UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ፍልስጥኤማውያን የቅን ሰዎችን ልቦች እያሸነፉ ነው!

ብዙ ሰዎች "እኛ ፍልስጤማዊ አይደለን! ምን አገባን? ደሞስ የኛን ጩኸት ማን ይሰማል?" እያሉ ለግፉአን ማሰማት የነበረባቸውን ድምፅ በገዛ እጃቸው ሲያፍኑ ይታያል።

ነገር ግን በዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመን በየትኛውም የዓለም ጥግ ያለ ሰው የሚያሰማው ጩኸት ተደማምሮ የመደበኛውን ሚዲያ አሻጥር ሰባብሮ ህዝብ እያነቃነቀ ነው። ሰፊው ህዝብ ከአሻጥረኛ መንግስታት በላይ መኾኑን በመላው ዓለም በታላቅ ድምፅ እያስተገባ ይገኛል። ከእንግሊዝ እስከ ኮሪያ ፣ ከቦሊቪያ እስከ ስፔይን ፣ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ጎረቤት ኬንያ ድረስ በርካታ የዓለም ህዝብ ከፍልስጥኤማውያን ጎን ቆሟል።

ዛሬ የፂዮናውያን ቅጥረኛ ምዕራባውያን መሠሪ ፖለቲከኞች ብቻቸውን ቀርተዋል። የአየርላንድ ፣ የስፓኝ ፣ የአሜሪካ ሴናተሮች የእስራኤልን ክፋት በፅኑ ኮንነዋል። ስፔን ደፈር ብላ የእስራኤልን መንግስት በአሸባሪነት ከስሳለች። የአየርላንድ ሴናተሮች እስራኤል ሽብርና የጦር ወንጀል እየፈፀመች መኾኑን መንግስታቸው በይፋ እንዲያውጅ ወትውተዋል። አዛውንቱ የአሜሪካው በርኒ ሳንደርስ እስራኤል ግፍ እየፈፀመች መኾኑ በግልፅ ቌንቋ ተናግረዋል።

በርካታ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች አይሁዳውያንን ጨምሮ የጺዮናውያንን ፋሺስታዊ አካሄድ በአደባባይ ኮንነዋል። በራሳቸው ሚዲያ ላይ ሳይቀር ቀርበው ሞግተው ረትተዋል። አፍቃሬ ፅዮናዊ ጋዜጠኞች ላይ ህዝብ ተሳልቆባቸዋል።

እስራኤልም በዓለም አቀፍ መድረክ ውርደቷን ተከናንባለች። "ሀማስ አሸባሪ ነው" የሚለው ሙግቷ ውሃ በልቶት እንዲያውም በግልባጩ ዓለም የኔታኒያሁ እና የእስራኤል መንግስትን አሸባሪነት በግልፅ አስተጋብቷል። እውነት ገሀድ እየወጣ ነው።

አስደናቂው ነገር ግን ፍልስጥኤማውያን ሰፊ ድጋፍና ተቀባይነት ያገኙት ከሙስሊምና ዐረብ ሃገራት ሳይሆን ከምዕራብ ሃገራት መኾኑ ነው። ጌታህ ስራው ረቂቅ ነው። አንተ ለወንድሞችህ ድምፅህን ብትነፍግ እሱ በመረጠው በኩል ይረዳቸዋል። ከግፉአን ወገን ለመቆም ቢተናነቅህ ከጠላት ወገን ድጋፍ ሲቸረው ታያለህ። ان الله ينصر الدين بالرجل الفاجر እንዲል።

ፍልስጥኤማውያን የቅን ሰዎችን ልቦች እያሸነፉ ነው። የቅን ሰዎችን ልብ ከማሸነፍ በላይ ምን ድል አለ?

image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

"Home is where the heart is" ይላሉ።

ቤታቸውን ልታፈርስ ትችላለህ። ነገር ግን ልባቸው ውስጥ የታተመውን የሀገር ፍቅር ልትነጥቅ አትችልም።

#palestineforever

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ጋዛ ውስጥ ይገኝ የነበረው ፥ እስራኤል ብዙ ንፁኌንን የፈጀችበትና ያወደመችው ሆስፒታል ከሀገረ-እስራኤል የበለጠ ዕድሜ አለው። እኤአ በ1904 የተገነባ ሲሆን በውስጡም ቤተክርስቲያን ነበረው።

@ Friends of Palestine

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Aktualisiere deinen Browser | Facebook

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group