Translation is not possible.

ከትናንቱ የሼይኽ ተውፊቅ ሳይግ የጁምዓ ኹጥባ በጥቂቱ የተወሰደ

ከምስራቅ አፍሪካውቷ ሀገረ ኤርትራ ተገኝተው በአለም አቀፍ ደረጃ ተደማጭነትን ካገኙ ቃሪዖች እና ኻጢቦች መካከል አንዱ መሆን የቻሉት ሼይኽ ተውፊቅ ሳይግ ስለ ሀበሻ ታላቅነት በሚያስደምም የንግግር ጥበባቸው የዘነጋነውን ቦታችንን አስታውሰውናል

በጁምዓ ኹጥባቸው በፍልስጤም ምድር እየሆነ ባለው አሳዛኝ እልቂት ሁላችንም ልባችን እየደማ መሆኑን ከማስታወስ ጋር ለኢስላም የዳዕዋ ጥሪ ጥላ ከለላ መሆን በቻለችው የሀበሻ ምድር ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል::

አርደል መህሸር (የመሰብሰቢያው መሬት) ከተባለቺው ሻም አስቀድሞ ፣ ኢማን የመናዊ ነው ከተባለላት የመን አስቀድሞ ከምርጦቹ ሀገር ሚስርም አስቀድሞ፣ ሌላው ቀርቶ ከታላቋ የስሪብ መዲናም አስቀድሞ የታላቁ ነብይ ባልደረቦች  የመጀመሪያው የኢስላምን ብርሀን ሊተክሉ የመጡት እዚሁ የሀበሻ ምድር ላይ መሆኑን፣ እንዲሁም በድርቁ ወቅት በረከቱል ሀበሺያ የረሱል ተንከባካቢ እንደነበረችው ሁሉ ሀበሻም እንዲሁ በከባዱ ወቅት ለሳቸውን ዳዕዋ መጠጊያ ሆና ጥላ ከላላ የሰጠች የተባረከች ሀገር መሆኗን አስታውሰዋል::

የሀበሻ ምድር ላይ ሰሀቦች ብቻ ሳይሆን ፣ የረሱለላህ ሴት ልጅና የሰይደና ዑስማን ባለቤት የሆነቺው ሩቅያን ጨምሮ ብዙ አህለል በይቶችም እንደተመላለሱባት በማስታወስ ከሁሉም ቀዲም እና ፊት የሆነች ሀገር እንዳለን በማስታወስ ጥንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም የሀበሻ ሙስሊሞች ቦታው ኃላ ሳይሆን ከፊት መሆኑን አውቆ በሁሉም ነገር ቀዳሚ እና ፊት መሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል::

ትውልዱ የትላንት ታሪኩን ሌሎች ከሚመሰክሩለት በላይ ሊያውቅ እና ዛሬም እንደ ጥንቱ የኢስላምን ብርሀን በመጠበቅ እና በማዳረስ ቀዳሚ መሆን እንደሚገባው በተለይ ወጣቱ ሊዘነጋው አይገባም::

ኡማ ቲቪ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group