በዩ ቲዩብ ገንዘብ መቀበል እንደት ይታያል⁉️
============================
✍ ሌላኛው ባለፈ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ መልስ ከሰጠባቸው ጥያቄዎች አንዱ የሰማሁት በዩ ቲዩብ ቻነል በኩል ዩ ቲዩብ የሚከፍለውን ገንዘብ በተመለከተ ብይኑ ምንድን ነው የሚለው ነው።
ይህ ብዙዎቻችሁን ስለሚመለከት ቃል በቃል ባይሆን የመልሱን ይዘት ላጋራችሁ።
እኔ እስከማውቀው ድረስ ዩ ቲዩብ ገንዘብ የሚከፍለው ማስታወቂያ እንዲሠራላቸው የሚፈልጉ አካላት ገንዘብ ይከፍሉትና ዩ ቲዩብ ደግሞ ያንን እንዲሰራጭ የሚፈልጉትን ማስታወቂያቸውን በተለያዩ ቻነሎች ላይ የሚለቀቁ ቪድዮዎች ሲታዩ ማስታወቂያው ጣልቃ እንዲገባ በማድረግ ነው። እነዚህ የማስታወቂያ ጣልቃ የሚገባባቸው ቻነሎች ከዩ ቲዩብ ጋር መስፈርቱን አሟልተው ተነጋግረው ይህ ማስታወቂያ በሚሰሯቸው ቪድዮዎች ጣልቃ እንዲገባና ቪድዮዋቸውን የሚያይ እንዲያየው መፍቀዳቸው ነው። (በጎግል AdSense በኩል የሚፈጸመው የዩቲዩብ monetization ማለት ነው በአጭሩ!)
★
ነገሩ እንደዛ ከሆነ እነዚያ በማስታወቂያነት ጣልቃ የሚገቡት ነገሮች በይዘት ደረጃም ሆነ ማስታወቂያው በሚቀርብበት መንገድ ሐላልነታቸው ሊረጋገጥ ይገባል። ማለትም እነዚህ ማስታወቂያዎች ይዘታቸው በሸሪዓው የተከለከለ ሐራም ነገር መሆን የለበትም። በመሠረታቸው ሐላል ቢሆኑ እንኳ ማስታወቂያ የቀረበበት መንገድ ሐራም መሆን የለበትም። (ለምሳሌ፦ አንድ አዲስ ሐላል ለስላሳ መጠጥ ቢመረትና ያመረተው አካል ማስታወቂያውን ያሠራው በተገላለጠች ሴት ሊሆን ይችላል።)
ስለዚህ እነዚህ በየ ቪድዮው ጣልቃ የሚገቡ ማስታወቂያዎች (Ads) በይዘትም ሆነ በአቀራረብ ሐራም ከሆኑ በነርሱ ሰበብ የተገኘውም ገንዘብ ሐራም ይሆናል። ምክንያቱም አላህን በማመፅና በወንጀል መተባበር ስለሌለብን።
ምናልባት ግን ዩ ቲዩበሩ ከዩ ቲዩብ ጋር ስምምነቱን ሲፈጽም፤ በቪድዮው ላይ ጣልቃ እንዲገቡ የሚፈቅድላቸውን ኮንተንቶች ሐላል ሐላሎቹን ብቻ መርጦ ስምምነት መፈጸም የሚችልበት ነገር ካለ ችግር የለውም። ይሄን ደግሞ እርግጠኛ መሆን አለበት።
እንደ ጥቅል ደግሞ ዲናዊ በሆኑ ቪድዮዎች ገንዘብ ባይቀበልና ለአላህ ብሎ ቢሠራ የተሻለ ነው። ከዚያ ውጭ እንደ አካዳሚክና መሰል ሐላል ኮንተንቶች ላይ ይሻላል። ይሄውም ሐራም ማስታወቂያን መከላከል ከተቻለ ነው።
አላሁ አዕለም! በሉ! በዚህ ዘርፍ ላይ የተሰማራችሁና ለመሠማራት ያቀዳችሁ ካላችሁ ማስታወቂያውን ተውት፤ ወይም ለገንዘብ ከሆነ ደግሞ ሌላ ሐላል ከስብ ፈልጉ። በዚህ ሰበብ ነፍስያችሁን ካላሸነፋችሁ ሌላውንም ሐላል ገንዘባችሁን እንዳይበክልባችሁ።
||
t.me/MuradTadesse