኩስ አቁምን በተመለከተ አለመግባባቶች ተከስተዋል።
👉የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ እና የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይማን ሳፋዲ ጥቃቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡
👉 ብሊንከን ግን በጋዛ የተኩስ አቁም ይደረግ በሚለው ሃሳብ በይፋ አልተስማሙም።
👉 ዩናይትድ ስቴትስ ጦርነቱ እንዲቆም ሳይሆን የሰብአዊ እርዳታን ወደ ጋዛ ለማድረስ ይቻል ዘንድ ጦርነቱ ጋብ እንዲል ብቻ ነው የጠየቀችው፡፡
👉 ነገር ግን ይህንኑ ጦርነቱ ባዮምም ለጊዜው ጋብ ይበል የሚለዉን የብሊንከን ሃሳብን ደግሞ እስራኤል ታጋቾች አሁንም በታጣቂው ሃማስ እንደተያዙ ባለበት ሁኔታ እስራኤል ጦርነቱ ጋብ ብሎ እርዳታ ይግባ የሚለዉን የአሜሪካንን ሃሳብ ሃሳቡን አልቀበልም ነው ያለችው።
-------
👉ጦርነቱ እንዲቆም የሚፈልጉ እስራኤላውያን ቅዳሜ እለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ቤት ደጃፍ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማት ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል።
👉 ተቃዋሚ ሰልፈኞች "ናትያንያሁ አሁኑኑ ስልጣን ይልቀቅ! አሁኑኑ ይታሰር!" ሲሉ ነው የተደመጡት
------
👉"በጋዛ ስለሞቱት የሲቪል ሰዎች ሞት ማንኛውም የሰው ልጅ ሊያሳስበው ይገባል!" ሲሉ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መናገራቸው ተዘግቧል፡፡
👉አርብ እለት የእስራኤል መከላከያ ሃይል የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ ተሽከርካሪዎቹን ኦፕሬተሮችን እና የጦር መሳሪያዎችን ለመሸከም ሲጠቀምባቸው እንደነበር በመግለጽ በአልሺፋ ሆስፒታል አቅራቢያ የነበሩ ጉዳተኞችን ማመላለሻ አምቡላንሶችን ደበደቡ።
👉የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ማህበር በጥቃቱ ከ12 በላይ ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።
👉በጋዛ የሚገኘው የፍልስጤም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደገለፀው እስካሁን ከ9,200 በላይ ሰዎች በጋዛ ተገድለዋል። እስራኤል በበኩሏ ከ1,400 በላይ ሰዎች እንደተገደሉባት የገለጸች ሲሆን አብዛናው በኦክቶበር 7ቱ ድንገተኛ የሃማስ ጥቃት ወቅት የተገደሉ መሆናቸው ነው የተዘገበው፡፡
👉ባለፈው ሳምንት "ሀማስ ነጻ አዉጪ እንጂ አሸባሪ ድርጅት አይደለም" ሲሉ የተደመጡት የቱርክዬው ጠይብ ኤርዶጋን አሁን ደግሞ "የእስራኤሉ ናታንያሁ አሸባሪ ነው!" ሲሉ መወንጅላቸው ዳግም አነጋጋሪ አድርጓቸዋል፡፡
👉በአለም አቀፍ ደረጃ ከወትሮው በተለየ መልኩ በመላው አለም ፍልስጤማዊያንን የሚደግፍና በአስቸኳይ ጦርነቱ እንዲቆም የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች እየተደረጉ ይገኛሉ!
---